Hiber Radio: የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ከሕዝቡ ደማቅ ድጋፍ ተቸራቸው

በተለያዩ ጊዜያት ሀሳባቸውን በነጻ በመግለጻቸውና ከገዢው የህወሃት በላይነት ሞመራው አገዛዝ የተሌ አቋም በማራመዳቸው በጠላትነት ተፈርጀው በልዩ ልዩ የፈጠራ የሽብር ክስ ሳቢአ ተፈርዶባቸው አሉም ሆነ በቀጠሮ ካሉ በሺህ የሚቆጠሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች  መካከል ዛሬ የተለቀቁትን ጋዜጠና እስክንድር ነጋ፣የቀድሞው ሕጋዊው የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አንዷለም አራጌ፣የመኢዴፓ አመራር አበበ ቀስቶ፣ናትናኤል መኮንን፣የኦፌኮ ኦልባና ሌሊሳ፣የእድሜ ልክ ፍርደናዋ ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ፣የጋምቤላው የቀድሞ ፕ/ት ኦኬሎ አኳይ እና ለሌሎቹም ሕዝቡ ዛሬ ከቃሊቱ ከወጡበት ሰዓት ጀምሮ አክብሮቱን ገለጸ።የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኪሚቴ አባላት መካከል የህዝብ ግንኑነቱ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበልና ሌሎችም ተፈተዋል።

ትላንት የተፈቱት የኦፌኮው ም/ል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ በአዳማ ስታዲየም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ የጀግና አቀባበል ያደረገላቸው ሲሆን የከተማዋ ከንቲባም በስፍራው ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸው በኦህዴድ በኩል እየታየ ያለውን ለውጥ በለጠ ተስፋ ሰጪ አድርገው የወሰዱ አሉ።

እነ ጋዜጠና እስክንድርን በብዙ ሺህ የሚቆተር ህዝብ.የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ጋዜጠኞች፣ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ከቃሊቲ ደጃፍ ጀምረው ሞቅ ያለ አቀባበል ማድረጋቸው በብዙዎችን ያስደሰተ ሲሆን የአገዛዙ የፌዴራል ፖሊሶች በተቃራኒው ለአቀባበል ከወጡት መካከል ጋሻነህ ላቀ፣ይድነቃቸው አዲስ፣አዲሱ ጌታነህ፣ባየልኝ ብርቁ፣ስለሽ ደቻሳ፣ጥላሁን እና ሌሎች ወጣቶች ንፁሁን ሰንደቅ አላማ ይዛችሁ ከእስር የተፈቱትን አጅባችኋል ተብለው መታሰራቸው ታውቋል።

ጋዜጠና ውብሸት ታዬ ከዝዋይ እስር ቤት የተፈታ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሺህ የሚቆጠሩ የህሊና እስረኞች ዛሬም እየማቀቁ መሆናቸውን ትላንት አቶ ደጀኔ ጣፋ ለመገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ይታወሳል። እነ መ/አ ማስረሳ ሰጡን ጨምሮ እስር ቤቱ በኦሮሞና በአማራ ብሄር ተወላጅ እስረኞች ተጨናንቋል። የቅሊንጦ ቃጠሎ በሚል ሀሰተኛ ክስ ከሚማቅቁት ውስጥ በቅርቡ ተማጽኖ ደብዳቤ የጻፉት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ቀደም እነ መ/አ ማስረሳ ድረሱልን ዐቃቤ ሕግ ያሰለጠናቸው የሀሰት ምስክሮች እንዳይመሰክሩብን ለዓለም አጋልጡልን ማለታቸው አይዘነጋም።

በመፈንቅለ መንግስት በሚል ከታሰሩት መካከል ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ ሲፉ እነ ጄ/ል አሳምነው ጽጌና ብ/ጄ/ል ተፈራ ማሞን ጨምሮ በአባሪነት የተከሰሱት፣ከጎንደር ተግዘው ከመጡ ወጣት ንግስ ይርጋን ጨምሮ ብዙዎቹ፣የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት እና የዋልድባ መለኮሳት መቼ እንደሚፈቱ አልታወቀም።

የመኢአድ ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማረ ዛሬ ከተፈቱት የሚገኙ ሲሆን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊውን ለገሰ ወ/ሃናን ጨምሮ ከመቶ በላይ አመራሮች ዛሬም እስር ቤት ናቸው።ትግሉ በርካታ ንጹሃን መስዋዕት የከፈሉበት የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄና ሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ተጠይቋል።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *