Hiber Radio: ሰበር ዜና -አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፓርላማ አባላቱን ሕጋዊ ድምጽ ባለማግኘቱ የተጭበረበረ ቁጥር ይፋ ሆነ <<አዋጁ በ346 ድምጽ በ88 ተቃውሞና በ7 ተአቅቦ ጸድቋል...>> አፈጉባዔ አባዱላ ገመዳ፣<<.አዋጁ በም/ቤቱ ከተገኙት 490 አባላት በ395 ድጋፍ በ88 ተቃውሞ በ 7 ድምጸ ተአቅቦ ጸድቋል..>> የሕወሓት ልሳን ፋና ሬዲዮ አዋጁ ሕጋዊ ለመሆን ከ547 አባላት 2/3ተኛ የ365 አባላት ድጋፍ ያስፈልገው ነበር አልተገኘም

ሕወሓት ሙሉ ለሙሉ በተቆጣጠረው ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ በምክር ቤቱ ከተገኙ 441ሲሆን ቀደም ብሎ ሆን ተብሎ 490 አባላት ተገኙ የተባለው ሀሰት መሆኑን ስብሰባውን የተከታተሉ የውጭ አገር ጋዜጠኞች ጭምር አጋለጡ። በስብሰባው ከተገኙት አባላት መካከል በ346 ድጋፍ፣ በ88 ተቃውሞ እና በ7 ድምጸ ታአቅቦ ፀድቁዋል። አዋጁ ለመጽደቅ ከ547 የም/ቤቱ አባላት መካከል 2/3ተኛ ድምጽ ማግኘት እንዳለበት ሕገ መንግስቱ የሚደነግግ ሲሆን አስአኳይ ጊዜ አዋጁ ለመጽደቅ የሚአስፈልገውን 365 ድምጽ ባለማግኘቱ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ በይፋ በም/ቤቱ ይፋ ያደረጉትን ቁጥር ወደ ጎን በማድረግ የአገዛዙ መገኛኛ ብዙሃን አዋጁን ሕጋዊ ለማስመሰል ያወጡት ቁጥር ተጋለጠ።

በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 93 ንኡስ አንቀጽ 2 እንደሚደነግገው <<..የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሁለት ሶስተኛ ድምጽ ተቀባይነት ካላገኘ ወዲአውኑ ይሳራል>> በሚለው ድንጋጌ መሰረት አዋጁ ሕገ ወጥ ሲሆን ይህን ለመከላከል በም/ቤቱ ያልተገኙ አባላትን ቁጥር ይፋ በማድረግ ሕጋዊ ለማስመሰል የተሞከረው ሙከራ ፋና 490 አባላት ተገኙ ሲል 346 ደገፉ የሚለውን ደጋግመው ኤዲት አድርገው ተጋልጠዋል።

በፓርላማው የፌስ ቡክ ገጽም ዋናው ቁጥር 346 ድጋፍ ከወታ በሁዋላ ተመልሶ ተደጋግሞ ኤዲት ተደርጎ ተጋልጠዋል።

ቄሮን ጨምሮ የአፈና አዋጁን ከሕውሓት ውጭ ያሉ አባላት በተቃውሞ እንዳያፀድቁ ማስጠንቃቸው ይታወሳል።አዋጁ 2/3ተኛ ድምፅ ማግኘት ባለመቻሉ በሕገወጥ መንገድ ማለፋ ታውቁዋል።ለዚህም በም/ቤት የተገኙ አባላት ቁጥር በአገዛዙ መገናኛ ብዙሀን የተለያየ መረጃ ወጥቱዋል።

የህብር ሬድዮ/ዘሐበሻ ምንጮቻችንን ጠቅሰን ባለፈው እሁድ የፓርላማ አባላቱን ማስፈራራት መጀመሩን መዘገባችን ይታወሳል።

 Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *