Hiber radio: በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆች አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም በአገር ቤት ያሉት ወኪሎች የእኛም ተወካዮች ናቸው ሲሉ ወሰኑ፣ በሕወሓት ኢህአዴግ አገዛዝ በአንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሪፖርት ብቻ ከ7ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ ተገድለዋል፣የባለስልጣናቱ ለዓለም ዓቀፉ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት አለመቅረብ ጠንካራ ስራ አለመሰራቱ ውጤት ጭምር ነው ተባለ፣ኬኒያ ባለሃብቶቼ መሬት ለመቀራመት ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱብኝ ነው አለች፣ በኢጣሊያው የላምባዱሳ ደሴት አቅራቢያ ለሞቱ ወገኖቻችን ተጠያቂዎች የሆኑ 6 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፣ሰሞኑን በጋምቤላ ለደረሰው የጎሳዋች ግጭት ” እጃችን የለብትም” ሲሉ የ ደ/ሱዳን ባለሰልጣናት አስተባበሉ፣ዶ/ር ሊክ ማቻር ለኢትዮጵያ አደገኛ መሆናቸው ተገለጸ፣የኢትዮጵያ፣የግብጽ እና የሱዳን መሪዎች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ግብጽ ውስጥ ሊመክሩ ነው እና ቃለ መጠይቅ ከኢትዮጵያዊው የሰብኣዊ መብት ተማጋችና ባለሙያ አቶ ያሬድ ሀይለማርያም ጋር፣በኡጋንዳ ምርጫ ላይ የተጠናከረ ዘገባና ሌሎችም

             የህብር ሬዲዮ የካቲት 6 ቀን 2008 ፕሮግራም <…በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ ባለስልጣናት በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃንን አስጨፍጭፈው በዓለም አቀፉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት አንድም ባለስልጣን ያለመቅረቡ የዓለም ዓቀፉ …

Read More