Hiber Radio: ኮሎኔል ደመቀን ከጎንደር እስር ቤት ተለቀው ተመልሰው እንዲያዙ ሀሳብ ቀርቧል የሕወሓት መሪዎች ኮ/ል ደመቀን ፌዴራል አዟል በሚል አፍኖ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሱ ነው፣ሰሞኑን ጎንደር ውስጥ የተከሰተው ግጭት እና ውጥረት አገዛዙ ለዓመታት የዘራው የጥላቻ ፖለቲካ ውጤት መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 10 ቀን 2008 ፕሮግራም

<… የወልቃይት ጉዳይ ብዙ ሲብላላ የቆየ ነው ። ሕወሓት ያልገባው እነዚህ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ የኮሚቴ አባላት ታጋዮች የነበሩ በሕዝቡ ውስጥ የተከበሩ ናቸው ። እነሱን በቀላሉ አፍነን የፈለግነውን እናደርጋለን ማለታቸው ትልቅ ስህተት ነው ሕዝቡ ለመብቱ አንድ ሆኖ ቆሟል …የኦሮሞ ሕዝብ እና በጎንደር የተነሳው የአማራ ሕዝብ ተቃውሞ ከኦሮሚያው ተቃውሞ ጋር የሚመሳሰልም ነገር ታያለህ በእርግጥ በጎንደር ግድያው ያልበዛው እነሱ ሲገድሉ የሚገድል እንዳለም አሳይተዋል … > ጃዋር መሐመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ስለ ጎንደሩ ተቃውሞ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ (ክፍል አንድ ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ከዚህ በሁዋላ የአማራ ሕዝብ አንድ ሆኖ ሕወሓት ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት የፈጸመበትን የዘር ማጥፋት ወንጀል በጋራ ሆኖ የሚመክትበት ወሳኝ ወቅት ነው ። ይሄ የዲሞክራሲ ትግል ብቻ አይደለም ለአማራ ጎንደር ላይ የተጀመረው ትግል የህልውና ትግል ነው…ከኦሮሚያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ብዙ ልምዶች መውሰድ ይቻላል በተለይ ተቃውሞውን በፍጥነት ወደ ብዙ አካባቢዎች ማስፋቱ ላይ ነገር ግን ከዚህም እነሱ ልምድ ሊወስዱ ይችላሉ ሕወሓት የሚያውቀው ገድሎ መሄድ ብቻ ሳይሆን መገደል እንዳለም ሕዝቡ አሳይቷል አሁንም ይሄ ትግል ጎንደር ላይ ብቻ ሳይሆን…> ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የቀድሞ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ከጃዋር መሐመድ ጋር በአንድ ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ክፍል አንድ ያዳምጡት)

<..ኮሎኔል ደመቀንም ሆነ ታፍነው የተወሰዱት አራቱ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ የህዝብ ወኪል የኮሚቴ አባላት እንዲያመጡ ጠይቀናል ። በፍጹም ኮሎኔልንም አፍነው አይወስዱትም ።የአካባቢው የጸጥታ ክፍል ሀላፊዎች ቃል ገብተውልናል…ይሄ ትግል የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ነው ያንን ማክበር ትተው ኮሎኔሉን አፍኖ በመውሰድ ሰዎችን በመግደል ሊያስቆሙት በጭራሽ አይችሉም የወልቃይት ጉዳይ የመላው አማራ የህልውና ጉዳይ ነው…> አቶ ሽፍቅ አደም ከወልቃይት የአማራ ማንነት የሕዝብ ተመራጭ የኮሚቴ አባላት አንዱ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ (ቀሪውን ያድምጡ)

የአሜሪካ እና የም እራባዊያን አገራት ቁልፍ ሸሪክ የሆነቸው ቱርክ ከመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አመለጠች ፣በርካታ ዜጎቿ ሞተዋል፣ ሺዎች ቆስለዋል፣ አፈንጋጭ ወታድሮች እና ዳኞች ታስረዋል። ከመፈንቀለ ምንግስቱ የትረፉት ፕ/ቷ “አፈንጋጮቹ የዋጋቸውን ያገኛሉ”ሲሉ ዘተዋል(ልዩ ጥንቅር)

የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውድድር እና የትኛው ዕጩ ለኢትዮጵያ አሜሪካውያን መራጮች የተሻለ ነው (ሁለተኛ ክፍል ውይይት ከፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ጋር)

በቬጋስ በስራ ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የታክሲ አሽከርካሪ ጉዳይ

የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጥሪ

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

ኮሎኔል ደመቀን ከጎንደር እስር ቤት ተለቀው ተመልሰው እንዲያዙ ሀሳብ ቀርቧል

የሕወሓት መሪዎች ኮ/ል ደመቀን ፌዴራል አዟል በሚል አፍኖ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሱ ነው

ሰሞኑን ጎንደር ውስጥ የተከሰተው ግጭት እና ውጥረት አገዛዙ ለዓመታት የዘራው የጥላቻ ፖለቲካ ውጤት መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ

ግብጽ”አባይ ከሌለ ሕዝቤ አይኖርም ስትል”ዳግም ስጋቷን ገለጸች፣ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን እሰጣእገባ ለማስቆምም ካይሮ የእስራኤል ጥልቃ ገብነትን ትሻለች

በፕ/ር መረራ ጉዲና የሚመራው ኦፌኮ የዓለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን አገዛዙ በጎንደር የወሰደውን የመብት ረገጣ አወገዘ

ግድያው በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል

“የአማራ እና የትግራይ ሕዝብ ለዘመናት በሰላም ኖሯል፣ወደፊትም በፍቅር እና በስምምነት   ይኖራል”የጎንደር ነዋሪዎች

ኤርትራ የጸጥታው ምክርቤት የጣለባት ማእቀብ እንዲነሳላት እና ኢትዮጵያም ጦሯን ከአወዛጋቢው ድንበር እንድታስወጣ ጠየቀች

 ለአሰመራ መንግስት ወታደራዊ መርጃ ሲያቀብሉ ነበሩ የተባሉ ኤርትራዊያኖች እና ኢትዮጵያዊያኖች ሰሞኑን የእስራት ፍርድ ተበየነባቸው

ሀብታሙ አያሌው በጸና እንደታመመ ነው

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Advertisement

2 Responses to “Hiber Radio: ኮሎኔል ደመቀን ከጎንደር እስር ቤት ተለቀው ተመልሰው እንዲያዙ ሀሳብ ቀርቧል የሕወሓት መሪዎች ኮ/ል ደመቀን ፌዴራል አዟል በሚል አፍኖ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሱ ነው፣ሰሞኑን ጎንደር ውስጥ የተከሰተው ግጭት እና ውጥረት አገዛዙ ለዓመታት የዘራው የጥላቻ ፖለቲካ ውጤት መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች”

 1. Lewawi Teshome

  Jul 18. 2016

  Welcome

  Reply to this comment
 2. Tesfaye Molla

  Jul 19. 2016

  hi thanks for u’r urgent information.does it cost if i want listen the program through my phone?

  Reply to this comment

Leave a Reply