Hiber Radio: ኢትዮጵያ የአሰብ እና የ ምጽዋ ወደብን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማጓጓዣ እንድትጠቀም ጥሪ ቀረበላት፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ የቃላት ጨዋታውን ትቶ በኦሮሚያ የሕዝቡን ሰላማዊ ጥያቄ ተከትሎ የገደሉትን ለፍርድ እንዲያቀርብ የታሰሩትን እንዲፈታ ጠየቁ፣ተቃዋሚዎች ተባብረው መቆም ያለባቸው ወሳኝ ወቅት መሆኑን ገለጹ፣በኦሮሚያ ተቃውሞው ቀጥሏል፣ በመላው ዓለም በሚደረጉ ሰልፎች የአገዛዙ አፈና ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ቀረበ፣በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚማቅቀው “የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሄት አዘጋጅ የእስራት ቅጣት ተበየነበት፣በመርካቶ በርካታ ሱቆች ሕገ ወጥ ሞባይልና ዕቃ አስገብታችሁዋል በሚል በዘመቻ ታሸጉ፣በኦጋዴን ውስጥ በኢሕአዲግ፣ በቻይና እና በጅቡቲ መካከል የተፈረመው ግዙፍ የነዳጅ ፕሮጀክት ከአካባቢው ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፣መንግስታቱ ከኦጋዴን ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ተጠይቋል እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር መረራ ጉዲና፣ከአክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስና ኦባንግ ሜቶ ጋር፣በአፍሪካዎ የሰብኣዊ ፍርድ ቤት መንግስት ላይ 150 ሺህ ዶላር እንዲቀጣ ስላስፈረደችው ተበዳይ ኢትዮጵያዊቷ ወይንሸት ዘበነ ልዩ ጥንቅርና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 4 ቀን 2008 ፕሮግራም <…አሁን መንግስት የያዘው የሰራውን ሰርቶ መልሶ ስህተቱ ይሻሻላል የሚል በተለይ ፕሬዝዳንት ኦባማ መጥተው ከሄዱ በሁዋላ የያዙት ፈሊጥ ነው። አሁን እግዜርም ቢመጣ ሕዝቡ ኢህአዴግን …

Read More

Hiber radio: መንግስት አገሪቱን እየመራ ነው ማለት እንደማይቻል ተገለጸ፣ሕዝቡ ተቃውሞውን አስተባብሮ ዳር የሚያደርስ መሪ ማጣቱ ተገለጸ፣በወልቃይት ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ካላቆመ ሁኔታው ወደ አደገኛ አቅጣጫ ሊቀየር ይችላል ተብሏል፣ግብጾች በአባይ ጉዳይ ዛሬም ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ተገለጸ፣ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በኦሮሚያ ለተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ የሀይል አማራጭና በኦህዴድ ላይ የተያዘው ሹም ሽር ውጤት እንደማያመጣ ገለጹ፣በአዲስ አበባ በሆስኒ ሙባረክ ላይ ግድያ ያሴሩት የሱዳኑ አል ቱራቢ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ድሪም ላይነር አውሮፕላን አዲስ አበባ ላይ እንግዳ የሆነ ሰው ሰራሽ ችግር ገጠመው፣ሱዳን ወደ ኤርትራ ታፍነው የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን ታጋቾችን ለማስለቀቅ የገላጋይነት ሚና መጫወቷ ተነገረ፣ ፓርላማው አጠገብ የሚገኘው በፌዴራል ፖሊስ ጠዋት ማታ የሚጠበቀው የፌዴሬሽን ም/ቤት መጋዘን መዘረፍ አነጋጋሪ ሆነ እና ቃለመጠይቅ ከጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው፣ልዩ ዘገባ አበረታች ዕጽ ወስደዋል በተባሉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና አስተዛዛቢው የአሜሪካ አቋም ከአጼ ሀይለስላሴ እሰከ ወያኔ፣ከኢትዮጵያ አንድነት እስከ ኤርትራ መገንጠል እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ የካቲት 27 ቀን 2008 ፕሮግራም እንኳን ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ! <በአሁኑ ወቅት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ ስርዓቱ በራሱ ሕገ መንግስት እንኳ የተፈቀደውን አማራ ነን ስላሉ የተፈጸመውን ግፍ …

Read More

Hiber Radio: ኦነግ ወያኔ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ዘር ማጥፋት ለመቃወም የሰራዊቱ አባላትና ሰራተኛውን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ አዲስ ጥሪ አስተላለፈ፣የኤርትራ መንግስት በኦሮሚያ ተቃውሞ እጄ የለበትም የወያኔ ውሸት የተለመደ ነው ሲል መግለጫ አወጣ ፣በአዲስ አበባ የተጠራውን የታክሲዎች አድማ የአገዛዙን ማስፈራሪያ አልፎ ውጤታማ ከሆነ ለውጡን ያፋጥናል ተብሏል፣የእስራኤል መንግስት ከኢትዮጵያ ሊወስዳቸው የነበሩ ቤተ እስራላዊያን ጉዞን አቋጠ፣ የአድዋ ድል በማርች ወር እንዲታወስ የሜሪላንድ ሞንቲጎመሪ ካውንቲ በአዋጅ ወሰነ፣በኦሮሚያ ክልል በተነሳው ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ማለት ሕዝቡን እንደመሳደብ ይቆጠራል ሲሉ ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ገለጹ፣በሱዳን አማላጅነት ወደ ኤርትራ ታፍነው ከተወሰዱት 32ቱ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለጸ፣ፕ/ር መረራ ጉዲና በኦሮሞ ሕዝባዊ እንቀሰቃሴ ጋር የኤርትራ እጅ አለበት በሚለው የአገዛዙ ውንጀላ ዙሪያ ምላሽ ሰጡ፣አንድ ግብጻዊ ቱጃር እና የ ሕዘብ እንደራሴ በሕዳሴው ግድብ ውዝግብ ዙሪያ የ እስራኤልን ጣልቃ ገብነትን መሻታቸውን አስታወቁ፣የሰብኣዊና የሴቶች መብት ተሟጋቿ ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው አረፉ፣ በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በአገሪቱ ህዝብ ዘንድ የተጠላ መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ፣ የአውሮፓ ህብረት ለሰላም አሰከባሪው ጦር የሚላከው የገንዘብ ደጎማን በ20 በመቶ እንደሚቀነስ አስታወቀ እና ቃለ መጠይቅ ከኦነግ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ስለ አዲሱ የግንባሩ ጥሪ፣ስለ አድዋ 120ኛ በዓልና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ የካቲት 20 ቀን 2008 ፕሮግራም እንኳን ለአድዋ ድል 120ኛ ዓመት በዓል አደረሳችሁ! <…ወያኔ እየፈጸመ ያለው ግልጽ የዘር ማጥፋት ነው። ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ ሲያደርግ የነበረውን ነው ዛሬ በይፋ በወታደራዊ …

Read More

Hiber Radio: ኦነግ ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሌሎችም የነጻነቱን ትግል ይቀላቀሉ ሲል ጥሪውን በድጋሚ አቀረበ፣የአዲስ አበባ ጉዳይ በሕዝቡ ወደፊት የሚወሰን ይሆናል ፣ ወያኔ ቢወድቅ አገሪቱ ትበታተናለች የሚለው የስርዓቱ ቅዠት መሆኑን ገለጸ ፣በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሃብ ለመቋቋም የገንዘብና የሎጀስቲክ ችግሮች መከሰታቸው ስጋት ፈጠረ፣ኬኒያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያወዛግባትን ቁልፍ በማዕድን የበለጸገ መሬት በድርድር ለመውሰድ ዘመቻ ጀመረች፣ዶ/ር መረራ ጊዲና የሚመሩት ኦፌኮ ቢሮ በወታደሮች ቁጥጥር ስር ወደቀ በስፍራው የነበሩ ተደብድበው ታሰሩ፣ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው የጥናት ውጤት አይገዛኝም ማለቱዋ ተዘገበ፣የሕወሓት ወታደራዊና የደህነት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማፈን ተጨማሪ ወታደሮች ተሰማርተው አፈናው እንዲቀጥል ወሰኑ፣የተቃውሞው አመራሮች ጊዜው ሲደርስ ራሳቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ተገለጸ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች ቃለ መጠይቅ ከኦነግ የድርጅትና ፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ እና ከታሪክ ተራኪው ኤድዋርዶ ጋር ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ የካቲት 13 ቀን 2008 ፕሮግራም <…የኦሮሞ ወጣቶች ትግል ከወያኔ ጋር እንጂ ከማንም ጋር አይደለም ።የወያኔ የጭካኔ እርምጃ መንፈራገጥ ካልሆነ ትግሉን የሚያቆም አይደለም ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል…ትግሉ ሁሉም …

