Hiber Radio: ከእነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጋር በአባሪነት የታሰሩት ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ ሌሎቹ ካልተፈቱ ከእስር እንደማይወጡ ገለጹ

በእነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ መፈንቅለ መንግስት በመጠንሰስ ስርዓቱን በሀይል ለማስወገድ ተደራጅታችሁዋል ተብለው በአገዛዙ ክስ ሳቢአ ዕድሜ ልክ ተፈርዶባቸው ባለፉት አስር ዓመታት በእስር ላይ የሚገኙት ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ  ለፍቺ የተሐድሶ ስልጠና ላይ ከነበሩበት አብረውኝ የታሰሩት እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ካልተፈቱ ከእስር አልወጣም በማለታቸው ወደ እስር ቤት መመለሳቸው ተገለጸ።

የወ/ሮ እማዋይሽ ልጅ ወጣት ናርዶስ ዘሪሁን ከስደት ካለችበት እንዳስታወቀችው እናቷ እስረኞች ከመፈታታቸው በፊት የሚሰጠውን ስልጠና ለመውሰድ ከሔዱበት ባቀረቡት ቅድመ ሁኔታ ሳቢያ ሳይፈቱ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተመልሰዋል።

ከወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ በተጨማሪ ከፍቺ በፊት ይሰጣል ከተባለው ስልጠና ተመርጠው ከተመለሱት ባጩ መርጋ፣አየለች አበበም ወደ ቃሊቲ መመለሳቸው ታውቋል።

ወ/ሮ እማዋይሽ በአማራ ብሄር ተወላጅነታቸው ሳቢአ ማዕከላዊ ጡታቸው በምላጭ እየተተለተለ ጭምር ከፍተኛ ግፍ ተፈጽሞባቸው በቀረበባቸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሳቢያ ዕድሜ ልክ ከተፈረደባቸው በሁዋላ ሰሞኑን በአገዛዙ ላይ ከአገር ውስጥና ከውጪ እየተፈጠረ ባለ ጫና ይፈታሉ ተብለው ለከሚጠበቅ የፖለቲካ እስረኞች አንዷ ነበሩ። ቀደም ሲል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አበበ ቀስቶ ፣አንዷለም አጋራ ለፍቺ የቀረበላቸውን ቅድመ ሁኔታ ላይ አንፈርምም ብለው የተቃወሙ ሲሆን ድጋሚ የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ መጤቃቸው ቢሰማም እስካሁን እነሱን ጨምሮ በሺህ የሚቆጠሩ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች ዛሬም በልዩ ልዩ እስር ቤቶች በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ።

ወ/ሮ እማዋይሽ እንዲፈቱ የጠየቋቸው አብረዋቸው የታሰሩት እነ ጄ/ል ተፈራ ማሞ፣ጄ/ል አሳምነው ጽጌና ኮ/ል ደምሰው አንተነህ በማዕከላዊ ከፍተኛ ግፍ እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤት መግለጻቸው አይዘነጋም።

እማዋይሽ ዓለሙ፣ ባጩ መርጋ እና አየለች አበበ ለቅድመ ፍቺ ሥልጠና ከተላኩ በኋላ ተመርጠው ወደ ቃሊቲ ተመልሰዋል። ለምን እንደተመለሱ አልታወቀም። በሌላ በኩል፣ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለሥልጠናው ከተላኩት ውስጥ መሆኑ ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የመኢአድ ሕጋው ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማራን ጨምሮ ለፍቺ ስልጠና እየወሰዱ ነው ቢባልም እስካሁን እሳቸውን ጨምሮ ከ122 የመኢአድ አመራሮች እና ሌሎች በርካታ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች አለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እየተጠየቀ ነው።

ቄሮ የጠራውን ሶስት ቀን የስራ ማቆም አድማ በሁለት ቀኑ የተሳካ ተቃውሞ የተደናገጠው አገዛዝ አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች ዘጠኝ ሰዎችን ቢፈታም ዛሬም እስር ቤት የቀሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እስኪፈቱ ጥአቄው ተጠናክሪ መቀጠል እንዳለበት ብዙዎች መጠየቅ ጀምረዋል።ወጣቱዋ ንግስት ይርጋ ከተፈቺዎች ውስጥ አለመካተቱዋም ታውቋል።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *