Hiber Radio: ኦነግ ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሌሎችም የነጻነቱን ትግል ይቀላቀሉ ሲል ጥሪውን በድጋሚ አቀረበ፣የአዲስ አበባ ጉዳይ በሕዝቡ ወደፊት የሚወሰን ይሆናል ፣ ወያኔ ቢወድቅ አገሪቱ ትበታተናለች የሚለው የስርዓቱ ቅዠት መሆኑን ገለጸ ፣በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሃብ ለመቋቋም የገንዘብና የሎጀስቲክ ችግሮች መከሰታቸው ስጋት ፈጠረ፣ኬኒያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያወዛግባትን ቁልፍ በማዕድን የበለጸገ መሬት በድርድር ለመውሰድ ዘመቻ ጀመረች፣ዶ/ር መረራ ጊዲና የሚመሩት ኦፌኮ ቢሮ በወታደሮች ቁጥጥር ስር ወደቀ በስፍራው የነበሩ ተደብድበው ታሰሩ፣ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው የጥናት ውጤት አይገዛኝም ማለቱዋ ተዘገበ፣የሕወሓት ወታደራዊና የደህነት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማፈን ተጨማሪ ወታደሮች ተሰማርተው አፈናው እንዲቀጥል ወሰኑ፣የተቃውሞው አመራሮች ጊዜው ሲደርስ ራሳቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ተገለጸ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች ቃለ መጠይቅ ከኦነግ የድርጅትና ፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ እና ከታሪክ ተራኪው ኤድዋርዶ ጋር ሌሎችም አሉን

habtamu05

የህብር ሬዲዮ የካቲት 13 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…የኦሮሞ ወጣቶች ትግል ከወያኔ ጋር እንጂ ከማንም ጋር አይደለም ።የወያኔ የጭካኔ እርምጃ መንፈራገጥ ካልሆነ ትግሉን የሚያቆም አይደለም ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷልትግሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በእኩልነት የሚተዳደሩበት ስርዓት መፍጠር ነው።ሁሉም ትግሉን ሊቀላቀል ይገባዋልየአዲስ አበባ ወይም ፊኒፊኔ ጉዳይን እኛ የኦሮሚያ ክልል አካል ናት ብለን ነው የምናውቀው።የወያኔን ሕገ መንግስትንም ሆነ የወያኔን መግለጫዎች በጠቅላላ አንቀበልም።የፊንፊኔንም ሆነ የአዲስ አበባን ሁኔታ ወደፊት ሊወስን የሚችለው ሕዝቡ ነው።ሕዝቡ በፌዴሬሽን በኮንፌዴሬሽን ወይንም በተለያየ መንገድ አብሮ የመኖር ውሳኔ ካለው ፊንፊኔ በምን አይነት ሁኔታ ልትተዳደርና በምን አይነት ሁኔታ ልትኖር እንደምትችል ለወደፊት የሚታይ ነገር ነው።ለወደፊት የአገሪቷም ማዕከል የማትሆንበት ምክንያት የለም።ለሁሉም ይህንን ሊወስን የሚችለው ሕዝቡ ነው…> አቶ ኦዳ ጣሴ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) በውጭ የድርጅትና የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ   የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

 <…የየካቲት 12 ሰማዕታት ጉዳይ ሲነሳ በአብዛኛው የሚታወሱት ወይ ስማቸው የሚነሳው አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ወጣቶቹ አርበኞች በግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ያደረጉት ናቸው። ባለፈው ዓመት በዚህ ብሮግራም ቦንቡን በቤት ውስጥ ለወጣቶቹ የሰራላቸውን አባ አምዴን አንስተናል። ዘንድሮ ደግሞ በዕለቱ ታላቅ ተግባር የፈጸሙትን ወጣት አርበኞች እናስታውስ። እነዚህምታሪክን በታሪክነቱ መውሰድና መረዳት እንጂ ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከር አይገባም። አባቶቻችን በብሄር ተከፋፍለው ታሪክ አልሰሩም።መስዋዕትነታቸው በአንድ ላይ ተሪኩም የጋራ ታሪካቸው ነው።ወጣቶች ዛሬ የሚደረገውን ታሪክን የማዛባትም ሆነ የማጥፋት ለመከላከል እውነትን መመርመር የታሪክ መዛግብትን ማገላበት አለባቸው።ይህ ካልሆነ ግን…> ታሪክ ተራኪው ኤድዋርዶ ባይኖሮ የየካቲት 12 ሰማእታት አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ የአክብሮት ምሽት በቬጋስ መካሄድን አስመልክቶ ከአዘጋጆቹ አንዱ ጋር ቆይታ

የኔቫዳ የዲሞክራቲክ ካከስ ምርቻ የሂላር አሸናፊነትና የሴናተር በርኒ ሳንደርስ መራጮች   ( አጭር ቆይታ  ከመራጮች ጋር )

ዓለማችን የኢኮኖሚ እስትንፋስ እና የራስ ምታት የሆነው የነዳጅ ምርት አቅርቦት እና የአምራች አገሮች ስጋቶች  ከመጪው እቅዳቸው ጋር ሲቃኝ(ልዩ ወቅታዊ  ዳሰሳ)

  የአሜሪካ በጥቅሟ ላይ የተመሰረተው የውጭ ፖሊሲ እና ከአፍሪካውያን አምባገነኖች ጋር ቀን እስኪጎድልባቸው የምትፈጥረው ወዳጅነት በቆዩት ዲፕሎማቶቿ ሪፖርት ውስጥ ሲፈተሽ(ልዩ ዘገባሁለተኛ ክፍል)

በረድ ግጥም

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኦነግ ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሌሎችም የነጻነቱን ትግል ይቀላቀሉ ሲል ጥሪውን በድጋሚ አቀረበ

የአዲስ አበባ ጉዳይ በሕዝቡ ወደፊት የሚወሰን ይሆናል

 ወያኔ ቢወድቅ አገሪቱ ትበታተናለች የሚለው የስርዓቱ ቅዠት መሆኑን ገለጸ

በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሃብ ለመቋቋም የገንዘብና የሎጀስቲክ ችግሮች መከሰታቸው ስጋት ፈጠረ

ኬኒያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያወዛግባትን ቁልፍ በማዕድን የበለጸገ መሬት በድርድር ለመውሰድ ዘመቻ ጀመረች

/ መረራ ጊዲና የሚመሩት ኦፌኮ ቢሮ በወታደሮች ቁጥጥር ስር ወደቀ በስፍራው የነበሩ ተደብድበው ታሰሩ

ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው የጥናት ውጤት አይገዛኝም ማለቱዋ ተዘገበ

የሕወሓት ወታደራዊና የደህነት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማፈን ተጨማሪ ወታደሮች  ተሰማርተው አፈናው እንዲቀጥል ወሰኑ

የተቃውሞው አመራሮች ጊዜው ሲደርስ ራሳቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ተገለጸ

የህቡው መሪዎች የስትራቴጂ ለውጥ ያደርጋሉ ተብሎ ተጠብቋል

የኤርትራ ጦር ሃይል የደምብ ልብስን የለበሱ ታጣቂዎች በኢትዮኤርትራ ድንበር ላይ 80 በላይ ወጣት ኢትዮጵአውያንን አፍነው ወሰዱ

ስለ ጉዳዩ የአዲስ አበባም ሆነ የአስመራ ባለስልጣናት ያሉት የለም

ሒላሪ ክሊንተን በኔቫዳ ከዲሞክራት መራጮች የበለጠ ድጋፍ አግኝተው በርኒ ሳንደርስን አሸነፉ

የኡጋንዳውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዩዌሪ ሙሲቪኒ አሸነፉ መባሉ በአገሪቱ ውጥረት አነገሰ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-022116-022816

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *