Hiber Radio: <<በምርመራ ወቅት የግድያ ዛቻ ተደርጎብኛል>> የቀድሞው የአየር ኃይል አብራሪ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ

ስም፡- ማስረሻ ሰጠኝ

ዕድሜ፡- 34

አድራሻ፡- ድሬዳዋ ከተማ

አሁን በእስር የምገኝበት ቦታ፡- ቂሊንጦ እስር ቤት

ለእስር የተዳረግሁበት ምክንያት፡- በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረሃል የሚል ነው፡፡

በይፋ የተመሰረተብኝ የክስ አይነት፡- ቀደም ሲል የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀጽ 7(1) መተላለፍ የሚል የሚል የሽብር ክስ እንዲሁም የመንግስትን ጦር መሳሪያ ይዞ መሰወር የሚል ክሶች ነበር የቀረቡብኝ፡፡ በእነዚህ ክሶች የአስር አመት ፍርደኛ ነኝ፡፡ አሁን ላይ ደግሞ በነሐሴ 2008 ዓ.ም ቂሊንጦ እስር ቤትን አቃጥላችኋል በሚል የሽብር ክስ ከቀረበባች እስረኞች መካከል አንደኛ ተከሳሽ አድርገው ከሰውኝ በእስር ላይ እገኛለሁ፡፡

 

በእስር በምገኝበት ወቅት የሚከተሉት የመብት ጥሰቶች ተፈጽመውብኛል፡፡

ሀ. ማዕከላዊ ወንጅል ምርመራ እያለሁ

 1. ቀዝቃዛና ጨለማ ክፍል ታስሬያለሁ፡፡
 2. ጠያቂና የህግ ባለሙያ እንዳላናግር ተከልክየ ቆይቻለሁ፡፡
 3. ስድብና ዛቻ ደርሶብኛል፡፡
 4. ማታ ማታ ምርመራ ተደርጎብኛል፡፡

ለ. በቂሊንጦ ቃጠሎ ክስ ምክንያት ሸዋሮቢት ለምርመራ በተወሰድሁባቸው ጊዜያት

 1. የግድያ ዛቻ ደርሶብኛል፡፡
 2. ሲቪል በለበሱ መርማሪዎች በተደጋጋሚ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡
 3. ሁለቱን የእጅ አውራ ጣቶቼን በሲባጎ አስረው አሰቃይተውኛል፡፡
 4. ልንገድልህ ነው እያሉ በመዛት ሜዳ ላይ ወስደው ፊቴ እስኪያባብጥ ደብድበውኛል፡፡
 5. ስድብ፣ ዛቻ፣ ማንቋሸሽ፣ የንቀት ንግግር አድርሰውብኛል፡፡
 6. ቀንና ሌሊት በካቴና ታስሬያለሁ፡፡ በተለይ ማታ ማታ ከአልጋ ጋር ያስሩኝ ነበር፡፡
 7. ጸጉሬን እየነጩ፣ የነጩትን ጸጉር እያሳዩ፣ ‹‹አንተ ለዚህ መንግስት እንደዚህ ጸጉር ደቃቅ ነህ›› እያሉ ተሳልቀውብኛል፡፡
 8. በግዳጅ እነሱ የሚፈልጉትን ብቻ እንድናገር እያደረጉ በቪዲዮ ቀርጸውኛል፡፡
 9. ሽንት ቤት ጥንድ አድርገው በካቴና አጣምር ከሌላ እስረኛ ጋር በማሰር አብረን እንድሄድ አስገድደው፣ ክብረ ነክ በሆነ መልኩ አንዳችን ስንጸዳዳ ሌላችን ቆመን እንድናይ ተድርጌያለሁ፡፡
 10. በግዳጅ የሰጠሁት ቃል ላይ ተገድጄ እንድፈርም ተደርጌያለሁ፡፡

 

*የተወለድሁት ምስራቅ ጎጃም ነው፡፡ ትምህርቴን የተማርሁትም በተወለድሁበት አካባቢ ነው፡፡ እስከታሰርሁበት ጊዜ ድረስ ድሬዳዋ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል በአብራሪነት እሰራ ነበር፡፡ የመኖሪያ አድራሻዬም እዚያው ድሬዳዋ ከተማ ነበር፡፡

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Advertisement

No comments.

Leave a Reply