Hiber Radio: ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩና በእስር ላይ ያሉ ወገኖችን በነገው ዕለት ለማሰብ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጠራ

በአገር ቤት በሕዝቡ ላይ የሚደርሱ በደሎችን ያለ ፍርሃት በማህበራዊ ሚዲያው በተለይም የህሊና እሰረኞችን ጉዳይ ጭምር እየተከታተለ በመዘገብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በአሁኑ ወቅት ሀሳቡን በነጻ በመግለጹ ታስሮ እየደረሰበት ያለውን እንግልት በመማብ እሱና ሌሎችም በእስር ቤት መከራ እየከፈሉ የሚገኙ ጋዜጠኞችን ለማሰብ በነገው ዕለት በማህበራዊ ሚዲያው የዘመቻ ጥሪ ቀረበ።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ድንገት ታፈኖ ከታሰረ በሁዋላ ለወራት ያለ ክስ ከጣቢያ ጣቢያ እየተመላለሰ ቆይቶ በቅርቡ ክስ መስርተው ፍርድ ቤት ያቀረቡት ሲሆን ወደ ቅሊንጦ ተዛውሮ የተመሰረተበትን የሀሰት ክስ እየተከታተለ የሚገኝ ሲሆን በመጪው ረቡዕ ውደቅ በተደረገው የዋስትና ጥያቄው ላይ ተቃውሞ ፍርድ ቤት አንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል። #Justice4Elias#Freealljournalists#

 

 

 

Advertisement

No comments.

Leave a Reply