Hiber Radio: ኢትዮጵያን የዛሬው አገዛዝ ሶሪያ ሳያደርጋት ሕዝቡ በጋራ የተሻሉ አማራጮችን አሁኑኑ እንዲያዘጋጅ ተጠየቀ፣እስራኤል ለኢትዮጵያና ለኤርትራ የጦር መሳሪያ ማቅረቧ ተገለጸ፣ ኮ/ል መንግስቱ ሀ/ይለማሪያም ለፍርድ እንዲቀርቡ ዓለም አቀፍ ጥሪ ቀረበ፣ የኦሮሞ ሕዝብ በኦህዴድ አገዛዝ ራሱን አስተዳድሮ እንደማያውቅ አንድ ምሁር ሰሞኑን ተናገሩ፣በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞውን ተከትሎ ተደብድቦ ታሞ የነበረ ተማሪ ሕይወቱ አለፈ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የቀሩ ዋና ዋና አመራሮችን አገድኩ ያለው የስነስርዓት ኮሚቴ ሕገ ወጥ ውሳኔ ታገደ፣ ሕወሓት የአማራ ሕዝብን በጎሳ ለመከፋፈል የጀመረውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በድብቅ ያሰራጨው ሰነድ ተጋለጠ፣የቅማንት ጉዳይ የሕወሓት ዋና አጀንዳ መሆኑን በተዘዋዋሪ ሰነዱ አጋልጧል፣በሙስና የተዘፈቁት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማን ከስልጣን ለማውረድ የአገሪቱ ፓርላማ ማክሰኞ ለውሳኔ ሊቀመጥ ነው የሚሉና ሌሎችን ዜናዎች ጨምሮ የበዕውቀቱ ስዩም ከአሜን ባሻገር ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የጻፈውን በድምጽ ያነበበው፣ቃለ መጠይቅ እና ሌሎችም አሉን

   የህብር ሬዲዮ መጋቢት 25 ቀን 2008 ፕሮግራም <…አሁን ባለው መንግስት የፖለቲካና የተዛባ የኢኮኖሚ አስተዳደር ሳቢያ በዚሁ ከቀጠለ አገሪቱ የመፈራረስ አደጋ አጋጥሟታል። ይህን አደጋ የምናስቀረው እኛው ነን…በስልጣን ላይ ያለው መንግስት …

Read More