ኢትዮጵያ 90 ከመቶ የዝሆን ሀብቷን ማጣቷ… አልሸባብ ለኢትዮጵያ የሰልላል ያለውን ወጣት በአደባባይ መግደሉ…

የአገዛዙ ጄኔራል ድንበር ተሻግረው ጋዜጠኛውን እገድልሃለው ሲሉ መዛታቸው… የሌንጮ ለታ ከኢትዮጵያ መግባትና መባረር የጋዜጠኛ በፈቃዱ ሞረዳ አስተያየት… ግብፅ በአባይ ውሃ የመጠቀም ታሪካዊ መብቴ አይለወጥም ስትል አቋሟን ዳግም መግለጿ… የመኢአድ 20 አባላት መታሰራቸውና ሌሎችም…

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 13 ቀን 2007 ፕሮግራም

<…የአቶ ሌንጮ ለታ አገር ቤት በገቡ በ24 ሰዓት ውስጥ መባረር ጥሩ ነው ። ሰላማዊ ትግል የሚባለው…ሁሉም በመረጠው መንገድ ሰላማዊ የሚለውም የትጥቅ ትግል የሚለውም አንዱ በአንዱ ላይ ድንጋይ አይወርውር…> ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ በቅርቡ ከኦሮሚያ ሚዲአ ኔትወርክ የለቀቀና ቀድሞ በአገር ቤት ትታተም የነበረችው የጦማር ጋዜጣ አሳታሚና ዋና አዘጋጅ የአቶ ሌንጮን አገር ቤት መግባትና ከአገር ቤት መውታት አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…የናይጄሪያ መንግስት በሟቹ የአገሪቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጄ/ል ሳኒ አባቻ ከተዘረፈውን መካከል ከአስራ ስድስት ዓመት በሁዋላ እያስመለሱ ነው …ከኢትዮጵያ ተዘርፎ የወጣው ሰላሳ ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል የተዘረፈውን ግን የማይጠይቁት ሌባ ሌባን ስለማያጋልጠው …> ዶ/ር አክሎግ ቢራራ ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ስለወጣው ገንዘብ ጠያቂ መጥፋቱ ላይ አነጋግረናቸው ከሰጡን ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡ)

ሩሲያንና አሜሪካን ጨምሮ ታላላቅ አገሮች ጋር የምትወዛገብበት የክሪሚያ ሕዝበ ውሳኔና ውህደቱን ተከትሎ የቀረቡ ተቃውሞዎች (ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

– አቶ ሌንጮ ለታ በኢትዮጵያው አገዛዝ የደህንነት ሀላፊ ትዕዛዝ ከአገር ተባረሩ

* የድርጅታቸው ሰዎች አቶ ሌንጮ የሚያናግራቸው ባለስልጣን ስለጠፋ ከአገር ወጥተዋል ሲሉ ገልፀዋል

– የኢትዮጵያው አገዛዝ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ወደ ኤርትራ ዘልቆ የአየር ጥቃት አልሰነዘረም

* በጥቃቱ ወደመ የተባለው የካናዳው የወርቅ ማዕድን ኩባንያ ፋብሪካው ስራውን እንዳላቋረጠ ገለጸ

– ግብፅ በአባይ ውሃ የመጠቀም ታሪካዊ መብቴ አይለወጥም ስትል አቋሟን ዳግም ገለፀች

– የግብፅ መግለጫ ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ ደርሰንበታል ካሉት ፊርማ ቀረሽ ስምምነት አደጋ ላይ ሳይጥለው አይቀርም

– የሶማሊያው አክራሪ ቡድን አልሸባብ ለኢትዮጵያ የሰልላል ያለውን አንድ ወጣት ሰሞኑን በአደባባይ ገደለ

– ኢትዮጵያ 90 ከመቶ የዝሆን ሀብቷን ማጣቷ ተነገረ

– በጋሞ ጎፋ በቅስቀሳ ላይ የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

* የባህር ዳር የፓርቲው ቢሮ በወከባና ማስፈራሪያ መዘጋቱ ተገለፀ

– የመኢአድ ከ20 በላይ አባላቱ ማዕከላዊን ጨምሮ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በእስር ላይ መሆናቸውን ተገለፀ

– የኢትዮጵያው አገዛዝ ጄኔራል ድንበር ተሻግረው እገድለሃለሁ እንዳሉት ጋዜጠኛው ገለጸ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *