“በአሽባሪነት ተጠርጥሮ “የታሰረው ታዳጊ የፕ/ት ኦባማ ልዩ እንግዳ ሆኖ ተጋበዘ፣ “ልጄ በት/ቤት ጓደኞቹ ፊት በካቴና በመታስሩ በጣም አዝኛለሁ” ወላጅ አባት

Irving MacArthur High School student Ahmed Mohamed, 14, poses for a photo at his home in Irving, Texas on Tuesday, Sept.  15, 2015. Mohamed was arrested and interrogated by Irving Police officers on Monday after bringing a homemade clock to school. Police don't believe the device is dangerous, but say it could be mistaken for a fake explosive. He was suspended from school for three days, but he has not been charged. (Vernon Bryant/The Dallas Morning News via AP) MANDATORY CREDIT; MAGS OUT; TV OUT; INTERNET USE BY AP MEMBERS ONLY; NO SALES

(በታምሩ ገዳ)

የ 14 አመቱ አህመድ መሃመድ ገና ታዳጊ፣ የሙስሊም እምነት ተከታይ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በ እርሱ እድሜ ሊሰሩ አይደለም ሊታሰቡ የማይሞከሩትን የኢሌክትሮኒክስ ቁሶችን መገጣጠም የእለት ተገባራቱ ናቸው ። ታዲያ ይህ በአሜሪካው የቴክሳሱ ግዛት በኢቪርንግ ከተማ የ ማክአርቱር ከፍተኛ ደረጃ የመጀመሪያ አመት ትምህርቱን ሰሞኑን የጀመረው ታዳጊው አህመድ ባለፈው ሰኞ ወደ ት/ቤቱ አንድ እንግዳ ነገር ይዞ ጎራ ሲል ያለጠበቀው እና ያልገመተው ችግር ይገጥመዋል።አህመድ ከፈጠራ ሰራዎቹ መካከል አንዱ የሆነው የማንቂያ ሰአት ለመምህሩ ለማሳየት እና ችሎታውን ለማሰመረቅ ቢሞክርም መምህርቱ የአህመድ እቃ ሰአት ሳይሆን “ቦምብ ይመሰላል” ከሚል ጥርጣሪ ላይ በመወደቃቸው ፖሊስ ተጠርቶ አህመድም አጁ በካቲና ታስሮ በቁጥጥር ሰር ይውላል።

ከ ሱዳን ተሰደው በ አሜሪካ ከ 30 አመት በላይ የኖሩት ወላጅ አባቱ መሃመድ ኢል ሁሰን መሃመድ በልጃቸው ላይ የደርሰው የሰበኣዊ መብት ረገጣን በማሰመልከት ሲናገሩ “ ልጄ ያለበቂ ምክንያት በተማሪዎች ፊት እጁ በካቴና የፊጥኝ በመታሰሩ በጣሙን አዝኛለሁ። ይህ አይነቱ ድርጊት እኔ በማወቀው አሜሪካ መሬት ላይ ይካሄዳል ብዩ በፍጹም አልጠብቅም። ይሁን እንጂ ህዝቡ ከጎናችን በመቆሙ በጣሙን ተደሰተናል።ለጄ ጉብዘናውን ለ አለም ለማሳየት የሚጥር በሩህ አይምሮ ያለው ነው።” ብለዋል ። የወላጅ አባቱን ሞባይል ስልክ ፣መኪና ፣ ኮምፒውተር እና የመሳሰሉትን እንደነበሩ አደርጎ የሚጠግነው አህመድም “በራሴ ጥረት የሰራሁትን ሰአቴን ለአስተማሪዩ በማሳየት ላስገርማት ብሞክር በአስተማሬ ተጠርጣሪነት(የውሸት ቦምብ ነው ብላ በመሰጋቷ ) የተነሳ ለእስራት በመዳረጊ እጅጉን አዝኛለሁ።ከዚህ በሁዋላ በዚህ ትምህርት ቤ/ት መማር በጭራሽ አልፈልግም ት/ቤቱን ለቅቄ መሄድ እሻለሁ።” ብሏል። አህመድ በ አሁኑ ወቅት ከት/ቤቱ መታገዱም ታውቋል።

የአህመድ በ አራት ፖሊሶች በጥር ጣሪ ታስሮ ወደ ወጣቶች ጽባይ ማረሚያ/ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ የጣት አሻራ ሰጥቶ መለቀቅ በሺዎች የሚቆጠሩ የማህበራዊ ድህረ ገጾችን ያጨናነቀ እና ተከታዮችን ያስቆጣ ሲሆን ለአብነት ያህል ፕ/ት ባራክ ኦባማ በቲዊተር አካውንታቸው “ አህመድ ድንቅ ሰራ ነው የሰራሀው ። ይህን የለፋት ወጤትህን ወደ ዋይት ሃወስ(ቤተ መንግስታቸው ) ይዘሀው እንደትመጣ ትፈልጋለህ? ።በአንተ ትጋት ብዙ ታዳጊዎች በሳይንስ ትምህርት እንዲማረኩ ታደርጋለህ ። አሜሪካ ማለት የታላቅ ጥረት ውጤት አገር መሆኑን አስመሰክረሃል ።”በማለት ጥረቱን አወድሰውታል።የፕ/ት ኦባማ ቢሮም በበኩሉ እሮብ እለት ባወጣው መግለጫው በመጪው ጥቅምት 19 2015 እኤአ በቤተመንግስታቸው/ዋይት ሃውስ ውስጥ በሚደረገው የ ሰነ ኮዋክበት ባለሙያዋች ምሽት ላይ ታዳጊው አህመድ አዳሩን በክበር እንግድነት ከሳይነቲስቶች፣ ከኮዋክብት አጥኝዎች፣ ከኢንጅነሮች ከአስተማሪዎች እና ከተማሪዎች ጋር ኣንዲያሳልፍ ጋብዞታል ። የፊስ ቡክ መሰራቹ ወጣቱ ማርክ ዙኩር በርግ እንዲሁ በሰጠው አስተያየት “አህመድ ለሰራው ፈጠራ እስራት ሳይሆን ሽልማት ነበር የሚገባው ።ለማንኛውም የሚቸግርህ ነገር ካለ ወደ ፊስ ቡክ ጎራ በል፣ ላገኝህ እወዳለሁ ” ብሎታል ። ታዋቂዎቹ እነ ጉግል እና ቲዊተርም አህመድን “በርታ ከእኛ ጋር መሰራት ከፈለግህ በሩ ሁሌም ለአንተ ክፍት ነው”ሲሉ ጋብዘውታል ። አንዱ በር ሲዘጋ ሌላኛው ወለል በሎ ይከፈታል ነው ነገሩ። አንዳንድ ወገኖች አህመድን ሰሙ እና ሃይማኖቱ ለጭፍን ተጠርጣሪነት እና ለእሰራት ሳይዳርገው እንዳልቀረ ይገምታሉ። ይሁን እንጂ ፖሊስ ግን ወቀስውን አሰተባብሏል ። “ከክስተቱ ብዙ ተምረናል ፣ክሱንም ወድቅ አድርገነዋል “ብሏል። አሜሪካዊው አህመድን ሰናሰብ በእኛም አገር ቢሆን ያለበቂ ማሰረጃ ለእሰራት እና ለመንጓጠጥ የሚዳረጉ ከታሰሩ በሁዋላለምን እና እንዲት እንደተፈቱ እንኳን የማያውቁ አያሌ ወገኖች መኖራቸውን አንዘንጋ። ቢያንስ ለእርምጃ አንቸኩል ፣ከሆነም ይቅርታ ለመጠየቅ አንዘግይ።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *