Hiber Radio: በሬቻ በዓል ላይ በሕወሓት ታጣቂዎች የተጨፈጨፉት ንጹሃን ቁጥር ከመቶ በላይ ሊያሻቅብ ይችላል ተባለ፣ግድያውን ተከትሎ የአምስት ቀን ብሄራዊ የሐዘን ቀን ጥሪ ተላልፏል አገር አቀፍ ተቃውሞ ይቀጥላል

ዛሬ በእሬቻ በዓል ላይ በአጋዚ ጥይት ከተጨፈጨፉ ንጹሃኖች የጥቂቱ አስከሬን
ዛሬ በእሬቻ በዓል ላይ በአጋዚ ጥይት ከተጨፈጨፉ ንጹሃኖች የጥቂቱ አስከሬን

(ህብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ)ዛሬ በደብረዘይት በቢሸፍቱ የሚካሄደውን የኦሮሞ ሀይማኖታዊ የእሬቻ በኣልን ለማክበር የተሰባሰቡ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ላይ በሰላማዊ መንገድ <<ወያኔ ይሂድ ወያኔ ይውረድ >> የሚል ተቃውሞ መቅረቡን ተከትሎ በሕወሓት አገዛዝ አጋዚ ታጣቂዎች በተወሰደ የጅምላ ግድያ የሟቾች ቁጥር አስቀድሞ ከተገመተው የሚበልጥና ቢያንስ ከመቶ በላይ ንጹሃን መገደላቸውን አገዛዙ ደህንነቶች አስቀድመው ባደረጉት ዝግጅት ቆሰሉ ሰዎችን ሳይሆን የገደሏቸውን ሬሳ ሲያሹ እንደነበር የአይን እማኖችን የጠቀሱ ህብር ምንጮች ገለጹ።የቆሱትን ሙሉ ለሙሉ ወደ ሆስፒታል ለማጉዋጉዋዝ በቂ አምቡላንስ ባለመኖሩ በችነት መኪና ሳይቀር በየአቅጣጫው ሕዝቡ የቆሰሉ፣የሚያጣጥሩ ወገኖቹን ለማትረፍ ሲሯሯጥ በአንጻሩ የሕወሓት ደህንነቶች ካሜራ የሚያነሳ ሲያሳድዱና ከጥይት የተረፈውን ደብድበው አንዳንዶችን አፍነው ሲወስዱ እንደነበር ጨምረው ገልጸዋል። አስቀድሞ ሃምሳ ያህል ንጹሃን ተገለዋል ሚለው ቁጥር ከተፈጸመው ጭፍጨፋ አንጻር አነስተኛና ቁጥሩ በቀላሉ ከመቶ በላይ እንደሚበልጥ እነዚሁ ምንጮች ጠቅሰዋል።

በአገሪቱ ታሪክ በጠራራ ጸሐይ እንዲህ ያለ ጭፍጨፋ ኣለም እአየ ሲፈጸም ት እንዳለን ለማመን ይከብዳል ሚሉ የአይን እማኞች በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ አማራ ኦሮሞ እና ሌላውም በጋራ በንጹሃን ላይ በዘመቱ ፋሺስቶች ላይ ተባብሮ መነሳት አለበት ሲሉ በቁጭት ገልጸዋል።

ሰላማዊውን መንፈሳዊ በኣል በደም ያጨቀዩት የህወሓት መሪዎች ከአየርና ከምድር በቀጥታ ወደ ሕዝቡ በመተኮስ ከነሱ ዘር ውጭ ሌላው ኢትዮጵአዊ እንደ ሰብኣዊ ፍጡር የማይቆጠር መሆኑን አስመሰከሩበት በርካታ ኣለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን በስፍራው የነበሩበት እንደነበር ገልጸዋል።

ማምሳውን በሚወጡ መረጃዎች የዛሬው ጭፍጨፋ ያስቆጣቸው የአምቦ ነዋሪዎች ማምሳውን ተቃውሞ ጀመሩ ሲሆን በሌሎች አካባቢዎችም መንገድ መዘጋት ተጀምሯል። የኦሮሞ አክቲቪስቶች ግድአውን ተከትሎ አምስት ቀን ብሄራዊ ሀዘን በመላው አገሪቱ እንዲታሰብና ተጨማሪ ተግባራዊ እርምጃዎች በሰኣታት ውስጥ ተግባራዊ ኢሆናሉ ብለዋል።

<<ሕወሓት እየታደስኩ ነው>> በሚል ሰሞኑን ሰፊ ቅስቀሳ ላይ ከረመ ሲሆን ድርጊቱ ፋሺስቶች አስቀድሞም እንደተባለው ፈጽሞ ሊታደሱ እንደማይችሉ በዛሬው የእሬቻ በዓል ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ምስክር መሆኑን ብዙዎች አስተያየታቸውን በተለያዩ መንገዶች በመግለጽ ላይ ናቸው።

በዛሬው የእሬቻ በዓል ላይ የተገኙ ኣለም አቀፍ መገናና ብዙሃን ዘጋቢዎች ያዩትን ጭፍጨፋ እንዲአጋልጡ ካልሆነ አገር ጥለው እንዲወጡ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከወዲሁ ጥሪ በማቅረብ ላይ ናቸው። የህብር ሬዲዮ አዘጋጆች በዚህ አጋጣሚ በወገኖቻችን ላይ በሕወሃት አገዛዝ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ እያወገዝን ስለ ንጹሃኑ ሞት ሐዘናችንን እንገልጻለን።

 

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *