Hiber radio: የዓለም ጤና ድርጅት ለቀይ ስጋ አዘወታሪዎች የቀይ ካርድ ማስጠንቀቂያውን መዘዘ

ethio_meat_01

በታምሩ ገዳ

(ህብር ሬዲዮ) በመንግስታቱ የጤና ድርጅት(WHO) የካንሰረ ጥናት ማእከል በሰጋ አዘውታሪዎች ላይ አሳዝኝ እና እስደንጋጭ የሆነ መግለጫ አውጥቷል። መቀመጫውን በለዮን ፈረንሳይ ያደረገው ተቋሙ ሰኞ እለት ባወጣው ቀጭን ማሰጠንቀቂያው በተለያዩ መልክ ተቀመመው ከመደብሮች የሚገኙት (processed )ቤከን፣ሆት ዶግስ እና ሌሎች ፕሮሰሰድ የሰጋ ዘሮች ለ ካንሰር ሕመም የመጋለጣችን እድሉን ከ ፍ ያደርገዋል ሲል ያሰጠነቅቃል። ጥናቱ በመለጠቅም ቀይ ሰጋ የሚያዘወትሩ ሰዎች ለ ካንሰር “ምናልባት” ሊጋለጡ ይችላሉ ይላል።ፕሮሰሰድ የሆኑ የሰጋ አይነቶች ደግሞ ልክ እንደ አሰቤስቶስ እና የቱምባሆ ጢስ የሚመሳሰል ጉዳት አለው ተብሏል። ምንም እንኳን የጥናቱ ውጤት በማደግ ላይ ላለው የቀንድ ከብቶች ኢንዱስትሪይ ዘርፍ ምልካም ዜና ባይሆነም ከ አስር አገራት የተወጣጡ በአለም ላይ የሚገኙ ሃያ ሁለት እውቅ የህክምና ባለሙያዎች በአለም ላይ በሚገኙ በ ሰምንት መቶ ጥናቶች ላይ ባደረጉት የጋራ ምርምር እና” በቂ መረጃ አግኝተናል “ያሉት የሰጋ ነክ ምግቦችን ጣእም እና የመደረደርያ እድሚያችወን (ፕሪዘርቪንግ ) ለማራዘም ሲባል በጨው (ሳልቲንግ )፣ በመጥመቅ( ፈረመንቲንግ)፣ በጭስ መለበለብ( ስሞኪንግ)እና ቁንጣ(ከሪንግ) የተሰሩ እንደ ሆት ዶግ ፣ሶሰጅ፣ደረቅ ሰጋ ፣በቆርቆሮ የታሸጉ የሰጋ ዘሮች መጠናቸወን ሲያልፉ ለካንሰር ያላቸውን ቀረቤታ ማፋጠን ነው ይላል ከፈረንሳይ የወጣው እዲሱ ጥናቱ።

ጥናቱ ወደ ቀይ ስጋ ጉዳይ ሲመጣም(carcinogenic to humans) ቀዩን ሰጋ አንደ አገሪኛው በ ቁርጥ የሁን አንደ ክትፎ አለበለዚያ በጥብሰ ሆነ በ ወጥ መልክ ለሚያዘወትሩ ለጤና ጠንቅ የሆኑት አንደ አስበስቶስ(የኖራ ቡናኝ) ፣የትምባሆ ጢስ ፣የመኪና እና የመሳሰሉት ጢስ አንደ መማግ የቆጠራል ሲል ይሰጠነቅቃል።አነሰሳቱም ቢሆኑ ጥቦት ሆነ እሳማ፣ ፈየል፣የከብት ልዩነተ የለወም ዋንኛው ከመጠኑ ላይ ነው ተብሏል።የምናዘውተርው ፕሮሰሰድ የሆነው የ ስጋ ውጤት ለተለያዩ 16 አይነቶች የካንሰር አይነቶች ያጋልጠናል ያለው ጥናቱ ለምሳሌ ያህል በየቀኑ 50 ግራም(ጎበዝ እዚህ ላይ ልብ ይ በሉ እንዲት በሆዳችን ተገመተን አንበል እና መለኪያው በኪሎግራም ሳይሆን በግራም ነው ) የሆነ ፕሮሰሰድ ሰጋ በእየቀኑ መመገብ 18%የትልቁ አንጀት ካንሰር ተጠቂ ያደረጋል ሲሉ ምክርቸወን የለግሳሉ።

ያለተደባለቁት(ፕሮሰሰድ ያልሆኑት) ጥሬ ስጋዎቹ የእነ አሳም ፣የእነ በግ፣የእነ ፍየል ስጋ መዝወተራቸው “አስተማማኝ ባይሆነም “ “ጠንካራ “የሆነ ለካንሰረነት ምክንያት እንደ ሆኑት እነደ አሰቤስቶስ እና የሲጋራ ጢሶች ጋር እኩል ለካንሰር ጠንቅነት አላቸው ብለውናል ምሁራኖቹ።መቺም የሁሉ ጤነነት ጉዳይ ማጠነጠኛው ከሞት ጋር በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በልቺ ልሙት ካለለ በቀር ፕሮስሰድ ከሆኑ የሰጋ ውጤቶች ጋር በተያያዘ በአለማችን ላይ በአመት 34 ሺህ ሰዎች በእየ እመቱ ይሞታሉ። ከሲጋራ ማጤስ የተነሳ በአመት 6መቶ ሺህ ፣ በአየር ብክለት እና በ አልኮል መጠጥ ደግሞ 2 መቶ ሺህ ሰዎች ለሞት ይዳረጋሉ ። ከዚህ አኳያ በሰጋ ውጤ ት የሚመጣው የሟች ቁጥር አንስ ያለ ቢሆነም ትኩርት ሊነፈገው አይገባም ሲ ሉ ሳይንሲስቶቹ ይመክራሉ።

ይህ በእለተ ስኞ ብቅ ያለው አዲሱ ማሰጠንቀቂያን ብዙዎች ቢሰማሙበተም (እሰከ አሁን ደረስ የኢትጵያዊያን ስጋ አመራቺች እና ሰጋ አፈቃሪዎች አቋም አለተካተተም እንጂ) በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት የሰጋ ምርምር ማእከል የጥናቱን ውጤት ያጣጣለው ሲሆን “የተወስኑ ወገኖችን ቶርቸረ ለማደረግ የቀረበ አሃዝ ነው” የሚለው ይሄው ተቋም ብዙ ጤናማ ምግብ የመገባሉ ፣ ረጅም እድሜ ይኖራሉ የሚባሉት እነ ስፔን፣ ፈረንሳይ እና ጣልያን የመሳሰሉትን የአመጋገብ ባህልን ለማሰረጽ የተቃጣ ነው” በሎታል። እንግሊዞችም ብዙ ስዎች በአውሮፓ ወስጥ የሰጋ ምግብ ፈጆታቸው የተጋነነ ባይሆንም በሰጋ ውስጥ ያሉት እንደ ብርት እና ዚንክ የመሳሰሉት ወሳኝ ማእድናት ሊዘንጉ አይገባም፣ አንዲያውም”አትክለት ብቻ አዘወታሪዎች ለካንሰር በሽታ የመጋለጣቸ ወይም ያለመጋለጣቸው እድል ከሰጋ በላተኞች ጋር የተነጻጸረበት በቂ ማሰረጃ የለም “ ሲሉ ይሞግታሉ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዙ ሰጋ በላተኞች እያደጉባት የምተገኘ ኮሚኒስት ቻይናም በበኩሏ ዜጎቿ” እውን ሶሴጅ ፥ጨው የበዛበት ስጋ የመሳሰሉትን መብላት ለናቆም ነው?” በማለት እየጠየቁ ይገኛል ተበሏል። ቻይና በ እኤአ 2003 የነበራት የ 46 ኪሎግራም አመታዊ የነፍስ ወከፍ የሰጋ ተመጋቢዎቿ ኮታ በአሁነ ወቅት (የዜጎቿ ገቢ እና ኪስ ደጎስ በማለቱ) ቁጥሩ ወደ 60 ኪሎግራም ከፍ በሏል፡ ፡የቻይናው የ ሰጋ ማህበር በበኩሉ ሰኞ እለት ይፋ የሆነው የመንግስታቱ የጤና ተቋም ሪፖርትን ወዲያውኑ ውደቅ ያደረገው ሲሆን “አለማቀፍ ቆጠራ/ጥናት ያልተደረገበት’ሳይንሳዊ ያልሆነ ነው” ሪፖርቱ ይፋ ከመሆኑ በፊት ብዙ ጥናቶች ሊደረጉበት ይገባ ነበር ሲል የተቃርኖ አቋሙን ገልጿል። የቻይና መንግስት እሰከ እሁን ድረሰ የሰጠው መግለጫ ባይኖርም የቻይና ሕዝብ ከዚህ ቀደም በሕጻናት ወተት ሳቢያ ብዙ ህጻናትን በሞት በመነጠቁ ከመንግስት ባለሰልጣናት የሚወጣውን መረጃ በዙውን ጊዜ ተጠራጣሪ ነው “ሙሰኞች ናቸው” ይላል ። ይሁን እንጂ “በ ስጋ ብሉ ፣ በስጋ አትብሉ!” ዙርያ ግን ክርክሩ ጦፏል ገሚሱ”ገንዘብ ለማጋበስ ሲባል ይህንን ብሉ፣ ያንን ደግሞ አትብሉ ይሉናል” ሲል የተቀረው ደግሞ እስቲ ምን ምግብ ነው አንድንበላ የምንመከረው? ሲል ይጠይቃል።

የግርጌ ማስታወሻ አንዳንድ ወገኖች በኢትዮጵያ ውስጥ ከ 8.2 ሚልዮን በላይ ሕዝብ የእለት ጉርሱን ማግኘት ተሰኖት በሞት እፋፍ ላይ እያለ ለብዙዎች ህልም እና ” የቅንጦት ምግብ” ሰለ ሆነው ሰለ ሰጋ ማነሳሳት ምን አመጣው? ብለው ሊጠይቁ ይችሉ ይሆናል ። ነገር ግን አንደ አቅሚቲ ሆነ ሰጋ የሚመገቡ ወይም በቁንጣንም የሚሞቱ ወገኖችንም ማሰብ ተገቢ ይመሰለኛል ። “ማዘን ለተራበው ሳይሆን ለጠገብው ነው!” ይባል የለ?!። ከዚህ በተጨማሪ ምንም ሆነ ምን አዚህ ላይ የኢትዮጵያኖችን እና የጥሬ ሰጋ ታሪካዊ ቁርኝትን መዘንጋት የለብንም። የጨለመውም መንጋቱም አይቀረም ።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *