አሜሪካ ሙስሊም መሪ “አያስፈልጋትም “ ያሉ እጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪ ተቃውሞ ገጠማቸው

john_carson_donald_01

(በታምሩ ገዳ)

በመካሄድ ላይ ያለው የ አሜሪካዊያን የእጩ ፕሬዚዳንት ምረጡኝ ቅስቀሳ የተለያዩ ጉዶችን እና ግርምቶችን እያሰማን ነው። በሰሞኑ ቅስቀሳ ላይ ብቅ ያሉት ሪፐብሊካኑ እጩ ቤን ካርሰን ባለፈው እሁድ ከኢን ቢሲ ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ “አሜሪካ ከእሴቶቿ (values) እና ከ ህጎቿ ጋር የማይሄድ የእስልምና ሐይማኖት የሚከተል ፕ/ት በጭራሽ አያስፈልጋትም ፣ነገር ግን በተቃራኔው ከቆመ ችግር የለውም” በማለት መልሰዋል።

ጥያቄው በዚህ ብቻ አልተቋጨም ወረድ ሲልም “ታዲያ የእስልምና ሐይማኖት ከአሜሪካ ሕገ መንግሰት ጋር ይጣጣማል ብለው ያምናሉ?” የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። የቤን ካርሰን ምላሽ”ነው ብዩ በፍጹም ነው ብዩአላስብም ። አገሪቱን ሙስሊም ፕ/ት ይምራ ብዮ አልቀሰቅስም፣ በዚህ ሃሳብ በጭራሽም አልስማማም” የሚል ነበር ። የ64 አመቱ ጸሃፊው፣ፖለቲከኛው ፣ ጡረተኛው የእንጎል ቀዶ ጥገና ስፐሻሊስቱ(እዚህ ላይ የእርሳቸውም የእንጎል ሰራስር ትንሽ ላላ ያለ ይመሰላል) እና ወግ አጥባቂ ክርስቲያን የሆኑት ቤን ካርሰን ወዲያውኑ ከተለያዩ ወገኖች ተቃውሞዎች የገጠማቸው ሲሆን በተለይ የአሜሪካ የሙስሊም ካውንስልዳይሬክተር የሆኑት ኒሃድ አዋድ “ካርሰን በዚህ አንጋገራቸው ብቻ ብቁ ፕ/ት መሆን አይችሉም፣ከውድድር በቅድሚያ ሊባረሩ ይገባል፣ለእጩ ፕ/ታዊ ተወዳዳሪዎች የምመክራቸው ነገር ቢኖር የአሜሪካ ህገ መንግስት ምን እንደሚል በቅድሚያ አንዲያነቡት ነው ።”በማለት ተችተዋል፣መክረዋል።

የካርሰን የምረጡኝ ቅስቀሳ ቡደን በበኩሉ” የ እጩ ፕ/ታዊው የ ካርሰን አስተያየት ተጣሟል /ተጋንኖ ነው የቀረበው” ሲል መላሽ በመሰጠት የካርሰን አስተያየት የነበረው”አሜሪካ በአሁኑ ወቅት ሙስሊም ፕ/ት ለመቀበል ዝግጁ አይደለችም የሚል ነበር ፣ካርሰን በቅርቡ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማነጋገር ዝግጁ ናቸው።” በማለት አልሸሹም ዞር አሉ አይነት ምልሹን ሰጥቷል። ዛሬ ማክሰኞ የምረጡኝ ዘመቻውን ኦሃዮ ውስጥ ያካሄዱት ካርሰን ከቀደመው አቋማቸው ፈቀቅ እንዳላሉ “ይልቁንም ሃይማኖታዊ ተጽእኖ ለማሳደር የሚሻ ክርሰቲያናዊ መሪም ቢሆን ቦታ የለውም።”ሲሉ ተደምጠዋል።ካርሰን በአሁኑ ወቅት 20% ቅደመ ምርጫ ደጋፍ በማግኝት በረፖብሊካኑ ጎራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ከዚህ ቀደም “ ፕ/ት ኦባማ ትውልዳቸው አሜሪካ አይደለም ፣የልደት ካርዳቸውም ቢሆን አሜሪካዊነታቸውን ሰለ መጠቆሙ እጠራጠራለሁ ።”ያሉት (የሪፐብሊካኖችን እጩዎች እየመሩ ያሉት) ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሰሞን ደግሞ “ከተመረጥኩ የሜክሲኮ ሰደተኞች ወደ ግዛታችን (አሜሪካ ) ዝር እንዳይሉ በአለም ትልቁ የሆነ አጥር በድንበራችን ላይ እገነባለሁ፣ፕ/ት ኦባማ የክርስትና እምነትን እያጠፉ ነው። “ በማለታችው ከዲሞክራቶች ታላቅ ተቃውሞ ገጥሟቸው ሰንብተዋል ።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

One Comment on “አሜሪካ ሙስሊም መሪ “አያስፈልጋትም “ ያሉ እጩ ፕሬዝዳንታዊ ተወዳዳሪ ተቃውሞ ገጠማቸው”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *