Hiber Radio : እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የሸጠችው ሊኩሌር ሰሜን ኮሪያ እጅ እንዳይገባ ስጋት ፈጠረ፣ በኢትዮጵያ ድርቁን ተከትሎ የማጅራት ገትር በሽታ ተከሰተ፣በትግራይ ክልል ክትባት ተጀምሯል፣ የእንግሊዝና የኢትዮጵያው አገዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገናኝተውም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ መጨረሻው አልታወቀም፣የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች ሕክምናና ጠያቂ መከልከሉን ተከትሎ ለአገዛዙ የሰብዓዊ መብትና ዕንባ ጠባቂ የአቤቱታ ደብዳቤ አስገቡ ፣ሳውዲ በየመን ላደረገችው ወረራ ኤርትራ ድጋፍ ማድረጉዋ ተገለጸ ፣ የምርጫ 97ን ግድያ ካጣራው ሕጋዊው አጣሪ ኮሚሽን አባል ጋር ቃለ መጠይቅ የሰማዕታቱን አስረኛ ዓመት በመዘከር፣መምህር ግርማ ወንድሙን የተመለከተ ልዩ ዘገባና ሌሎችም

hiber_cover_110115

የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 21 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…ምርጫ 97 ተከትሎ እኛ በኮሚሽኑ ያጣረነው እንኳን 193 ሲቪሎች፣ 6 ፖሊሶች ተገድለዋል። 763 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። 40 ሺህ በልዩ ልዩ እስር ቤቶች በአንድ ጀምበር ታስረዋል። ይሄ የሚረሳ አይደለም ነገር ግን እኛ አንድ ነገር ሲመጣ አንድ ሰሞን በዚያ እንገረማለን ወይ እናዝናለን መልሰን ደግሞ ወደ ሌላው እናልፋለንእኔ በበኩሌ አቶ መለስ በምርጫ 97 የተገደሉት ሁኔታ እውነቱ እንዲወጣ የሚፈልጉ መስሎኝ ተሳስቼ ነበር። መንግስት ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ ወስዷል ብለን ከወሰንን በሁዋላ ማስፈራራቱ ግርግሩ በዝቶ አቶ መለስ ጋር ስንገባ ለምንድነው እንዲህ የሚደረገው አጣሩ አላችሁን አጣራን እኔ ለምንድነው ይሄን ስላጣራሁ የምሞተው ትገደላላችሁ እየተባልን ነው ስንላቸውይሄ ማስፈራራቱ ምናምኑ ቁንጥጫ ነው ጎራዴው ግን እኛጋር አለ አሉን።…> አቶ ምትኩ ተሾመ በምርጫ 97 የተፈጸመውን ግድያ ያጣራው የሕጋዊው አጣሪ ኮሚሽን አባል ጥቅምት 22 አስረኛ ዓመቱን በማስመልከት ካደረግንላቸው ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

መምህር ግርማ ወንድም ማናቸው? ለምን ታሰሩ? ለመሆኑ ለቤተ ክርስቲያን ምን አድርገዋል? በእርግጥ እንደተባለው አጭበርባሪ ወይም ጠንቋይ ናቸው? አገዛዙ ከመምህር ግርማ የፈለገው ምንድነው? መምህር ግርማ ከኢትዮጵአ መንፈሳዊ አገልግሎት እስከ ሱዳን ስደት የኖሩበትን እና በአገር ቤት ያደረጓቸውን መንፈሳዊ አስተዋጽዎዎች ምንድናቸው? በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያሰናዳነውን ይዘናል( ልዩ ጥንቅር)

ሁበር በቬጋስ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተለይ አዲስ የጀመረው ተጨማሪ አገልግሎት ላይና የሁበር አሽከርካሪዎች የገጠማቸው ችግሮች (ውይይት )

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የሸጠችው ሊኩሌር ሰሜን ኮሪያ እጅ እንዳይገባ ስጋት ፈጠረ

በኢትዮጵያ ድርቁን ተከትሎ የማጅራት ገትር በሽታ ተከሰተ

በትግራይ ክልል ክትባት ተጀምሯል

የእንግሊዝና የኢትዮጵያው አገዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገናኝተውም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ መጨረሻው አልታወቀም

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች ሕክምናና ጠያቂ መከልከሉን ተከትሎ ለአገዛዙ የሰብዓዊ መብትና ዕንባ ጠባቂ የአቤቱታ ደብዳቤ አስገቡ

ሳውዲ በየመን ላደረገችው ወረራ ኤርትራ ድጋፍ ማድረጉዋ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስርቆትን ለመከላከል በሚል ልምድ ሊወስዱ ናይጄሪያ እንደነበሩ የአገሪቱ ጋዜጣ ዘገበ

የቴሌ ባለስልጣናት አገልግሎቱን ለውጭ ኩባንያ መስጠት ገንዘብ ማሸሽ ነው ሲሉ ገለጹ

አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ በአበበ በቂላ ስም የተዘጋጀውን ሽልማት ተቀበለ

የባህር ዳር የባጃጅ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-110115-110815

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *