Hiber radio: አንድ ጸረ እስልምና እና ጸረ ሰደተኞች ማስታወቂያ በተተከለ በአንድ ቀኑ አንዲወርድ ተደረገ፣ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም አሜሪካንን ለምን አምርረው ይጠሉ እንደነበር ያውቃሉ?

add_against_imigrant_001_menege

በታምሩ ገዳ

እርሶስ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲነሳ/እንዲተከል የሚፈልጉት ማስታወቂያ ፣አንቀጽ ወይም ሃውልት የትኛውን ነው?

በአሜሪካው የሚኒሶታ ግዛት በቅዱስ ዮሴፍ ከተማ በስታርንስ ቀበሌ ውስጥ አንድ ሕዝብን ፣ከሕዝብ ሃይማኖትን፣ ከሃይማኖት ሊያቃቅር የችላል ተብሎ የተገመተ አውዛጋቢ ማስታወቂያ /ቢልቦርድ ብዙም ሳይቆይ ፣ከተሰቀለ ከአንድ ቀን ቆይታ በሁዋላ በነዋሪ ማህበረሰቡ እሮሮ የተነሳ አንዲወረድ ተደርጓል። “Catholic Charities Resettles Islamists : EVIL or INSANITY?” (ካቶሊኮች እስላሞችን በአካባቢያቸን እያሰፈሩ ናቸው ፣ይህደርጊት ስይጣነነት ነ ወይስ እብደት ነው ?) የሚለው ማስተታወቂያ በአካባቢው የሚገኙ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ማህበረሰብ ከ ሙስሊሙ ሰደተኞች እና ሰፋሪዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነትን በጤናማ ጎኑ አያነጸባርቅም የተባለ ሲሆን ማስታወቂያውም ባለፈው ማክሰኞ የካቲት 16/2016 ከተተከለ በሁዋላ በበነጋታው(እረቡ) እለት ከተተከለብት ስፍራ በፍጥነት እንዲውረድ ተደርጓል። ይህ በአንድ ግለሰብ ፍላጎት እና የገንዘብ ወጪ የተተከለው ማስታወቂያ በቅርቡ ከ 300 በላይ የሶማሊያ ተወላጆች እና መሰል ሰደተኞች (ኢትዮጵያዊያኖችንም ያካትታል ) እና የሙስሊም ማህበረሰብ እንዲሰፈሩ በተደረገበት ስፍራ የተተከለ ሲሆን የማስታወቂያውም መልእክት ሰደተኞቹ ወደ አካባቢው አንዲመጡ የተገፋፉት በካቶሊክ ገብረሰናይ ድርጅቶች አማካኝነት እንደሆነ ተድረጎ ነበር የቀረበው ።ይሁን እና የካቶሊክ ቤ/ክርስቲያን ከማስፈር ፕሮግራሙ ጋር ምንም አይነት ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሌላት አሰተባብላለች። ነገር ግን ቤተክርስቲያኒቱ ዘር ፣ጾታ ፣ሃይማኖት እና ቀለም ስትለይ የኑሮ ውጣውረድ ጀርባቸውን ያጎበጣቸውን ሁሉንም ዜጎች በተመጣጣኝ ክፍያ መኖርያ ቤት እንደምታቀርብላቸው አልሸሸገችም። በሚኒያፖሊስ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በተለይ የኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚኖሩባት ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ አየጨመረ የመጣው የሶማሊያ ማህበረሰብ ጉዳይ ግን ለአካባቢው ቀደምት ነዋሪዎች ስጋት መፍጠሩ አልቀረም።የአሜሪካ እስላሚክ ካውንስል የሚኒሶታ ክፍል( ቻፕተር) ተጠሪ ሰሞኑን በሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ ለተገኙ ከ 500 በላይ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ባሰሙት ንግግር በሚኒሶታ የሚገኙ የሙስሊም ማህረሰብ ከሌላ እምነት ተከታዩች ብርቱ የጥቃት ደመና እንዳንጃንበባቸው መግለጻቸውን ስታር ትሪቢዩን የተባለው ጋዜጣ ሃሙስ እለት አስነብቧል። በምድረ አሜሪካ ዜጎች የሌላውን ገለሰብ አፍንጫን እሰካልነኩ ድረስ የፈለጉትን የድጋፍ ይሁን የተቃውሞ ሃሳብ የማሰማት ገደብ የለሽ መብታቸው ( በፍርስት አመንድመነት ) ውስጥ የተካተተላቸው /የተከበረላቸው ቢሆንም ከማሕበረሰብ የስልጣኔ ደረጃ እኗኗር አኳ ያ ተቀባይነት ያላቸው እና ተቀባይነት የሌላቸው ማስታወቂያዎች፣ የህትመት ውጤቶች ከሕዝቡ መሃል በገፍ ከመሰራጨታቸው በፊት ከእይታዎች እንዲርቁ የሚደረጉባቸው ጌዚያት በርካታ ናቸው ። ምክንያቱም አሜሪካ የብዙሃኑ ብቻ ሳትሆን የአናሳዎቹም የማህበረሰብ ክፍል ውህደት መሆኑዋን ጠንቀቀው ሰለ ሚያውቁ እና ኋላም የሚያስከትለው መዘዝን ጠንቅቀው ሰለሚገነዘቡ ነው ። ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ሃየለማሪያም ለምን አሜሪካንን አምርረው ይጠሉ ነበር? ይህ ሁሉ ሲሆን ዛሬ ብዙዎቻቸን በአገራቸን በኢትዮጵያ እንዲተገበር የምንናፍቀለት እና ሁሌም የምንጎመዥለት የምእራባዊያኖቹ ዲሞክራሲ ከዚህ ደረጃ ለመድረስ ሁሉም ነገር የተደላደለላቸው አልነበረም ። ለምሳሌ ያህል ከዛሬ ስድሳ አመት በፊት የነበረውን ዘረኝነትን ሰንቃኝ በአንዳንድ የአሜሪካ የመዝናኛ ሰፍራዎች እና ምግብ ቤቶች መግቢያ ላይ ዘርን እና ቀለምን ማእከል ያደረጉ ጸያፍ ማሰታወቂያዎች በግላጭ ይለጠፉ እንደ ነበር ከምደረ አሜሪካ ከላስ ቬጋስ ከተማ ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 6፡30ፔኤም (በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡30) በአማሪኛ ቋንቋ የሚስራጨው ከዚያም ባሻገር በተወዳጇ በ ዘ -ሃበሻ ድህረ ገጽ አማካኝነት በመላወ አለም ተሰዶ ከሚገኘው ሕዝባችን ጆሮ የሚደርሰው የሕብር ራዲዮ እና የተወዳጆቹ አድማጮቿ በ 2010 አኤ አ የክብር እንግዳ የነበሩት ፣ የቀደሞው የኢትዮጵያ ርእሰ ብሔር የሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ብርጋዴር ጄነራል ታመነ ድልነሳው በትውስታ ማህደራቸው እንዳሰቃኙት “ወደ አሜሪካው የሜሪላንድ ግዛት ለወታደራዊ ትምህርት የተጓዙት ሌ/ ኮ/ል መንግስቱ እና ወጣት የሰራዊቱ አባላት በበርንላንድ ወታደራዊ ተቋም የሰልጠናቸው ወቅት በሳምንቱ ማብቂያ ላይ ለመዝናናት ሲፈልጉ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ ወደ አንድ ሬስቶራናት ጎራ ይላሉ። እነ ሌ/ኮ መንግስቱ ከ ምግብ ቤቱ ደጃፍ ላይ “ጥቁሮች እና ውሻ በፊት ለፊት በር እንዲገቡ አይመከርም “ የሚል ማስታውቂያ ያነባሉ ፣ ወጣቱ መንግስቱ ሃይለማሪያምም በወቅቱ በአሜሪካ ውስጥ ስር የሰደደ የመደብ ፣የቀለም ልዩነት እና የዘረኝነት መንፈስ እንዳለ ይረዳሉ ። ከዚያ ጊዜ አንሰቶ ሌ/ኮ/ል መንግስቱ ወደ አገር ቤት ሲመለሱ ( ዛሬም ቢሆን )ለአሜሪካ ያላቸው አመለካከት መሪር ሆነ ፣ መንግስቱ እና አሜሪካ ሆደ እና ጀርባ ሆነው ዘለቁ።” በማለት ጄ/ል ታመነ ትዝታቸውን አውግተዋል። አንዳንድ ዘገባዎች በበኩላቸው ሌ/ኮ/ል መንግስቱ ከ ሶሻሊስቱ ጎራ (አመለካከት ) የተቀላቀሉት ከዚያው ከአሜሪካ መሬት ሳይወጡ ነበር።

ሌ/ኮ መንግስቱ ሃይለማሪያምም በተለያዩ መድረኮች ላይ በሚያሰሟቸው ንግግሮቻቸው ላይ በወቅቱ ገንጣይ እና አሰገንጣዮች በማለት የሚያወግዟቸው እና የሚያብጠለጥሏቸው ሻቢያ እና ወያኔን ሰያወግዙ ይህንን እኩይ ተግባርን ከጀረባ ሆነው ከሚዘውሩት መካከል የአረብ ሃገራት እና አሜሪካንንም መወረፋቸው ይታወሳል። በአሰር ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰላሚዊ ዜጎች መታሰር ፣መገረፍ መሰደድ እና መሞት ተጠያቂ ተደርገው የሚፈርጁት ሌ/ኮ መንግስቱ ሃይለማሪያም የቀደሞ ፕ/ት ቡሽ ልዩ መልእክተኛ የነበሩት ሴናተር ሩዲ ቦሽቺዊዝን ባነጋገሩበት ወቅት “ለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል ሰልጣኔን እለቃለሁ “ማለታቸውን ኒዮርክ ትይምስ ጋዜጣ በወረሃ ግንቦት 22/ 1991 እኤአ ዘግቦታል ። ሌ/ኮ መንግስቱ በአሁኑ ወቅት ከደቡባዊ አፍሪካ (በዙምባብዌ) ውስጥ በሰደት አለም ይገኛሉ ። ታዲያ ያ ጸረ አሜሪካ አመለካከታቸው የቀይር ወይም ይጠንክር ለጊዜው መረጃ ባይኖርም ያቺ እንደ ጉድ የጠሏት አሜሪካ ግን ዛሬ ለአራት ኪሎው ቤተመንግስት ቤተኛ ሆናለች ። ጊዜ ተለዋዋጭ ነውና ። ወደ ተነሳንበት ቀዳማዊ ሃሳብም እና ተዛማጅነት ወዳለው ነጥብ ሰንመለስ ዛሬ በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ወደድነውም ፣ ጠላነውም ፣ገልጥልጥ አደረግነው አሊያም ሸፋፈነው የዘር እና የጎጥ ጥላቻ እና የወገንተኝነት ስሜት እያቆጠቆጠ ለመሆኑ ብዙም ማስረጃዎች ማጣቀስ አያሻውም ። እንደሚታወቀው እና ታሪክ እንደሚም ያስተምረንም አገርን ፣ አካባቢን ሆነ አገዛዘን ለመቀየር መጀመሪያ ራስን መለወጥ ግድ ስለሚል ሕዝቡ ነገሮችን የመለወጥ ሙሉ መብቱ ቢኖረው( እዚህ ላይ እርሶም የሕዝቡ አንድ አካል መሆኖትን ሳይዘነጉ ) የትኛው አመለካከት፣ አባባል፣ፖሊሲ፣ በአይነ ህሊናችን ወይም በገሃዱ የምናየው ምስል እና ሃውልት እንዲቀየር ወይም እንዲተከል ይሻሉ? ለምንስ ቢባሉ ምላሾት ምንድን ነው? መወያየት አይከፋም። ጊዜያት ይፍጅ እንጂ ከመልካም ውይይት መፍትሄም አይጠፋም ሕዝብ የለውጥ ጎርፍ ነው የሚባለውም ለዚህ ነው

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *