Hiber radio: በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆች አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም በአገር ቤት ያሉት ወኪሎች የእኛም ተወካዮች ናቸው ሲሉ ወሰኑ፣ በሕወሓት ኢህአዴግ አገዛዝ በአንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሪፖርት ብቻ ከ7ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ ተገድለዋል፣የባለስልጣናቱ ለዓለም ዓቀፉ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት አለመቅረብ ጠንካራ ስራ አለመሰራቱ ውጤት ጭምር ነው ተባለ፣ኬኒያ ባለሃብቶቼ መሬት ለመቀራመት ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱብኝ ነው አለች፣ በኢጣሊያው የላምባዱሳ ደሴት አቅራቢያ ለሞቱ ወገኖቻችን ተጠያቂዎች የሆኑ 6 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ፣ሰሞኑን በጋምቤላ ለደረሰው የጎሳዋች ግጭት ” እጃችን የለብትም” ሲሉ የ ደ/ሱዳን ባለሰልጣናት አስተባበሉ፣ዶ/ር ሊክ ማቻር ለኢትዮጵያ አደገኛ መሆናቸው ተገለጸ፣የኢትዮጵያ፣የግብጽ እና የሱዳን መሪዎች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ግብጽ ውስጥ ሊመክሩ ነው እና ቃለ መጠይቅ ከኢትዮጵያዊው የሰብኣዊ መብት ተማጋችና ባለሙያ አቶ ያሬድ ሀይለማርያም ጋር፣በኡጋንዳ ምርጫ ላይ የተጠናከረ ዘገባና ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ የኦሮሚአን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከተገደሉት የቀብር ስነ ስርኣት፣የሕወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት በከፊልአቶ አሬድ ሀ/ይለማርያም ፣ ከታች የኡጋንዳው ፕ/ት ሙሴቬኒ፣እኛ ለእኛ ጉባዔ ጥሪ፣በቬጋስ ከኣመታት በፊት የታክሲ አሽከርካሪዎች ቲኤን ሲቃወሙ
የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ የኦሮሚአን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከተገደሉት የቀብር ስነ ስርኣት፣የሕወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት በከፊልአቶ አሬድ ሀ/ይለማርያም ፣ ከታች የኡጋንዳው ፕ/ት ሙሴቬኒ፣እኛ ለእኛ ጉባዔ ጥሪ፣በቬጋስ ከኣመታት በፊት የታክሲ አሽከርካሪዎች ቲኤን ሲቃወሙ

             የህብር ሬዲዮ የካቲት 6 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ ባለስልጣናት በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃንን አስጨፍጭፈው በዓለም አቀፉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት አንድም ባለስልጣን ያለመቅረቡ የዓለም ዓቀፉ የፖለቲካ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን በእኛም በኩል የሰብዓዊ መብት የጣሱትን በየሄዱበት ተከታትሎ ለፍርድ ለማቅረብ ጠንካራ ከፖለቲካው ትግል ጎን ለጎን ራሱን የቻለ በባለሙያዎች የታገዘ ተከታታይ እና ዘላቂ ስራ መስራት አልተቻለም። ዛሬም እነዚህ ባለስልጣናትን በተለያየ ግፍ የፈጸሙትን በኣለም አቀፉ ይሁን በምዕራባውያን ሕግ ለመፋረድ አንድ ጠንካራ ስራ መሰራት አለበት።እኛ መስራት የምንችለውና ያልሰራነው ግን…> አቶ ያሬድ ሐ/ማርያም ኢትዮጵያውያን የሰብዓዊ መብቶች ማህበር ዳይሬክተር ከቤልጂየም ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ (የመጀመሪያውን ክፍል ያዳምጡት)

 <…ትብብር ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጠራው እኛ ለእኛ ጉባዔ ላይ የተገኘነው ከተለያየ ብሄረሰብ የተውጣጣን በጋራ የአገራችን ዛሬ ያለችበትም ሆነ ነገ ያለው ሁኔታ የሚያሳስበን ወገኖች ነን። ተሰባስበን በጋራ በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ውይይት አድርገናል።እንደዚህ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ ጉባዔ ወደፊትም መቀጠል ያለበት ኢትዮጵያውያን በአገራችን ጉዳይ የምንመክርበት ጥሩ አጋጣሚ ነው…> አቶ ሮባ አህመድ አክቲቪስት ከቬጋስ ትላንት በሜሪላንድ በተደረገው እኛ ለእኛ ጉባዔ ከቬጋስ ሄዶ ከተሳተፈበት ስለ ጉባዔው ከሰጠን ማብራሪያ ተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

 15 ሚሊዮን የኡጋናዳ ሕዝቦች ላለፉት 30 አመታት አገሪቱን በአንድ ፓርቲ እዝ የመሩት ፕ/ት ዮኢሪ ሙሲቪኔን ዳግም ለመመረጥ አሊያም አገዛዛቸውን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማሰወገድ የፊታችን ሃሙስ ደምጻቸውን ለመሰጠት በነቂስ ይወጣሉ። ሙሴቪኒ ግን እሩጫዬ ገና ነው ፣ጉዞዬም እሩቅ እና ራዕዬም ሰፊ ነው ይላሉ ( ልዩ ዘገባ )

 አሜሪካ ያልተስሟሟትን የአፍሪካ መሪዎች እንዴት ባለ ሁኔታ ከስልጣን እንደምታባርርና ሕዝባቸውን እየረገጡ ከእሷ ጋር የተወዳጁት ምን ያለ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ከወቅቱ ተጨባጭ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር ሲቃኝ(ልዩ ዘገባ)

 የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ቅሌትና እና የቬጋስ አሽከርካሪዎች ጉዳይ በሕግ አውጭዎቹ ፊት የተሰጠ ምስክርነት (ቃለ ምልልስ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆች አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም በአገር ቤት ያሉት ወኪሎች የእኛም ተወካዮች ናቸው ሲሉ ወሰኑ

በሕወሓት ኢህአዴግ አገዛዝ በአንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሪፖርት ብቻ ከ7ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ ተገድለዋል

 የባለስልጣናቱ ለዓለም ዓቀፉ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት አለመቅረብ ጠንካራ ስራ አለመሰራቱ ጭምር ነው ተባለ

 በኢጣሊያው የ ላምባዱሳ ደሴት አቅራቢያ ለሞቱ ወገኖቻችን ተጠያቂዎች የሆኑ 6 ግለሰቦች   በእስራት ተቀጡ

 ከቤልጄየም ወደ ኢትዮጵያ የተባረረው ኢርትራዊ ሰደተኛ ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል

 ሰሞኑን በጋምቤላ ለደረሰው የጎሳዋች ግጭት ” እጃችን የለብትም” ሲሉ የ ደ/ሱዳን ባለሰልጣናት አስተባበሉ

የጦር ጄነራሎቻቸውም ጋምቤላ ውስጥ ያለመታሰራቸውን ተናገሩ

ኬኔያ ባለሃብቶቼ መሬት ለመቀራመት ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱብኝ ነው አለች

የኢትዮጵያ፣የግብጽ እና የሱዳን መሪዎች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ግብጽ ውስጥ ሊመክሩ ነው

የደቡብ ሱዳኑ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣን ዶ/ር ሪክ ማቻር ለኢትዮጵያ አደገኛ መሆናቸው ተገለፀ

በጋምቤላ የጎሳ ግጭት ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር መሪ በሀሰት ስማቸው እንደተነሳ ገለፁ

የኦሮሚያ ሰሌዳ የለጠፉ ላይ አገዛዙ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የጣለውን እገዳ በተጠናከረ ተቃውሞ ለመለወጥ ተገደደ

የአሜሪካዊያኖች አመታዊው የፕሬዘዳንታዊ ክብረ በአል ቀንን በደማቅ ያከብራሉ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-021416-022116

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *