Hiber Radio: በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋምና አገሪቱን እንዲታደጋት አንድ የተቃዋሚ መሪ ጠየቁ፣በእስራኤል የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን በቴላቪቭ መንግስት ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ወጡ፣ ሁለት የጅቡቲ የጦር ምርኮኞች ከኢርትራ እስር ቤት አምለጠዋል፣13 እስረኞችም በኢርትራ ማጎሪያ ቤት ይገኛሉ ተብሏል ፣የኢትዮጵያው አገዛዝ ይምጡልኝ ብሎ አልቀበላቸውም ብሎ የመለሳቸው አራት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በመጪው አርብ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ፣ምዕራባዊያን አገራት እና ለጋሾ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዊ መብት ረገጣ ችላ እንዳይሉ ተጠየቁ የሚሉና ቃለ መጠይቅ ከሕጋዊው መኢአድ ፕሬዝዳንት፣ከድምጻዊ ዳዊት መኮንን(አኑፌን ጂራ)፣ከወልቃይት ጠገዴ የልሳነ ግፉአን ድርጅት ተጠሪ እና ልዩ ወቅታዊ ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 11ቀን 2008 ፕሮግራም

<…ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ እጅግ አደገኛ ነው።ለውጥ እንዲመጣ የሚሰራው ተቃዋሚ የግድ በጋራ መምከርና በአንድ ላይ መቆም ያለበት ወሳኝ ወቅት ነው። መንግስት ገድዬ አስሬ ሕዝቡን ጸጥ አደርጋለሁ የሚለው የሚቻል አይደለም። ሕዝቡ ከተባበረ መሳሪያ የያዘውም አልተኩስም የሚልበት ጊዜ ይመጣልተቃዋሚዎች በትላንትና ጉዳይ መጨቃጨቅ ወደሁዋላ መሄድ የለባቸውም ወደፊት የአገሪቱን ህልውና ለማቆየት ተነጣጥሎ ሳይሆን ሁሉም በጋራ አንድ ላይ መቆም አለበት ይሄ ካልሆነ ግን የጋራ አገር … >

አቶ ማሙሸት አማረ ሕጋዊው የመኢአድ ፕሬዝዳንት በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳይ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ   (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ወሰኔን የማያውቅ አለ? ወሰኔም አምቦ ገላ ገልገላም የቆዩ የሕዝብ ዜማዎች ናቸው እኔ እንደገና ዘፈንኳቸው። ኦሮሞ አንድን ነገር አለምክንያት አይናገርም አምቦ ሲመሻሽ ይላልሕዝብ ከሕዝብ ጋር ተጋጭቶ አያውቅም የሚያጋጩት ስርዓቶች ናቸው። እነሱ እርስ በእርስ ለማጋጨት የቤት ስራ ሰጥተውናል የነሱን የቤት ስራ ወደ ጎን …>>

ድምጻዊ ዳዊት መኮንን(አኑፌን ጂራ) ስለአዲሶቹ ዜማዎቹ እንዲያወጋን ካብዘነው    ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ላይ የሕወሃት አገዛዝ የከፈተው የዘር ማጥፋት ወንጀል ወደር የለውም  የዛሬውም በጠለምት የተነሳው ተቃውሞ በሕጋዊ መንገድ የህዝቡን ጥያቄ ለማቅረብ ከተነሱ ኮሚቴዎች ውስጥ የወጣት ሉላይን ታፍኖ መወሰድን በመቃወም ነው እነሱ ከትግራይ አምጥተው ያሰፈሯቸው እና ያስታጠቋቸው ወደላይ ከሕዝቡ ፊት ተኩስ ከፈቱየትግራይ ነጻ አውጪ ለመሬት መስፋፋት ሲል በወልቃይት ላይ የሚያደርሰውን ግፍ ለማዳፈን ጥያቄውን አልቀበልም ብሎ ከዚህ ቀደም ከትግራይ አምጥቶ ካሰፈራቸው ስድት መቶ ሺህ ሰፋሪዎች በተጨማሪ ሰማ አምስት ሺህ አሁን አምጥተው ሪፈረንደም እናደርጋለን ይላሉ ይሄ ተቃባይነት የለውም …>

አቶ ቻላቸው አባይ የወልቃይት ግፉአን ማህበር ተጠሪ በአሁኑ ወቅት በጠለምት የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ አስመልክቶ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ከሰጡን ምላሽ( ሙሉውን ያዳምጡ)

በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የተወሰዱ የመብት ረገጣዎችን የዳሰሰ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ሲዳሰስ(ልዩ ጥንቅር)

የዲሞክራቲክ ኮንጎን ምስቅልቅል ለመቀየር ገንዘባቸውን እና ራዕያቸውን በመሰነቅ ከአሜሪካው የኮለራዶ ግዛት ወደ አገራቸው ለመግባት የቆረጡት ቱጃር መጻኢ ውጥን እና ምኞት ሲቃኝ (ልዩ የዜና ዳሰሳ)

( ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ ውስጥ  ሁሉንም  ወገኖች ያካተተ  የሽግግር መንግስት  እንዲቋቋምና አገሪቱን እንዲታደጋት አንድ የተቃዋሚ መሪ ጠየቁ

በእስራኢል የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን በቴላቪቭ መንግስት ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ወጡ

ቀለማችን ቢለወጥ ኖሮ ይህ ሁሉ በደል እና ግፍ አይደረሰብንም ነበርየህግ አረቃቂዎች

ሁለት የጅቡቲ የጦር ምርኮኞች ከኢርትራ እስር ቤት አምለጠዋል፣13 እስረኞችም በኢርትራ ማጎሪያ ቤት ይገኛሉ ትብሏል

የኢትዮጵያው አገዛዝ ይምጡልኝ ብሎ አልቀበላቸውም ብሎ የመለሳቸው አራት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በመጪው አርብ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

 በሶማያ የሚገኝው የኢትዮጵያ ጦር የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥመው ተሰግቷል፣አለማቀፉ ማህበረስብ ችግሩን እንዲቀረፍ ጥሪ ቀረቧል

ምእራባዊያን አገራት እና ለጋሾ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለውን የሰበዊ መብት ረገጣ ችላ እንዳይሉ ተጠየቁ

ርሃቡን በቁጥጥር ስር እንዳረጋለን ያሉት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ አለማቀፉ ማህበረሰብ ካልደረሰልን ሁኔታዎች ይከፋሉ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ

<<ወሬ ብቻውን ፋይዳ የለውም>> አቶ ሃይለማሪያም ለአለማቀፉ ማህበረሰብ የላኩት ሰሞነኛ መልእክት

ፕሬዝዳንት ኦባማ አገራቸው ከወራት በፊት ከአሸባሪነት መዝገብ ስሟን ወዳወጣቻት ኩባ ከነቤተሰባቸው ተጉዋዙ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል።

ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-032016-032716

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *