Hiber Radio:ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ ጥቂት የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸው ተገለጸ፣በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ዛሬም እስር ቤት አሉ

የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ዝግጅት አድርገዋል በሚል ተይዘው ከፍተኛ በደል የተፈጸመባቸው የቀድሞ ታጋይ እና የሰራዊቱ ብ/ል ጄራል ተፈራ ማሞ፣ጄኔራል አሳምነው ጽጌን ጨምሮ በአባሪነት የታሰሩትን ከፌዴራል እንዲሁም የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባል  ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች የተወሰኑ የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ የተገለጸውን ተከትሎ ኮ/ል ደመቀ ማምሻውን መፈታታቸው ታውቋል።

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ ወጣት ንግስት ይርጋና ሌሎች በተመሳሳይ ወቅት የአማራን ሕዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴና ተጋድሎ ተከትሎ ከተያዙት ጥቂቶቹ ዛሬ የተፈቱ ሲሆን  ዛሬም ብዙዎች በየእስር ቤቱ ይገኛሉ።

እነ ጄ/ል አሳምነው ጽጌና፣ብ/ጄ.ል ተፈራ ማሞም ከተፈቺዎች መካከል የተገለጸ ቢሆንም መፈታታቸውን በእርግጠኝነት መናገር አልተቻለም።

በማዕከላዊ፣በቅሊንጦ፣በሸዋ ሮቢት፣በዝዋይ እና በሌሎችም እስር ቤቶች ከታሰሩት መካከል በደረሰባቸው ድብደባ ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው የፖለቲካ እስረኞች ከእስር እንዳይወጡ ወደ ሁዋላ አስቀሯቸው መሆኑም እየተገለጸ ይገኛል። የሕጋዊው መኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሰት አማረ ሰሞኑን ከእነ አቶ በቀለ ገርባ ጋር ቢፈቱም የፓርቲውን የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ለገሰ ወ/ሀና፣ ሌላው የፓርቲው አመራርና በማዕከላዊ በደረሰበት ድብደባ የአካል ጉዳት የደረሰበት ዘመነ ጌጤን ጨምሮ በርካቶች እስር ቤት ናቸው።

ከቅሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ጋር በተገናኘ በሀሰት ተከሰው በሸዋ ሮቢት ታስረው ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው እነ መ/አ ማስረሻ ሰጤ ጨምሮ በመቶ የሚቆጡሩ የፖለቲካ እስረኞች አልተፈቱም። የሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ተወካይ የነበረው አግባው ሰጠኝ ፣ የግንቦት ሰባት ወና ጸሐፊው የነጻነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣እውቁ የልብ ሕመም ሐኪም ዶ/ር ፍቅሩ ማሩና ሌሎችም እስኪፈቱ የእስረኞች ይፈቱ ጥያቄው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተጠየቀ ነው።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *