Hiber Radio: የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ተጨማሪ ወታደራዊ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

በቅርቡ ተደጋጋሚ ወታደራዊ ጥቃት እየፈጸመ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱን ያስታወቀው አማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) ትላንት በጎንደር ጯሂት ወረዳ ላይ በአገዛዙ የአስተዳደር መዋቅር ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አስታወቀ። የአዴኃን ሙሉ መግለቻ ተከትሎ ቀርቧል።

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን)

አዴኃን በጎንደር ጯሂት ወታደራዊ ጥቃት ሰነዘረ! በጎንደር ክፍለ ሀገር ጯሂት ወረዳ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) በወረዳው በአስተዳደር ፅህፈት ቤት ላይ እና በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ የፌደራል ፓሊስ እና ፀረ ሽምቅ ግብረ ሃይል ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡

በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፌደራል ፓሊሶች እና ፀረ ሽምቆች የምሽት አሰሳ የሚያደርጉበትን ቦታና ማረፊያቸውን የአዴኃን ታጋዮች በማጥናት በትላንትናው ምሽት ማለት የካቲት 4÷2010 ዓ.ም ሌሊት 9 ሰዓት ላይ በወረዳው አስተዳደር ፅህፈት ቤት ግቢ የሰዓቱን የጥበቃ ተረኛ በማፈን በግቢው በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይገኙ የነበሩት 4 ፌደራል ፓሊሶችና 7 ፀረ ሽምቆች ላይ የቦንብ ጥቃት ሲፈፀም ፅህፈት ቤቱ ላይም በእሳት ጥቃት ተፈፅሞበታል፡፡

በተወሰደው ጥቃትም 8ቱ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ 3 በከባድ ቆስለው ለህክምና እርዳታ ወደ ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ትግላችን የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ካለው ልዩ የሆነ የፖለቲካ፤የኢኮኖሚ፤የማህበራዊ፤የስነ-ልቦናና የዘር ጥቃት ነፃ ወጦ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተከበሩባትና ለዚህም የሚቆሙ ነፃና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት ዕውን የሚሆኑባት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤የህዝብ አንድነት፤ፍቅርና እኩልነት የጠነከረባት፤ጠንካራና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ዕውን ሆና ማየት።ለዚህም የማንከፍለው መስዋዕትነት አይኖርም፡፡ በቁርጥ ቀን ልጆች አጥንትና ደም ወያኔ ይደመሰሳል!

አማራው ከታወጀበት የዘር ማጥፋትና ማፅዳት እራሱን ይታደጋል!!! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የካቲት 5÷2010 ዓ.ም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *