Hiber Radio: ኢትዮጵያ የአሰብ እና የ ምጽዋ ወደብን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማጓጓዣ እንድትጠቀም ጥሪ ቀረበላት፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ የቃላት ጨዋታውን ትቶ በኦሮሚያ የሕዝቡን ሰላማዊ ጥያቄ ተከትሎ የገደሉትን ለፍርድ እንዲያቀርብ የታሰሩትን እንዲፈታ ጠየቁ፣ተቃዋሚዎች ተባብረው መቆም ያለባቸው ወሳኝ ወቅት መሆኑን ገለጹ፣በኦሮሚያ ተቃውሞው ቀጥሏል፣ በመላው ዓለም በሚደረጉ ሰልፎች የአገዛዙ አፈና ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ቀረበ፣በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚማቅቀው “የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሄት አዘጋጅ የእስራት ቅጣት ተበየነበት፣በመርካቶ በርካታ ሱቆች ሕገ ወጥ ሞባይልና ዕቃ አስገብታችሁዋል በሚል በዘመቻ ታሸጉ፣በኦጋዴን ውስጥ በኢሕአዲግ፣ በቻይና እና በጅቡቲ መካከል የተፈረመው ግዙፍ የነዳጅ ፕሮጀክት ከአካባቢው ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፣መንግስታቱ ከኦጋዴን ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ተጠይቋል እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር መረራ ጉዲና፣ከአክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስና ኦባንግ ሜቶ ጋር፣በአፍሪካዎ የሰብኣዊ ፍርድ ቤት መንግስት ላይ 150 ሺህ ዶላር እንዲቀጣ ስላስፈረደችው ተበዳይ ኢትዮጵያዊቷ ወይንሸት ዘበነ ልዩ ጥንቅርና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 4 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…አሁን መንግስት የያዘው የሰራውን ሰርቶ መልሶ ስህተቱ ይሻሻላል የሚል በተለይ ፕሬዝዳንት ኦባማ መጥተው ከሄዱ በሁዋላ የያዙት ፈሊጥ ነው። አሁን እግዜርም ቢመጣ ሕዝቡ ኢህአዴግን አያምንም። በኦሮሚያ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት ከፈለጉ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ፣የታሰሩት ይፈቱ ካልሆነ ይሄን ቀልድ አቁሞ ወደ እውነተኛ ብሄራዊ እርቅ መምጣት ያስፈልጋልእዚህ አገር ውስጥ ምርጫ ቦርድ ዘጠና ምናምን  ፓርቲዎች አሉ ይላል  ያው ከታወቁት ጥቂት ተቃዋሚዎች በስተቀር ብዙዎቹ የመንግስት ቅልቦች ናቸው ከእነዚህ ይልቅ ወሳኝ መፍትሄ ማምጣት የሚችሉት እውነተኞቹ ተቃዋሚዎች ከኢህአፓና መኢሶን ጀምሮ ባለፉት አርባ ዓመታት ያላለፉት ፈተና ተባብሮ መቆም ላይ ነው።ዛሬም…>

/ መረራ ጉዲና የኦፌኮ ሊቀመንበር በአቶ ሀይለማሪያም በኦሮሚያ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ለፓርላማ ላቀረቡት አስተያየት ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ስርዓቱ የሚፈልገው ተነጣጥለን ቆመን ለመምታት ነው። አሁን እየተሳካለት አይመስለኝም። በአገር ውስጥም በውጭም ኢትዮጵያውያን በጋራ አንድ ላይ እየቆሙ ነው። በሲያትል በአገር ቤት በኦሮሞ  ወገኖቻችን ላይ የተወሰደውን ግፍ በመቃወም የተጠራው ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያውያን አንድ መቆማችን በአንድ ላይ መጮሃችን ነው የታየው እኔም በወቅቱ ያደረኩት ንግግር ይሄንን ስርጫት ተነጣጥለን ሳይሆን በአንድ ላይ እንድንጥለው በአንድ ላይ እንነሳ የሚል ጥሪ ነው ።ጥሪውን እኛ ያደረግነው በአንድ ላይ ሁላችንም ተወያይተን በጋራ ድምጻችንን ለማሰማት ነበር። ያን አድርገናል ትብብራችን በአንድ ላይ መቆማችን በዚህ አያበቃም ሕዝባችንን እየገደለ እያጠፋ ያለውን ስርዓት በጋራ መጣል ያስፈልጋል …>>

 

አክቲቪስትና  የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል  ሙሉነህ ዮሐንስ በሲያትል ባለፈው አርብ በአገር ቤት በኦሮሞ ወገኖቻችን እና በሌሎቹም ላይ የሚደረገውን ግድያ በመቃወም የተደረገው ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ያደረገውን ንግግር መሰረት አድርገን   ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በሙርሲ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አስነዋሪ አያያዝ፣ግድያ፣አፈና ላይ ሕዝቡ ከዳር እስከዳር ተቃውሞውን በልዩ ልዩ መንገድ መግለጹ አስደሳች ነው።እነዚህ ሰዎች በሁሉም ቦታዎች ለሚፈጹሙት ግፍ ግድያ ተጠያቂ መሆን አለባቸው። ይህን ለማድረግ ተባብረን ጠንካራ ስራ መስራት አለብን…የኢህአዴግ ኤምባሲ አምባሳደር ግርማ ብሩ ወረቀት ጽፎ፣የጉዞ ይለፍ አዘጋጅቶ ከዚህ አሜሪካ ከታሰሩበት ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ያደረጋቸውን ዘጠኙን ኢትዮጵአውያን ልንደርስላቸው አልቻልንም።እናዝናለን ግን አሁን የቀሩ አራት አሉ እነሱንም ሆነ ወደፊት ሌሎቹ እንዳይላኩ ማድረግ አለብን የጋራ ስራ አለ አንን ጀምረናል ሁሉም የራሱን አስተዋጽዎ ማድረግ አለበት…>

አቶኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቱ ኢትዮጵአ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ከአሜሪካ የህወሃት ኤምባሲ ጽፎ ወደ አገር ቤት ስለወሰዳቸው ስደተኞችና በሙርሲዎች ላይ የስኳር ልማት በሚል ስለሚደርሰው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ተጠይቆ ከሰተው ምላሽ(ሙሉውን ያድምጡ)

ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስትን በአለማ ቀፍ የፍትህ አደባባይ የረታቸው እና ትምህርት የሰጠችው የወሲብ ተጠቂዋ ወይንሸት ዘበነ   ሰሞነኛ ውሎ ሲዳሰስ ( ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያ የአሰብ እና የ ምጽዋ ወደብን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማጓጓዣ እንድትጠቀም ጥሪ ቀረበላት

ዶ/ር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ የቃላት ጨዋታውን ትቶ በኦሮሚያ የሕዝቡን ሰላማዊ ጥያቄ ተከትሎ የገደሉትን ለፍርድ እንዲያቀርብ የታሰሩትን እንዲፈታጠየቁ

ተቃዋሚዎች ተባብረው መቆም አለባቸው ወሳኝ ወቅት መሆኑን ገለጹ

በኦሮሚያ ተቃውሞው ቀጥሏል በመላው ኣለም በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች የአገዛዙ አፈና ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ቀረበ

በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚማቅቀው “የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሄት አዘጋጅ የእስራት ቅጣት ተበየነበት

በመርካቶ በርካታ ሱቆች ሕገ ወጥ ሞባይልና ዕቃ አስገብታችሁዋል በሚል በዘመቻ ታሸጉ

ሶማሊያ ውስጥ ስልጠና ወስደዋል የተባሉ በርካታ ሰዎች ሰሞኑን   በጸረ-ሽብሩ ህግ ሽፋን አ/አ ውስጥ የከባድ ቅጣት ሰለባዎች ሆኑ

በኦጋዴን ውስጥ በኢሕአዲግ፣ በቻይና እና በጅቡቲ መካከል የተፈረመው ግዙፍ የነዳጅ ፕሮጀክት ከአካባቢው ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፈተኛ ተቃውሞ ገጠመው

“የቻይና እና ጅቡቲ መንግስታት እጆቻቸውን   ከኦጋዴን ሕዝብ ሃብት ላይ ባሰቸኳይ ያንሱ”ተቆርቋሪ ድርጅቶች

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል።

ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-031316-032016

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *