Hiber Radio ፡ ስምንት ሺህ የሰራዊቱ አባላት በአንድ ዓመት ብቻ በአገዛዙ ዘረኛ አመራር ተማረው ከሰራዊቱ ከድተዋል፣በአመራሩ ላይ እርምጃ የወሰዱ ወታደሮች አሉ፣ሰራዊቱና ሕዝቡ በአንድ ላይ ሲቆሙ ጠመንጃው ወደ ዘረኛው ስርዓት መሪዎች ላይ ይዞራል፣ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷን አንገቷን ቀልታ መግደሏ ይፋ ሆነ፣የመን የሴት ቀሚስ ያጠለቁ አራት ኢትዮጵያውያን ወንዶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉዋን ገለጸች፣ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከይሮ ላይ ኢትዮጵያን ያገለለ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፣ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ የቀረበላትን ማሻሻያ ሀሳብ ውድቅ አደረገች፣ዶ/ር መረራና ኢ/ር ይልቃል በጋራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተው ለሕዝቡ ጥሪ አቀረቡ፣ ቃለ መጠይቅ ከኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣ከአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ሌሎችም አሉን

             የህብር ሬዲዮ ጥር 1 ቀን 2008 ፕሮግራም  <…በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ በአገር ቤትና በውጭ የተደረገው የጋራ ውይይት ላይ ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በጋራ …

Read More

Hiber radio: የኢትዮጵያው አገዛዝ በአወዛጋቢው በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይቀሰቀስበት ስጋት እንዳለው የግብጽ ሚዲያዎች አጋለጡ ፣በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞው እንደገና ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው፣በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ተሰቅሎ ተገኘ፣አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሽብር ጥቃቱን ቀጥሏልቀጥሏል፣የንጹሃን ሞት ጨምሯል፣የእርዳታ እህልና ዘይት በባለስልጣናት ተዘርፎ እየተሸጠ ነው፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚ/ር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገውን የሰው አልባ አውሮፕላኖች የጸረ ሽብር ዘመቻውን ማቋረጡን አስታወቀ፣ ከኢትዮጵያ የሄዱ የደህነት አባላት የኬኒያ ድንበርን ተሻግረው የአፈና እና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ አድርሰዋል ስትል ናይሮቢ ወቀሳዋን አሰማች እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራና ከሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 24 ቀን 2008 ፕሮግራም እንኳን ለአዲሱ ዓመትና ለኢትዮጵያውያን የገና ዋዜማ አደረሳችሁ! <በረሀብ ሳቢያ ችግር ውስጥ ላለው ወገናችን መድረስ አለብን። ከሕዝቡ የሚዋጣውን ገንዘብ በቀጥታ የረሃብ አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖቻችን …

Read More

Hiber radio: ፕ/ር መረራ ጉዲና ኢሕ አዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ፣ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የአገዛዙ አጋዚ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ገብተው የሚያደርሱባቸውን ጥቃት በመቃወም ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄዱ፣ሴት ተማሪዎች መደፈራቸው ተገለጸ፣ ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች፣ሸንጎ የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የድንበሩን ጉዳይ ጨምሮ ያቀረቡትን የተምታታ ሪፖርት አጣጣለ ፣አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ፣የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እና ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የአገዛዙ ፍርድ ቤት 28 ቀን ፈቀደ፣ ዛሬ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለመወያየት ወደ ካርቱም የተጓዙት የኢትዮጵያ ልዑካኖች ከሰብሰባው ቦታ አርፍደው ደረሱ እና ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር እና ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 17 ቀን 2008 ፕሮግራም <…አቶ ሀይለማሪያም የሚሉት የሚታመን ቢሆን ኖሮ ድንበር ለሱዳን አይሰጥም ነበር። ይሄን ስርዓት ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት አይተነዋል ።የማይታመን የአገሪቱን ጥቅም አሳልፎ የሚሸት ነው። …

Read More

Hiber radio: ኦነግ የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄ የማይመልስ ከወያኔ ጋር የሚደረግ የጓዳ ድርድር ጥያቄ እንደማይቀበል ገለጸ ፣ሕዝቡ በወያኔ ሴራ ሳይከፋፈል ለነጻነቱ በጋራ መቆሙምን እንዲቀጥል ጠየቀ፣አና ጎሜዝ የወያኔ ባለስልጣናት ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋርና ከግንቦት ሰባት መሪዎች ጋር እንዳስታርቃቸው ጠይቀውኝ ነበር ሲሉ ገለጹ ፣በኦሮሚያ ክልል በርካታ ንጹሃን የተገደሉበትን ጭፍጨፋ የአገዛዙ ሸሪኮችን ጭምር አስቆጣ፣ሐርማን ኮህን አገዛዙ በሰላማዊ በዜጎች ላይ እየወሰደ ያለውን የጭካኔ እርምጃ ተቃወሙ፣ሰሞኑን በጎንደር የመከላከያ ሰራዊቱ በተቃዋሚው ሕዝብ ላይ ጦርነት የገጠመው ከግብጽ ሰራዊት ጋር ተዋጉ በሚል ማታለያ መሆኑን ቁስለኛ ወታደር ገለጸ፣በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ተቃውሞውን በተመሳሳይ ሰዓት በመጮህ እንዲገልጽ ተጠየቀ፣ የሰራዊቱ አባላት ድንበር ጠብቁ ብላችሁ ቤተሰቦቻችንን ትገላላችሁ ሉ መጠየቃቸው ተነገረ፣ ታፍነው የተወሰዱ አሉ ተባለ እና ቃለ መጠይቅ ከኦነግ ቃል አቀባይ ቃሲም አባነሻ ጋር እንዲሁም በታክሲ ሊዝ ጉዳይ ከቺጋጎ ኢትዮጵያዊው የታክሲ ኩባንያ ባለቤት ጋር እነ ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 10 ቀን 2008 ፕሮግራም <…የሕዝቡ የጋራ ጠላት እርስ በእርሱ በጎሳ በሀይማኖት ከፋፍሎ ሊአጋድለው የሚሰራው ወያኔ እንጂ ይሄ ህዝብ ትላንትም በሰላም አብሮ ኖሯል ነገም በሰላም አብሮ ይኖራል።ወያኔ እንደፈለገው …

Read More

Hiber Radio: በሕዝባችን ላይ አንተኩስም ያሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ኮሎኔሎች ከሰራዊቱ ውስጥ መታሰር መጀመራቸው ተገለጸ፣ አንድ የካናዳ ኩባንያ ኢትዮጵያን እና ግብጽን በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሊሸመግል ነው ተባለ፣የሱዳኑ ፕ/ት አልባሽር ካይሮን እና አ/አበባን ለመዳኘት መሬት ይሰጠኝ ማለታቸው ተሰማ፣ በ ታላቁ አንዋር መሰጊድ የደረሰው የቦንብ አደጋ አነጋጋሪ ሆኗል፣ እንግሊዝ ዜጎቿ ወደ መርካቶ እና መሰል ስፍራዎች እንዳይሔዱ አሰጠነቀቀች፣የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባለቤት የእንግሊዝ የው/ጉ/ሚ/ርን ለመጀመሪያ ጊዜ በግንባር አነጋገሩ፣ሳውዲ አረቢያ አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን ወደግዛቷ ዳግም ለማስገባት ሕዘበ ውሳኔ ልታካሄድ ነው ፣የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄ የአገዛዙን ዘረኛ እንቅስቃሴ በመቃወም በጎንደር ወታደራዊ ጥቃት ፈጸምኩ አለ፣ሰማያዊ ፓርቲ በኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን ግፍ ተቃውሞ አጋርነቱን ገለጸ፣ከመድረክና ከሌሎቹም ጋር ለመስራት ወሰነ፣ ቃለ መጠይቅ ከጃዋር መሐመድና ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር በወቅታዊ የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና ትግሉ ወደ ብሄራዊ ተቃውሞ ስለሚያድግበት ሁኔታ ሌሎችም ወቅታዊ ዝግጅቶች አሉን

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-121315-122015 የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 3 ቀን 2008 ፕሮግራም <…የህወሃት አገዛዝ አንዱን ብሄር ከሌላው ጋር ለማጋጨት ባለፉት በተማሪዎች ተቃውሞዎች የሄደበት ሴራ ዛሬ ከሽፏል፣ተማሪዎቹ አስቀድመው ስትራቴጂ አውጥተዋል።ይሄ የተለመደ የማጋጨት ስልትን እንኳን ሰው …

Read More

Hiber radio: የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱት የሀይል እርምጃ ዓለም አቀፍ ውግዘት ገጠመው፣በአዲስ አበባ መሬት ዝርፊያ ስማቸው በቀዳሚነት የሚነሳው ወ/ሮ አዜብ መስፍን የማስተር ፕላኑን በመቃወም የተገደሉ ተማሪዎችን ጉዳይ አናናቁ ፣ዕቅዱን ጀምረነዋል እንጨርሰዋለን ሲሉ ዝተዋል፣ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር ይራዘምልኝ ስትል ጠየቀች፣ኢትዮ-ኬኒያ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የጸጥታ እና ውጥረት የማብረድ ስራ ሊሰሩ መሆናቸውን አሳወቁ፣አገዛዙ በኦሮሚያ በማስተር ፕላን ስም የጀመረው የመብት ረገጣ የድርቁን አደጋ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ሕዝቡን ለመከፋፈል ሊጠቀምበት እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ ፣ ቃለ መጠይቅ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ እና ከፓርቲው ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሰብሳቢ አቶ ነጌሳ ኦዶ ጋር በወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና የተወሰደው የግፍ እርምጃ ላይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ  ህዳር 26 ቀን 2008 ፕሮግራም  <…የተማሪዎቹ ጥያቄ የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው።የመብት ጥያቄ ነው። ተማሪዎቹ ቤተሰቦቻቸው ሲቸገሩ ሲፈናቀሉ ከመሬታቸው ሲነሱና ሲቸገሩ ያዩ ናቸው።ብሶት ነው ያስነሳቸው።በምንም መንገድ በዚህ አካባቢ ሌላው አይኑር …

Read More

Hiber Radio: የሱዳን ዲፕሎማት አወዛጋቢው መሬት ቀድሞም የኢትዮጵያ ሳይሆን እኛ የሰጠናችሁ ነው ሲሉ ተናገሩ ፣የአማራ ክልል ባለስልጣናት ታጣቂዎችን እያደራጁ አስወጉን ሲሉ አወገዙ፣ የአባይ ወንዝን በተናጠል መገንባት እና መጠቀም ጦር ሊያማዝዝ ይችላል ተባለ፣በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅና ረሃብ አገሪቱንና ሕዝቧን እየተፈታተነ መሆኑ ተነገረ፣የጋሞ ብሄርን የሚያንቋሽሽ መጽሐፍ መውጣቱን ከተቃወሙ ውስጥ ዋና ዋና አስተባባሪ የተባሉት 69 ሰዎች በግንቦት ሰባት ስም ተወንጅለው መታሰራቸው ተገለጸ፣የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አውሮፓ ፓርላማ ድርቁን አስመልክቶ ለንግግር መጋበዝ ምዕራባውያን ለሚደረገው የትጥቅ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ያሳያል ተባለ ፣ በአገር ቤት በበጎ ፈቃደኞች በረሃቡ የተጎዱትን ለማገዝ የተቋቋመው <ቤዛ እንሁን> ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፣በመምህር ግርማ ጉዳይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ ህዳር 19 ቀን 2008 ፕሮግራም <…በረሃቡ ሳቢያ ለተጎዳው ወገን ቅድሚያ መድረስ አለብን ገና ለገና መንግስት ገንዘብ ይበላል ተብሎ ሰው ለቤተሰቡ ሳይልክ አይቀርም ።ለነዚህ ወገኖቻችንም በአፋጣኝ መድረስ አለብን።ለተራበ ሰው …

Read More

Hiber Radio ፡ በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እጁ ያለበት ያሸባሪዎች መሪ አሜሪካ በወሰደችው ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለጸ፣ በኢትዮጵያ የተከሰተውን አስፈሪ የረሃብ አደጋን ስፋት አገዛዙ ለመደበቅ መሞከሩ ተዘገበ፣ የኢትዮ-ኬኒያ ድንበር ወታደራዊ ውጥረት አይሏል፣ኢትዮጵያ የድንበር ኬላዎቿን ዘጋች፣ 3 የኢትዮጵያ 4 የኬኒያ ወታደሮች መሞታቸውን የኬኒያ ጋዜጣ ዘገበ፣የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህመም ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑና ዛሬም ሕክምና እንዳልተፈቀደለት ተገለጸ፣በቬጋስ የሁበርና ሊፍትን ተወዳዳሪነት ለማርገብ በርካታ አዲስ ታክሲ ለኩባንያዎች ተጨመረ እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር ኑሩ ደደፎ የኦነግ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ጋር እና ሁበር ሲያሽከረክር ጥቃት ከደረሰበት ኢትዮጵያዊ ጋር ውይይት እንዲሁም ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ ህዳር 12 ቀን 2008 ፕሮግራም <…ወያኔ በጉልበት ያለፈው ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ የሞከረውንና ያልተሳካለትን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ዛሬ በህግ ስም የኦሮሚያ ከተሞች አስተዳደር ሕግ በሚል የኦሮሚያ ም/ቤት እንዲያወጣ …

Read More

Hiber Radio : በደቡብ ክልል በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ለአባይ ቦንድ አንከፍልም ሲሉ ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል አስራ አምስቱ ታሰሩ፣በተቃውሞው ሳቢያ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የኤርትራዊያን ስደት እንዲገታ ከተፈለገ የአስመራ መንግስት መወገድ አለበት ማለታቸው ቁጣ ቀሰቀሰ፣በተመድ የኤርትራ አመባሳደር ግርማ አሰመሮም <<የራሷ አሮባት>> ሲሉ የአቶ ሀይለማሪአምን ንግግር ማታታላቸው፣ በጎንደር ልዩ ልዩ አካባቢዎች ከአከላለል ጋር በተነሳ ግጭት የገበሬ ጦር ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር ውጊያ መግጠሙ፣ሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ታጣቂ ተቃዋሚዎችን እየረዳች መሆኗ ተዘገበ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የአለም ባንክ አሰተርጓሚ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠየቀ ፣ስደተኛው ሲኖዶስ በአገር ቤት ያለው አገዛዝ ተቃዋሚዎችን <<አሸባሪ>> የሀይማኖት አባቶችንና ሰባኪያንን <<ተሃድሶ>> የሚል ስም እየለጠፈ የሚያደርገውን ውንጀላ አወገዘ፣ ዘጠኝ ተጨማሪ ጳጳሳት ሊሾም ነው ፣በመምህር ግርማ ዙሪያ ወቅታዊ ዘገባ፣የአርበኞች ግንቦት ሰባት የፊኒክስ- አሪዞና ስብሰባና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ጥቅምት 28 ቀን 2008 ፕሮግራም <…የአቶ ሀይለማርያም ንግግር ከልብ ለውጥ ለማምጣት ነው ወይስ ዲስኩር ብቻ የሚለውን መመርመር ያሻል።ከልብ ለማድረግ የመፈለግ ምስል ሰጥቶ ለሰው፣ ሰው ያንን ይዞ ተስፋ እያደረገ …

Read More