Hiber Radio: አልሽባብ ከወደቀ የጦር አውሮ ፕላን ውስጥ አሜሪካኖችን እና በርካታ ዶላሮችን መማረኩ ተነገረ

al_shebab_02

በታምሩ ገዳ (ህብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) መነሻውን ከኬኒያ በማድረግ መዳረሻውን ወደ ሶማሊያ ሊያደርግ የነበር አንድ የእፍሪካ ህብረት የ ሶማሊያ ዘማቾች የእቃ መጫኛ አውሮፕላን አሮብ አለት ከሞቋደስሾ ደቡባዊ ክልል ተከሰክሶ በመወደቁ በወስጡ የነበሩ ሰራተኞቹ ከአክራሪው አልሽባብ እጅ ሳይወድቁ አልቀረም የሚል ስጋት ናኝቷል።

ከሞቋዲሾ ሰሜናዊ ምዕራብ 100 ኬሜ ርቀት ላይ ከሚገኝው ወደ ባልዶጋሌ አውሮፕላን ጣቢያ ሲበረ የነበረው የእቃ መጫኛ አወሮፕላን በመጥፎ አየር ምክንያት(ዘናባማ እና ነፋሻማአየር ሳቢያ ) በገጠራማው የአፋጎም ቀበሌ ውስጥ ተከሰክሶ በወወድቁ ፣አካባቢውም በአክራሪው በአልሽባብ ቁጥጥር ሰር በመሆኑ በውስጡ የነበሩት ወደ 12 የሚገመቱ ምእራባዊያን ወታደራዊ ባለሙያዎች ከውስጡ እንደነበሩ ዛሬ አርብ ጥቅምት 30 2015 የገለጸው የጀርመኑ የዜና አገልግሎት ዳፕ(dap) አውሮፕላኑን በሄሊኮፕተር በማፈላለግ ላይ የሚገኙት የ አፍረካ ህብረት ኮማንደሮች እና “ምእራባዊያን ባለሙያዎች” የወደቀውን አውሮፕላን እንዳያገኙት አልሽባብ ኣውሮፕላኑን በርካታ የዛፍ ቅጠሎች በማልበሰ ከአየር ላይ ለሚደረገው ቅኝት ደብዛውን ሳይ ደብቀው እና በአውሮፕላኑ ውስጥም የነበሩ ሰራተኞችንም አልሽባብ ሳያሸሻቸው እንዳለቀረ የታችኛው ሸበሌ አስተዳደር አፈቀላጤ የሆኑት መሐመድ ሃሰን ሻይን ጥርጣሪያቸወን ለዜና አገልገሎቱ ገለጸዋል።ነገር ግን መጠነ ሰፊው የኣውሮፕላኑ እና የተሳፋሪዎቹን የማግኘት አሰሳ አየተካሔደ ነው ተብሏል።

አወሮፕላኑ በውስጡ 12 ሰዎች እንደነበሩበት እና በርካታ የአሜሪካ ዶላሮች በውስጡ ሳይጭን እንዳልቀረ የተገመተ ሲሆን የወታደራዊ ተጓዦቹ ዜግነት ለጊዜው ባይገለጽም የአሜሪካ ዘጎች ሳይሆኑ እናዳልቀር የሶማሊያ ከፈተኛ ባለሰልጣናት የጠራጠራሉ ። ይሁን እና የአሜሪካው የመከላከያ ሚ/ር (ፔንታጎን )ዘገባውን አሰተባብሏል።ማንነታቸው እናዳይጠቀሰ የጠየቁ በሞቋዲሾው አውሮፕላን ጣቢያ የሚሰሩ የበረራ /አቪዮሽን መቆጣጠሪያ ሰራተኞች አወሮፕላኑ ለደህንነት ሲባል የበረራ መረጃው ይፋ የማይደረግ ነገር ግን በማንኛውም ጊዜ ኣና ቦታ መብረር የሚችል (አንደር ከቨር) አውሮፕላን አንደነበር አወስተው የአሮፕላኑም መከሰከስ በቅድሜያ የተሰማው ከናይሮቢ የአየር መቆጣጠሪያ ነው ብለዋል።፡ የባይ ዶጎሌ አውሮፕላን ጣቢያ የአሜሪካ ወታደሮች በተለይ ለሰው አልባ አወሮፕላኖች (ድሮኖች) መጠቀሚያ አንደሚገለገሉበት ይነገራል። የአሜሪካኖች ነገር ከተነሳ ምንም እንኳን አልሽባብ ሰለወደቀው የወታደራዊ አውሮፕላን ሆነ በወስጡ ሰለነበሩት ስዎች ማነነት አሰከ አሁን ድረስ ምንም አይነት መግለጫ ባይሰጥም ከሰበርባሪው የተረፉ ስዎች ካሉ አሊያም የሞቱት ስዎቹም አሜሪካዊያኖች ከሆኑ አልሽባብ ሁኔታውን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታው አጉልቶ ሊጠቀምበት እንደሚችል ይገመታል።ሶማሊያ ከዚህ ቀደም ( አኤአ1996 ) በእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ ሰላም ለማሰፈን ብለው ወደ ሞቃዲሾ የዘለቁት የአሜሪካ ወታደሮች መጥፎ ገጠመኝ አይዘነጋም። የሶማሌያ ታጣቂዎች ሞቃዲሾ ውስጥ የአሜሪካ ወታደር አሰክሬን በጎዳናዎች ላይ በመጎተት ያም አሳዛኝ ገጠመኝ በምዕራባዊያን የቴሊቭዥን መስኮቶች በመታየቱ ሁኔታውም በአሜሪካኖች ዘንድ ከፈተኛ ቁጣ ማሰከተሉን ተከተሎ አሜሪካን ሶማሌያን እንደፈራረሰች ጥላት በሶማሊያ የነበራትን ጦሯን ወዲያውኑ ማስወጣቷ አይዘነጋም። አልሸባብ ደካማውን የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስትን በሃይል በመጣል የራሱ የሆነ እስላማዊ አገዛዝ ለመተግበር የሚነቀሳቀስ፣ ለበርካታ የጅምላ ጥቃቶች ሃላፊነት የወሰደ እና ከአልቅይዳ ጋርም ዝምድና ያለው አክራሪ ሙስሊም አንጃ መሆኑ ይነገራል

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *