Hiber Radio ፡በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ረሀቡን ዘንግቶ በተሃድሶ ድግስና ለፖለቲካ ስብሰባ በሚሰጠው የአበል ክፍያ የአገሪቱን ሀብት እያባከነ መሆኑ ተገለጸ፣በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ የአሜሪካ የደህንነት ሰራተኞች በደል ፈጸሙብኝ ያለ አሜሪካዊ ዜጋ ይግባኙ ውድቅ ሆነበት፣የ 19 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሚካኤል በሳውዝ ዳኮታ በጥይት ተገደለ ፣ግብጽ ህገ ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሯን ገለጸች፣እንግሊዝ በአየር ሀይላ ግቢ ለሰፈሩ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት መንፈጓ ቅሬታ አስነሳ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበት ሁኔታ አለመታወቅ አሳሳቢ መሆኑን ቤተሰቦቹ ገለጹ፣በቦትስዋና የፖለቲካ ጥገኝነት የጤቁት ኤርትራውያን ተጫዋቾች በወታደራዊ እስር ቤት እተሰቃዩ መሆኑ ተገለጸ፣የአቶ አስማማው ሀይሉ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ፣ዋልያዎቹ ድል ተቀዳጁ እና ሌሎችም አሉን

hiber_radio_program_cover_102515_02

 

የህብር ሬዲዮ  ጥቅምት 14 ቀን 2008 ፕሮግራም

<… የሀይማኖት አባቶች ፖለቲካ ውስጥ አንገባም በሚል ሽፋን በአገር ቤት የሚደረገውን በደል፣የዘር ማጥፋት ወንጀል አለመናገር አግባብ አይደለም የጥቅም ጉዳይ ካልሆነ በቀር አባቶቻችን እነ አቡነ ጴጥሮስ ለዕውነት ለአገራቸው ሞተዋል ዛሬ ወጣቶች በገንዘብ የማይተመኑ ምሁራን መፍትሄ አጥተው ጫካ ገብተዋል። የሀይማኖት አባቶች ግን ስርዓቱን ላለማስቀየም ፖለቲካ ውስጥ አንገባም የሚል አነጋገር ከየት የመጣ ነው? ከጥቅም አኳያ ነውማንም ሰው ስፍራ ይለቃል።የባቢሎን ግንብ እንኳን ተንዷል። መንግስት ይቀየራል።ቤተ ዕምነቶች ራሳቸውን ሊፈትሹ ይገባል። ፍርድና ፍትህ በሌለበት አገር ላይ የእምነት ተቋማት ፍርድ ሰጪ መሆን አለባቸው ።ለወገናቸው መጮህ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን…>

 ፓስተር ተፈራ ፈቃዱ  ከሰሞን አሜሪካ ኤልሻዳይ ዓለም አቀፍ የሳተላይት ቲቪ መንፈሳዊ አገልግሎት የሀይማኖት አባቶች ፖለቲካ ውስጥ አንገባም ማስፈራሪያ ማንን ለመጥቀም ሚለውን ጉዳይ አንስን ተወያይተናል (ሙሉውን አዳምጡት)

 <…ጋዜጠኛ ተመስገን ዕውነትን ስለጻፈ ነው ወንጀለኛ ነው ብለን አናምንም።አሁን ሙሉ ለሙሉ ቤተሰብም እንዳይጠይቀው ተከልክሏል። በዝዋይ እስር ቤት የወገብና የጆሮ ህመሙ ሕክምና ተከልክሎ እስረኞች እንዳያናግሩት እንዳይጽፍ እንዳያነብ በስቃይ ታስሮ አሁን ሙሉ ለሙሉ አትጠይቁትም የበላይ ትዕዛዝ ነው ተብለናል።በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አናውቅም ደህነቱ ያሳስበናልተመስገን ለዕውነትና ለፍትሕ ቆሟል ሕዝቡ ዛሬም ከጎኑ ቆሞ ድምጹን እንዲያሰማለት …> ታሪኩ ደሳለኝ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም ስለወቅታዊው ክልከላ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ሰራዊት (ኢሕአሰ) አባልና የዚያ ታሪክ ጸሐፊው አስማማው ሀይሉ(አያ ሻረው ) አጭር የሕይወት ታሪክ

በኢትዮጵያ የተከሰተው አስከፊው  የረሃብ አደጋ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስጋት ፈጥሯል(ልዩ ጥንቅር)

ከአቶ ኦባንግ ሜቶ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ (ክፍል ሁለት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ረሀቡን ዘንግቶ በተሃድሶ ድግስና ለፖለቲካ ስብሰባ በሚሰጠው የአበል ክፍያ  የአገሪቱን ሀብት እያባከነ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ የአሜሪካ የደህንነት ሰራተኞች በደል ፈጸሙብኝ ያለ አሜሪካዊ ዜጋ ይግባኙ ውድቅ ሆነበት

የ19 ኣመቱ ኢትዮጵያዊ ሚካኤል በሳውዝ ዳኮታ በጥይት ተገደለ

አምስት ብሔር ተኮር የኢትዮጵያ ተቋዋሚ ሐይሎች የኢሕአዲግ ስልጣንን ለማሳጠር  የጋራ ግንባር ፈጠርን አሉ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ያለበትን ሁኔታ አለማወቅ ቤተሰቡን እንደሚያሳስባቸው ገለጹ

ግብጽ ህገ ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሯን ገለጸች

እንግሊዝ በአየር ሀይሏ ግቢ የሰፈሩ ኢትዮጵያዊያኖችን ጥገኝነት መንፈጓ ቅሬታ  አስነሳን

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሰራዊት አባልና ታሪኩን በሁለት ቅጽ የጻፉት አቶ አስማማው ሀይሉ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

ቦትስዋና ውስጥ የፖለቲካ ጥገኝነት  የጠየቁት 10ሩ ኤርትራዊያን ተጨዋቾች በወታደራዊ እስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ ናቸው ተባለ

ኤርትራ የተመድ ላራዘመባት የመሳሪያ ማዕቀብ ዳግም   የኢትዮጵያውን አገዛዝ  ከሰሰች

የኔቫዳ ትራንስፖርት ባለስልጣን የሁበርና ሊፍት አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር ሰባት ተጨማሪ ሰራተኞችን ቀጠረ

የኢትዮጵያው ዋልያ ብሔራዊ ቡድን የቡርንዲ ቡድንን በአስገራሚ ሁኔታ በማሸነፍ ለቻን 2016 ውድድር አለፈ

ሸንጎ ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት አዲስ አመራር መረጥኩ አለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-102515-110215

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *