Hiber Radio: ጎንደር ሕብረት ወያኔ ጎንደርና ቅማንትን ለመከፋፈል ማሰቡን ትቶ ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ ጠየቀ፣የአሜሪካው ፕ/ት ዶናል ትራምፕ ” ሕይወታቸው በሰው እጅ ያልፋል” ያሉት የህዝብ እንድራሴ ታላቅ ተቃውሞ አስነሱ፣በኦሮሚያ ክልል ከረቡዕ ነሐሴ 17 ጀምሮ ለአምስት ቀን የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ ተጠራ ማስጠንቀቂያም ተላልፏል፣የባሕር በር አልባዋ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገር ወደብ ለመግዛት እየተደራደረች ነው፣በአገር ቤት የአዲስ ዓመት ኮንሰርቱ ለታገደበት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በመላው ዓለም በማህበራዊ ሚዲያው ዳግም ሊከበር ነው፣በካናዳ በአሰቃቂ የመኪና አደጋ ሕይወታቸው የጠፋውን ሶስት ልጆች አስከሬን ለማጓጓዝ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ፣እነ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለቀረበባቸው የፍርድ ቤት ማዘዣ ተገዢ የመሆናቸው ጉዳይ እያጠራጠረ ነው እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 14 ቀን 2009 ፕሮግራም <…ወያኔ ጎንደርን ብቻ ሳይሆን ለራሱ እንዲያመቸው ሁሉንም ለመከፋፈል ሞክሯል።ጎንደርን በአራት ለመክፈል ያሰቡት  ወልቃይትን ጨምሮ የትግራይ አካል አድርገው በጉልበት ለማስቀረት ነው። ይሄ የጀመሩት ከፋፍሎ ለማዳከም …

Read More

Hiber Radio: ተቃዋሚዎች በአስቸኳይ አማራጭ መንግስት ተባብረው እንዲመሰርቱ አቶ ሌንጮ ለታ ጥሪ አቀረቡ፣ፋሺስት ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ ላደረሰው የመርዝ ጋዝ ጭፍጨፋ የእንግሊዞች ድጋፍ እንደነበረው ተጋለጠ፣በአማራ ስም ትግራይ በሽማግሌ ስም ከሔዱት ብዙዎቹ ሕዝቡን ሲያስገድሉና ሲገሉ የነበሩ መሆናቸው ተገለጸ፣አንድ ምእራባዊያን አገር ጎብኚ ኢትዮጵያ ውስጥ ከባለቤታቸው ፊት በዝሆን ተጨፍልቀው ሞቱ፣በሳውዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዛሬም አሳሳቢ ነው የምህረት አዋጁ ዳግም እንዲራዘም ተጠየቀ፣ከቁርጥ ግብር ጋር የተነሣው ተቃውሞ ብሔራዊ አቅጣጫ ሊይዝ እንደሚችል ባለስልጣናቱ ስጋታቸውን ገለጹ አገዛዙ ሽንፈት ደርሶበታል ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 16 ቀን 2009 ፕሮግራም <…ተቃዋሚዎች ራሳችንን ማታለል የለብንም። በአስቸኳይ ከኢህአዴግ ተቃራኒ የሆነ ሀይል መፍጠር አለብን። እነሱ ስልጣን ላይ ሲወጡ ሁለት ስትራቴጂ ነድፈው ነው። ከቻሉ ኢትዮጵያን መግዛት ካልቻሉ …

Read More

Hiber Radio: ጃዋር መሐመድ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ የተባለው አዋጅ ሕወሃት የማስተር ፕላን ማስፋፊያ ያለውን ተግባራዊ ለማድረግ የወጣ መሆኑን ገለጸ፣ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በሕወሓት/ኢህአዲግ የጭቆና በትር ሲቀጠቀጡ ምዕራባዊያኖች ችላ ማለታቸው አሳፋሪ ነው ተባለ፣የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን ኢትዮጵያውያን በሼህ አላሙዲን ላይ ድል በመቀዳጀታቸው አመሰገነ፣ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ስደተኞ ፈርንሳይ ውስጥ የተካረረ የቡድን ግጭት አደረጉ፣ከቤንሻንጉል ከአራት ዓመት በፊት የተፈናቀሉ የአማራ ገበሬዎችን ጨምሮ በባህር ዳርና በጎንደር አመጽ አስነሱ በሚል በሀሰተኛ የሽብር ክስ ተከሰሱ፣ኢትዮጵያዊው ባለሀብት የህዋት ባለስልጣናት ሕዝቤን እንዳልረዳ እንቅፋት ሆኑብኝ ይላሉ እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ሰኔ 25 ቀን 2009 ፕሮግራም <…ሕወሃት አስቀድሞ በማስተር ፕላኑ ማስፋፊያ ስም ኦሮሞን መሬት ለመዝረፍ ያወጣውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ያወጣው አንዱን ከአንዱ ለማጋቸት ሆን ብሎ ያቀደበት የኦሮሞ ልዩ ጥቅም …

Read More

Hiber Radio: የሳውዲ አረቢያ የምህረት አዋጅ ተጠናቋል ከዚያስ? ስለ ኢትዮጵያኑ ዕታ ፈንታ ነብዩ ሲራክ ይተነትናል ያድምጡት

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 …

Read More

Hiber Radio: የሕወሃት -ኢህአዲግ አገዛዝ የመከላከያ ጦሩን ኤርትራን እና ጅቡቲን ወደ አወዛገበው ኮረብታ አጓጓዘ፣ፈረንሳይ ተዋጊ አውሮፕላኖቿን ለቅኝት አሰማርታለች፣ኢትዩጵያዊያን ሙስሊሞች የታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓልን በጸሎት እና በምስጋና አከበሩ፣በልማት ስም እንዲፈርስ ከተደረገው እውቁ የነጻነት ታጋይ የፕ/ር አስራት ወ/የስ መቃብር የወጣ አጽማቸው በክብር በስላሴ አረፈ፣በሳውዲ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የምህረት አዋጁ እንዲራዘም ወገኖቻቸው ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቀ፣የእንግሊዟ ጠ/ሚ/ር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መለቀቅ ጉዳይ ጣልቃ እንዲገቡ ዳግም ተጠየቁ፣የኢትቪው ጋዜጠኛ ሙስናን በመዋጋ ቱ ባለስልጣኑ ሽጉጥ እንደመዘዙበት ገለጸ፣አትሌት ገለቴ ቡርቃ ከለንደን ሻምፖዮና ቡድን አላግባብ መገለል ፣በአዲስ አበባ የጠፋው ኮንደሚኒየም በኢዲት ጉዳዩ እንዲጣራ ታዘዘ እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ሰኔ 18 ቀን 2009 ፕሮግራም <…በአሰሪዎቼ ከሚደርስብኝ ስቃይ አንጻር ኤምባሲ ደውዬ ምን ላድርግ ስል ምንም ሳትይዢ እጅሽን ለፖሊስ ስጪ አሉኝ እጄን ለፖሊስ ሰጠሁ ።ድረሱልኝ ብዬ ይሄው አስር ወር …

Read More