Hiber Radio: በሕዝባችን ላይ አንተኩስም ያሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ኮሎኔሎች ከሰራዊቱ ውስጥ መታሰር መጀመራቸው ተገለጸ፣ አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ፣የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ካይሮን እና አ/አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ፣ በ ታላቁ አንዋር መሰጊድ የደረሰው የቦንብ አደጋ አነጋጋሪ ሆኗል፣ እንግሊዝ ዜጎቿ ወደ መርካቶ እና መሰል ስፍራዎች እንዳይሔዱ አሰጠነቀቀች፣የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ የው/ጉ/ሚ/ርን ለመጀመሪያ ጊዜ በግንባር አነጋገሩ፣ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው ፣የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ፣ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ፣ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ፣ ቃለ መጠይቅ ከጃዋር መሐመድና ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር በወቅታዊ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና ትግሉ ወደ ብሄራዊ ተቃውሞ ስለሚያድግበት ሁኔታ ሌሎችም ወቅታዊ ዝግጅቶች አሉን
https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-121315-122015 የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 3 ቀን 2008 ፕሮግራም <…የህወሃት አገዛዝ አንዱን ብሄር ከሌላው ጋር ለማጋጨት ባለፉት በተማሪዎች ተቃውሞዎች የሄደበት ሴራ ዛሬ ከሽፏል፣ተማሪዎቹ አስቀድመው ስትራቴጂ አውጥተዋል።ይሄ የተለመደ የማጋጨት ስልትን እንኳን ሰው …
Read More
