Hiber Radio: ወገን ወዴት እያመራን ነው-በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪዎች ሕንጻ ቤ/ክንን በጠራራ ጸሃይ በእሳት አጋዩ፣ በርካታ ንብረትም ዘረፉ

ቄስ አበረሃም ደስታና ጥቃት የደረሰበት የቤተ ክርስቲያን ንብረት
ቄስ አበረሃም ደስታና ጥቃት የደረሰበት የቤተ ክርስቲያን ንብረት

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ሕዝቡን በሀይል ለመግዛት አብይ ስልት ያለው ዜጎች አንዱ ያንዱን ሀይማኖትና ብሄር ሆነ ማንነት በጋራ አክብረው የሚኖሩበትን መሰረት ውስጥ ውስጡን ለመናድ መስራት ነው።በአደባባይ ጭምር አንዱ ሀይማኖት በሌላው አንዱ ማህበረሰብ ከሌላኛው ጋር ፍጥጫ ውስጥ እንዲገባ ሲሰራ ቆይቷል ዛሬም እየሰራ ነው። ሕዝቡ በአስተዋይነት በርካታ ችግሮችን እንደ ቀድሞው በሰላም አብሮ በመቆም ሲያሳልፋቸው ቆይቷል፡ አልፎ አልፎ በየቦታው የሚከሰቱ ችግሮች ግን መኖራቸው አልቀረም።በቅርቡ በኦሮሚያ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ተቃጥሏል።የቤተ እምነቶቹ ቃጠሎ በግልጽ ከሕዝቡ ጥያቄ ጋር የሚያገናኘው አልነበረም። በበርካታ ቦታዎች የታየው ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መብትን መጠየቅ ሲያልፍም የአገዛዙን የአውሬ እርምጃ በመቃወም የስርዓቱ ንብረት የሆኑ ተቋማት ላይ ጥቃት መሰንዘር የአልሞት ባይ ተጋዳይነት እርምጃዎች የእምቢ ባይነት ምልክቶች ናቸው። አልፎ አልፎ የሚሰሙት በሀይማኖት ተቋማትና ብሄር ላይ ያነጣጠሩት ጥቃቶች ከጀርባቸው ይህ ስርዓት መኖሩ የማያጠራጥሩ ምልክቶች ቢኖሩም ነገሩ በዚህ እንዳይቀጥል ሁሉም የሚመለከተው ወገን ቆም ብሎ ሊነጋገርበት፣ሊመክርበት የሚገባ ጉዳይ ነው። የዛሬውን ዘገባ ተከታተሉት።

በታምሩ ገዳ

“ሰዎች እንዴት ሰለ እነርሱ የቆመ እና ለእነርሱ የተገነባ ህንጻ ቤ/ክንን ያወድማሉ?”ቄስ አብረሃም ደስታ

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሆነ ሕንጻ ቤተክርስቲያን እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት በቅርቡ በምስራቅ የአገሪቱ አካባቢ ልዩ ስሙ መቂ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በአካባቢው ነዋሪዎች የድንጋይ ናዳ እንደወረደበት፣የመፈራረስ ጥቃት እንደገጠመው እና በስተመጨረሻም የዝርፊያ ተግባራት እንደደረሰበት ቄስ አበረሃም ደስታ ሰሞኑን “እርዳታ ለሜገባት ቤ/ክ እርዳታ” ለተባለ ድሀረገጽ መሪር ቅሬታቸውን እና ሃዘናቸውን ባለፈው መጋቤት 2/ 2016 ገለጸዋል።

እንደብጹነታቸው ገለጻ ከሆነ ባለፈው የፈረንጆቹ የካቲት 18/2016 “ብዛታቸው ወደ 55 የሚጠጉ ከተለያዩ የአለማት ክፍሎች የመጡ ክርስቲያን ወንድሞች እና እህቶች በአርብቶ አደሮች አካባቢ ሊደረጉ ሰለሚገባቸው እንክብካቤዎች ኮንፈረንስ በማካሄድ እና በመወያየት ላይ ሳሉ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሆኑ የሚገመቱ አዛውንቶች ፣ሕጻናት ፣ወጣቶች ፣ ወንዶች እና ሴቶች ሳይሉ “በጥላቻ መንፈስ በመነሳሳት” ህንጻ ቤተ ክርስቲያኑን በእሳት አጋይተዋል፣ ለአካባቢው ማሕበረሰብ ለአንድ አመት ይውል ዘንድ የተከማቸ 25ሺህ ፓውንድ እሩዝ፣ፓስታ ፣ስንዴ፣ለሙከራ ተግባር በትንሽ ስፍራ ላይ እንዲራቡ የተደረጉ ላሞችን እና ዶሮዎችን ፣ለማሕበረሰቡ ጥቅም የሚውሉ ከ250 በላይ አልጋዎችን ፣ ፍራሾችን ፣ከ700 በላይ ብርድ ልብሶችን፣የፍራሽ ሽፋኖችን ፣ማቀዝቀዣዎችን፣ልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ቴሌቭዥኖች ፣በነዳጅ ሃይል የሚሰሩ የሃይል መስጫዎች(ጄንሬተሮች)፣የፎቶኮፒ ማሽኖች የወሰዱ ከመሆናቸው በተጨማሪ የአካባቢው ማሕበረሰብን ጤነንት የሚንከባከቡ እና በተለይ አካለ ስንኩላን በሽተኞቻቸውን ጥለው “አንሄድም “ያሉ እህቶችንንም ንብርቶቹን ሁሉ እንዲያስረክቡ ከተነገራቸው በሁዋላ የ አገልጋይ እህቶቹን የግል አልባሳት ሳይቀር በመንጠቅ አይናቸው አያየ ከተከፋፈሉ በሁዋላ ከአካባቢው እርቀው እንዲሄዱ ጫና በመደረጉ በፈጣሪ እገዛ ወደ አጎራባች ከተማ ፣ሻሸመኔ ፣ለመሰደድ ተገደዋል ። “ ሲሉ ቄስ አብረሃም በሃዘኔታ ተናግረዋል። ለጊዜው በነዋሪዎቹ ጥቃት ያልደረሰበት ተቋም ቢኖር ቤ/ክርስቲያኒቱ ያሰገነባችው ትምህርት ቤት ብቻ ነው ተብሏል።

ቄስ አብረሃም አስተተያየታቸውን ሲያራዝሙ” በመቂ አካባቢ እድሜ ጠገብ የሆነው እና ትልቁ የጅግሳ ቤ/ክን ሰለ እነርሱ እና ለእነርሱ ተብሎ በተቋቋመላቸው እና ከ እኛ ጋር በጣም ቀረቤታ ባላቸው ተጠቃሚዎች/የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃት ደረሶበታል።እህቶቻችን እግዜ አብሔር በነጻ ከሰጣቸው ታላቁ ነፍሳቸው በቀር ሁሉንም ጥሬታቸውን አጥተዋል”ብለዋል።

ቄስ አብረሃም በሰተመጨረሻም ”ዛሬ አንድ ጥያቄ በልባችን እና በአይምሯችን ውስጥ ይብላላል እርሱም ፈጣሪ ለምን ይህን አይነቱን አሳዛኝ ችግር በእኛ ላይ አንዲፈጠር ፈቀደ?ጊዜ ይፍጅ አንጂ ፈጣሪ የራሱ ምላሽ እንዳለው ተሰፋ አናደረጋለን”በማለት ተሰፋ እና ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ምንም እንኳን አገዛዙ ሆነ የአካባቢው ሹማምንቶች ተከሰተ በተባለው አሳዛኝ እና አሳፋሪ ጉዳይ ዙሪያ የሰጡት የተቃውሞ ሆነ በሕገውጥ ተግባሩ ላይ የተሰማሩ ወገኖችን ለሕግ ሰለማቅረብ የ ወስዱት እርምጃ ሰለ መኖሩ እሰከ አሁን ድረስ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ይህ ኢ-ኢትዮጵያዊ ፣ኢ-ሀይማኖታዊ እና ኢ- ኢሰብ አዊ ድርጊት ነገ በሌላው አካባቢ በሌላው ማህበረሰብ እና በሌላው አማኝ ላይ ላለመከሰቱ ምን ዋስትና አልን? ብሎ መጠየቁ ግድ ይላል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *