Hiber Radio : በምርጫ 97 ወንድሙ የተገደለበት የሰማዕታቱ መታሰቢያ ሰብሳቢ ታሰረ

november-killing-eyob-kebede

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) ማዕከላዊ ምክር ቤት አባል የሰኔ 1/1997 ዓም ሠማዕታት ሠብሳቢ አቶ ኢዮብ ከበደ ዛሬ ጥቅምት 3/2009 ዓም ተይዞ መታሰሩ ከቤተሰቡ ተረጋግጧል። አቶ ኢዮብ ከበደ በዘመነ ደርግ ታላቅ ወንድሙ የተረሸነ ሲሆን በ1997 ዓመተ ምህረት በዘመነ ወያኔ ታላቅ ወንድሙን አጥቷል ፡፡

ኢዮብ ከበደ አያያዝ እና የፍ/ቤት ውሎ

ኢዮብ የተያዘው ጥቅምት 3/2009 ዓም መርካቶ ምዕራብ ሆቴል አካባቢ የስልክና የመብራት ለመክፈል ከባንክ ብር አውጥቶ ባንኩ አጠገቡ የሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ሊገባ ሲል በር ላይ ነው የተያዘው እንደያዙት ቀጥታ የወሰዱት የድሮው አራተኛ ፓሊስ ጣቢያ ነው አራተኛ ፓሊስ ጣቢያ በመፍረሱ አዲስ ወደ ተመሠረተው ዮሃንስ አካባቢ ወስደውታ አሁንም የሚገኘው እዛው ዮሃንስ ነው እስከ ዛሬ ጥቅምት 06/2009 ዓም ሠው እንዳያነጋግረው በመደረጉ እንዴት እና የት እንደተያዘ አልታወቀም ነበር ትላንትና በ5/2009 ዓም መድሃኒዓለም አካባቢ በሚገኝ ፍርድ ቤት አቅርበውታል የቀረበበት ክስ መርካቶ ምዕራብ ሆቴል አካባቢ ሁከትና አመፅ ሲቀሰቅስ አግኝተነዋል በተጨማሪም በስልኩ ውስጥ አመጽና ሁከት የሚቀሰቅሱ ጽሁፎችን ሲያሰራጭ እንደነበረ ከስልኩ ውስጥ አግኝተናል ብሏል ከሳሽ በተጨማሪም

ጉዳዩ ወቅታዊ እና አሳሳቢ በመሆኑ የ14 ቀን ጊዜ ይሰጠን ብዙ የምናጣራው ጉዳይ አለን ማለታቸውም ታውቋል ፡፡

ኢዮብም በበኩሉ የቀረበብኝ የሀሰት ክስ ነው ልጄ ወድቆ እጁ ተሰብሯል ህክምና እየተከታተለ ነው ሀኪም ቀጠሮ አለው ማመላለስ አለብኝ የዋስትና መብቴ ይጠበቅልኝና ጉዳዩን በውጭ ሆኜ ልከታተል ብሎ አቅርቧል በነገራችን ላይ የኢዮብ የመጀመሪያ ልጅ ወድቆ እጁ ላይ ስብራት ደርሶበት እያሳከመ ነበር ካንጋሮው ፍርድ ቤት የዋስትና መብትህ አልተጠበቀም እስር ቤት ትቆያለህ ብሎታል ፓሊስ ለምርመራ የ14 ቀን ጌዜ ቀጠሮ ቢጠይቅም ዳኛው የ14 ቀን ይበዛል በአጭር ጌዜ ምርመራችሁን ጨርሱ በማለት 3 ቀን ሰጥቷል ፡፡

ማክሰኞ ጥቅምት 8/2009 ዓም ዳግም ይቀርባል ፡፡

 

የኢትዮጵያዉያን ያልተፈታ ህልም:- የአቶ ከበደ ሮቢ ቤተሰብን እንደማሳያ

================================

የኢዮብ አባት አቶ ከበደ ሮቢ ኢትዮጵያን ጠላት በወረረ ጊዜ ገና ታዳጊ ቢሆኑም ከታላላቆቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል ጠላት ጣሊያንን የተዋጉ አርበኛ ነበሩ:: ጠላት ከሀገር ከወጣም ብኋላ በወታደር ሙያ ሀገራቸውን አገልግለዋል:: ከሀገራቸው አልፎም ኮሪያ ድረስ በመዝመት ሌሎች ህዝቦችን ነጻ አውጥተዋል::

ሀገራቸው ኢትዮጵያን ከጠላት ነፃ ያወጡት አባት ዛሬ ለልጆቻቸው የተመቸች ሀገር ማግኘት አልቻሉም:: ደርግ በቀይ ሽብር ዘመን የመጀመሪያ ልጃቸውን ማለትም ጌታቸው ከበደን ነጠቃቸው:: ያንን ሀዘን ይረሱ ዘንድ ፈጣሪ ሌሎች ልጆች ሰጣቸው::ሆንም እንደገና በ1997 ዓም ምርጫ ማግስት የኢዮብን ታላቅ ወንድም ሚሊዮን ከበደን ዳግም ገበሩ::

በቅንጅት ምርጫ ማግስት በህውሃት ቤተሰቦቻቸውን የተነጠቁ ኢትዮጵያዉያን የሰማዕታት ቤተሰብ በ1997 ዓም ሲያቋቁሙ ኢዮብ የሰማዕታት ቤተሰብ ሰብሳቢ ሆኖ ተመረጠ:: የሰማዕታት ቤተሰብን የሚያስተባብረዉ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ስለነበረም ኢዮብ ከመኢአድ አመራሮች ጋር የመተዋወቅ እድል አገኘ:: እናም ኢዮብ ይህንን ገዳይ: ከፋፋይ ስርዓት መታገል እንዳለበት አምኖ የመኢአድ አባል ሆነ::ኢዮብ እስከዛሬ ድረስ ከመኢአድ ሀይላት ጋር በመሰለፍ ይሄዉ በመራራ ትግል ዉስጥ አለ::

አቶ ከበደ ሮቢ እና ባለቤታቸዉ የደረሰባቸውን ሀዘን መቋቋም አልቻሉም እና በሚያሳዝን ሁኔታ ባልም ሚስትም ይህችን ዓለም ለቀዉ ወደ ዘላለማዊ አለም ሄዱ:: ሆኖም ኢትዮጵያ ግፍ በማይፈራ ዘረኛ እና አንባገነን ሀይል ስር ወድቃለች እና ይሄ ወንበዴ ስርዓት ሰሞኑን ደግሞ የመኢአድ አባል በመሆኑ ብቻ እንደገና ኢዮብን ከሁለት ልጆቹ ነጥሎ አሰረው::

ጥያቄዉ የኢዮብ አባት አቶ ከበደ ብዙ የደከሙላት ኢትዮጵያ ለልጆቻቸዉ የምትመች ሳትሆን እሳቸዉንም በብስጭት ከዚህ አለም እንደሸኘቻቸዉ ትዉልዳቸዉንም እያበሳቆለች ትቀጥል ይሆን ? የሚለዉ ነዉ:: እናም ዛሬ ኢዮብ እየደከመላት እና እየታገለላት ያለችዉ ኢትዮጵያ ለልጆቹ እና ለትዉልዱ የምትመች ዲሞክራሲያዊት ሀገር መሆን ትችል ይሆን?

ኢትዮጵያዉያን ተባብረዉ አንዲት ዲሞክራሲያዊት ሀገር: ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የምትመች እና ሁል አቀፍ ብልጽግና የሰፈነባት ሀገርን መመስረት ይችሉ ይሆን?

በአቶ ከበደ ሮቢ የቤተሰብ ሂደት ዉስጥ የሚገኘዉ አንድ እዉነት የኢትዮጵያዉያን ያልተፈታ ህልም ነዉ::

ለገሰ ወልደሃና በገጹ ካሰፈረው የተወሰደ

 ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *