Hiber Radio: በአሜሪካና በአውሮፓም ግፍ የፈጸሙ የሕወሃት/ኢህአዴግ መሪዎችን መክሰስ ስለመቻሉ፣የቴዲ አፍሮ አልበም ምርቃት መታገድና የሕዝቡ ቁጣ፣የደቡብ ሱዳን የደህነት ሀይሎች ጋምቤላ አስተዳደር ውስጥ መግባት፣የስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት ኤርትራውያን ስደተኞችን አባርራለሁ ማለቱ፣ቤተ ክርስቲያን እንዲፈርስ መደረጉ፣ራያ ቢራ መስቀልን ለቢራ ማስታወቂያ መጠቀሙ ያስነሳው ተቃውሞ፣የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ዛሬም ትግሉን እንዲያግዙ መጠራት፣ትግራይ ክልል ተለይታ ሽልማት ማግኘቱዋ ያስነሳው ጥያቄ፣በእስራኤል የትውልደ ኢትዮጵያዊው ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመት ማግኘት እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 28 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በእንግሊዝ የሚገኙ ኤርትራውያን ሰቆቃ ፈጽሞብናል ያሉትን ኤርትራዊ ባለስልጣን ባሉበት አገር ሕግ መሰረት ክስ መስርተዋል። በርካታ ኢትዮጵአውያን የስቃይ ሰለባዎች ጭምር በውጭ አገር ይኖራሉ ግፍ የፈጸሙ የወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣናትን በውጭ አገር ለፍርድ ለማቅረብ የሚቻልበት ዕድል እያለ ያአልተደረገም. .. በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ ሽብርተኝነትን ሽፋን አድርጎ የእንግሊዝ መንግስት ከወያኔ ጋር ተመሳጥሮ የሚፈጽመው ድርጊት ግን…> አቶ ያሬድ ሀ/ማርያም የሰብኣዊ መብት ተሟጋች የሆነው ድርጅት ዳይሬክተር ከቤልጂየም   በወቅታዊ ጉዳይ ከህብር ጋር ያደረገው  ቃለ ምልልስ(ቀሪውን አዳምጡት)

<…የአንድ ስርዓት መፍረስ ምልክቱ ሕግን መጣሱና ሕግን አለማክበሩ ነው።ይሄ ስርዓት በሕግ ላይ የፈጸመው ህገ ወጥ ተግባር የራሱን ውድቀት ነው የሚያመጣው…የኬኒያ ዳኞች ውሳኔ ታላቅ ወኔ የሚጠይቅ ከዕለታዊ ጥቅም በላይ አገርና ሕዝብን ያስቀደመ ለዕውነትና ለፍትሕ የመቆም በትልቅ ወኔ የተፈጸመ ታላቅ ተግባር ነው። በኬኒያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ግን መጪው ምርጫ ይፈጸማል የሚለው ላይ…> አቶ አለማየሁ ዘመድኩን በኢትዮጵያ የ<<ፍትሕ>> ሚኒስቴር ረዳት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የፍትሐብሄር ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ የነበሩ የኬኒያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ መሰረት አድርገን በኢትዮጵያ ስላለው የፍትህ ስርዓት ከሰጡን ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

ኬኒያ ፕ/ታዊ ምርጫን በመስረዝ ከአለም አራተኛ አገር ያደረጋት ሰሞነኛው  የፍ/ቤት ውሳኔ ሲዳሰስ(ልዩ ዘገባ)

የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት የአትላንታ ጉዳዔ በተመለከተ የተደረገ ቃለ ምልልስ(አድምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በአሜሪካና በአውሮፓም ግፍ የፈጸሙ የሕወሃት/ኢህአዴግ መሪዎችን ከሳሽ ካለ ለፍርድ ማቅረብ እንደሚቻል ተገለጸ

የደ/ሱዳን የደህንነት ሀይሎች በጋምቤላ መስተዳደር ውስጥ ስውር እጆቻቸውን መክተታቸው ተጋለጠ

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በራሱ ወጪ በሒልተን ሆቴል በጠራው የኢትዮጵያ አልበም ምርቃት መታገድ ላይ መግለጫ ሰጠ

በክልከላው ብዙዎች ቁጣቸውን እየገለጹ ነው ስልጣን ላይ ያሉትን ሰዎች የመንደር ጎረምሶች ድርጊት ማሳያ ነው ተብሏል

በኦሮሚያ ውስጥ የኢህአዲግ ካድሬዎች ቤተ ክርስቲያን አፈረሱ፣ንዋየ ቅድስት እናጽላትን መጣላቸውም ታላቅ  ቅሬታ አስነሳ

“ደርግ እንኳን እንደዚህ አይነት ግፍ እና በደል አልፈጸብንም።”ቅር ከተሰኙ ምእመናኖች የተወሰደ አስተያየት

በህወሓቱ ቀድሞ ጄኔራል ጻድቃን ባለቤትነት የቋቋመው ራያ ቢራ መስቀልን ለማስታወቂያ በመጠቀሙ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ቁጣቸውን እየገለጹ ነው

የሕወሓቱ ጳጳስ አቡነ ማቲያስ ዝምታን መርጠዋል

 ስዊዘርላንድ በግዛቷ የሚገኙ በርካታ የኤርትራዊያ ተገን ጠያቂዎችን ልታባርር መሆኗን አስታወቀች፤

ወደ አገራችሁ ብትመለሱ እስራት እና ብቀላ አይጠብቃችሁምሰሞነኛው የስዊዝ /ቤት ውሳኔ አሳለፈ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት ዛሬም ትግሉን እንዲያግዙ ጥሪ ቀረበ

ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን ጨምሮ ማህበሩን የሚመሩ ተመርጠዋል

የትግራይ ክልላዊ መስተዳደር በተናጥል የሁለት የአለማቀፋዊ የሽልማቶች ባለቤት መሆኑ እያነጋገረ ነው

የተቀሩት የኢትዪጵያ ግዛቶች እስከ መቼ ድረስ የበይ ተመልካቾች ይሆናሉ?”የአገር ወዳዶች ወቅታዊ ጥያቄ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዶክተር እስራኤል ውስጥ የመጀመሪያ የማህበረሰቡ ከፍተኛ መኮንን ሆነው ተሾሙ

የአይጦች መንጋ የናይጄሪያው ፕ/ትን ከቤተ መንግስታቸው አባረራቸው

ፕ/ቱ ከቤታቸው ሆነው የመንግስት ስራን ለማከናወን መገደዳቸው አለማቀፍ አግራሞትን አጫጭሯል

እና ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Advertisement

No comments.

Leave a Reply