Read More

Hiber radio: በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆች አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም በአገር ቤት ያሉት ወኪሎች የእኛም ተወካዮች ናቸው ሲሉ ወሰኑ፣ በሕወሓት ኢህአዴግ አገዛዝ በአንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሪፖርት ብቻ ከ7ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ ተገድለዋል፣የባለስልጣናቱ ለዓለም ዓቀፉ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት አለመቅረብ ጠንካራ ስራ አለመሰራቱ ውጤት ጭምር ነው ተባለ፣ኬኒያ ባለሃብቶቼ መሬት ለመቀራመት ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱብኝ ነው አለች፣ በኢጣሊያው የላምባዱሳ ደሴት አቅራቢያ ለሞቱ ወገኖቻችን ተጠያቂዎች የሆኑ 6 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፣ሰሞኑን በጋምቤላ ለደረሰው የጎሳዋች ግጭት ” እጃችን የለብትም” ሲሉ የ ደ/ሱዳን ባለሰልጣናት አስተባበሉ፣ዶ/ር ሊክ ማቻር ለኢትዮጵያ አደገኛ መሆናቸው ተገለጸ፣የኢትዮጵያ፣የግብጽ እና የሱዳን መሪዎች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ግብጽ ውስጥ ሊመክሩ ነው እና ቃለ መጠይቅ ከኢትዮጵያዊው የሰብኣዊ መብት ተማጋችና ባለሙያ አቶ ያሬድ ሀይለማርያም ጋር፣በኡጋንዳ ምርጫ ላይ የተጠናከረ ዘገባና ሌሎችም

             የህብር ሬዲዮ የካቲት 6 ቀን 2008 ፕሮግራም <…በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ ባለስልጣናት በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃንን አስጨፍጭፈው በዓለም አቀፉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት አንድም ባለስልጣን ያለመቅረቡ የዓለም ዓቀፉ …

Read More

Hiber Radio: ኬኒያ ከኢትዮጵያ የመብራት ሃይል በርካሽ ለመግዛት በጥድፊያ ላይ ነኝ አለች፣በጋምቤላ ውስጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው ግድያ በገለልተኛ ወገኖች እንዲጣራ ተጠየቀ፣ ሳውዲ አረቢያ 47 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሯን ገለጸች፣በኢትዮጵያ ወያኔ ስልጣን ላይ እስካለ በሕዝቡ መካከል የጎሳና የሀይማኖት ግጭት እንዳይከሰት አስቀድሞ የጥንቃቄ ስራ እንዲሰራ ጥሪ ቀረበ፣ የታላቁ ሰማዕት አርበኛና የሐይማኖት አባት አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት ወደ ቦታው መመለስ የሕዝቡ የተቃውሞ ውጤት መሆኑ ተገለጸ፣ የዚካ ቫይረስ ያሰጋቸው የአሜሪካ ባለሰልጣናት ወንዶች ኮንዶም አሊያም መታቀብን እንዲከተሉ አሰጠነቀቁ እና ቃለ መጠይቅ ከአቶ ኦባንግ ሜቶና ከሐጂ ነጂብ መሐመድ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ ጥር 29 ቀን 2008 ፕሮግራም <…በጋምቤላ ሰሞኑን የተከሰተው የጎሳ ግጭት ከዚህ በፊት በተለያዩ መንገዶች በሌሎችም አካባቢዎች ተከስቷል። ይሄ አይነቱ የጥላቻ እርስ በእርስ የመጋጨት ሁኔታ የመጣው ይሄ ስርዓት ከመጣ …

Read More

Hiber radio: ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ትግሉ አገር ቤት መግባቱንና እሳቸውም ከትግሉ እንደማይርቁ ገለጹ፣ ግንባሩ የኢትዮጵያን ህልውና ከሚቀበሉ ሀይሎች ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል፣በጋምቤላ ክልል በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት የበርካት ሰዎች ሕይወት እየጠፋ ነው ቤት ንብረት ወድሟል፣ ምዕራባዊያን ዲፕሎማቶች ዜጎቻቸው ወደ ስፍራው እንዳይጓዙ ጥብቅ ማስጠቀቂያ ማስተላለፋቸው ተገለጸ፣ በጋምቤላ የተከሰተው የጎሳ ግጭት ሳይሆን አገዛዙ የሚያካሂደው የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑ ተገለጸ፣ የሱዳን ከፍተኛ ባለሰልጣናት አወዛጋቢው የኢትዮ- ሱዳን ድንበርን መጎብኘታቸው ታወቀ፣የተመድ ዋና ጸሐፊ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያንነ ሕዝባን እንዲታደጋት አዲስ አበባ ላይ ጥሪ አቀረቡ የሚሉና ቃለ መጠይቅ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለተገኙበት የዲሲ ስብሰባ፣በአገር ቤት ትኩረት ስላላገኘው አሳሳቢ የረሃብ አደጋ፣በጋምቤላ ወቅታዊ የዘር ማጥፋት እርምጃ ለይ እንዲሁም ስለ ዚካ ቫይረስ ወቅታዊ ዘገባ እና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ ጥር 22 ቀን 2008 ፕሮግራም <…የአርበኞች ግንቦት ሰባት ትግል የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ታልቅ ስብሰባ ነው። ፕ/ር ብርሃኑ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ወታደሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው ትግሉ አገር ቤት …

Read More

Hiber Radio: አወዛጋቢውን የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር በዚህ ወር እንዲያካልሉ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መመሪያ ተሰጠ፣በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ሕዝቡ ጥያቄ ስላልተመለሰ ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል፣የአቶ አንዳረጋቸው ጽጌ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አንድ ታዋቂ እንግሊዛዊ የጤና ባለሙያ አሳሰቡ፣በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ረሃብ የዓለማ አቀፉ የግብርና ተቋምን በእጅጉ አሳስቦታል፣ በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ባልታወቀ ሁኔታ የሞተው ወጣት ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ፣አገዛዙ ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት አዲስ ዶክመንተሪ ፊልም አውጥቶ የሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከሽብር ጋር አመሳሰለ፣ አልሽባብ በኢትዮ ኬነያ ድንበር ላይ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን እና መማረኩን ገለጸ እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር መረራ ጉዲና ፣ ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር እና ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ ጥር 8 ቀን 2008 ፕሮግራም <…አዲሱ የፈጠራ ፊልምን ዶክመንተሪ አልለውም ሙስሊሙና ክርስቲያኑን ለማጋጨት ብለው በከንቱ የደከሙበት ነው …የኢትዮጵያ ሙስሊምና ክርስቲያን ከሃያ አምስት ዓመቱ የወያኔ ስልጣን በፊት ለረጅም ዘመን …

Read More

Hiber Radio: ኢትዮጵያዊው ግለሰብ የሰው ስጋ በመብላት ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ

(በታምሩ ገዳ) አንድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የታመነ ግለሰብ እራሷን ከሶማሊያ ገንጥላ ሶማሊላንድ ብላ በምትጠራው ግዛት ውስጥ “የሰው ስጋ በመብላት “ ወንጀል ተጠርጥሮ ሰሞኑን በቁጥጥር ሰር መዋሉን የአካባቢው የፖሊስ ሹም ለዜና …

Read More