Hiber Radio: ኢትዮጵያን የዛሬው አገዛዝ ሶሪያ ሳያደርጋት ሕዝቡ በጋራ የተሻሉ አማራጮችን አሁኑኑ እንዲያዘጋጅ ተጠየቀ፣እስራኤል ለኢትዮጵያና ለኤርትራ የጦር መሳሪያ ማቅረቧ ተገለጸ፣ ኮ/ል መንግስቱ ሀ/ይለማሪያም ለፍርድ እንዲቀርቡ ዓለም አቀፍ ጥሪ ቀረበ፣ የኦሮሞ ሕዝብ በኦህዴድ አገዛዝ ራሱን አስተዳድሮ እንደማያውቅ አንድ ምሁር ሰሞኑን ተናገሩ፣በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞውን ተከትሎ ተደብድቦ ታሞ የነበረ ተማሪ ሕይወቱ አለፈ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የቀሩ ዋና ዋና አመራሮችን አገድኩ ያለው የስነስርዓት ኮሚቴ ሕገ ወጥ ውሳኔ ታገደ፣ ሕወሓት የአማራ ሕዝብን በጎሳ ለመከፋፈል የጀመረውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በድብቅ ያሰራጨው ሰነድ ተጋለጠ፣የቅማንት ጉዳይ የሕወሓት ዋና አጀንዳ መሆኑን በተዘዋዋሪ ሰነዱ አጋልጧል፣በሙስና የተዘፈቁት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማን ከስልጣን ለማውረድ የአገሪቱ ፓርላማ ማክሰኞ ለውሳኔ ሊቀመጥ ነው የሚሉና ሌሎችን ዜናዎች ጨምሮ የበዕውቀቱ ስዩም ከአሜን ባሻገር ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የጻፈውን በድምጽ ያነበበው፣ቃለ መጠይቅ እና ሌሎችም አሉን

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

   የህብር ሬዲዮ መጋቢት 25 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…አሁን ባለው መንግስት የፖለቲካና የተዛባ የኢኮኖሚ አስተዳደር ሳቢያ በዚሁ ከቀጠለ አገሪቱ የመፈራረስ አደጋ አጋጥሟታል። ይህን አደጋ የምናስቀረው እኛው ነን…በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እኔ በጉልበት ካልገዛሁ አገሪቱ እንደ ሶሪያ ትሆናለች ሲል እኔ ስልጣን ካጣሁ ሶሪያ አደርጋታለሁ ማለቱና አንድ አደገኛ አማራጭ ብቻ ሰጥቶናል እኛ ነን ለአገራችንና ለሕዝባችን ሁለት ሶስት የተሻሉ አማራጮች አሁኑኑ ማዘጋጀት ያለብን። መንግስት አሁን የሚያደርገውን ጥፋት ከማድረግ አይመለስም።እኛ ግን ዛሬውኑ… >

ዶ/ር አባድር መሐመድ ኢብራሂም የሕግ ባለሙያና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች በሚኒሶታ ከተደረገው የኢትዮጵያ ፍትሐዊና ርትዓዊ ጉባዔ በሁዋላ ስለ ጉባዔው ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<…የኢትዮጵያ ህሕብ እርስ በእርሱ አልተጣላም ስርዓቱ ግን መደማመጥ እንዳይችል ለጋራ ችግር የጋራ መፍትሄ እንዳይፈልግ እያደረገ ነው። የጎዳን የስርዓቱ ጥንካሬ አይደለም የእኛ በጋራ አለመቆም ነው…ሕዝቡ አንድ ላይ እንዲቆም ተቀራርቦ እንዲነጋገር እየተራዘመ ያለውን ሰቆቃ በጋር እንዲታገል መተማመንና መነጋግ አለበት ዛሬ ይሄን ጀምረናል በየቦታውም ይሄ ይቀጥላል። ለመተማመን መነጋገር አለብን። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን…>

አቶ ነጌሶ ዋቀዮ የኢትዮጵያ ፍትሐዊና ርዕታዊ ጉባዔ መስራችና የጉባዔው ተናጋሪ ስለ ጉባዔው በጋራ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የመጨረሻው ምሳ- ወጣቱ ባለቅኔና ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም(ከአሜን ባሻገር ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የጻፈውን ምዕራፍ የተመስገን ደሳለኝን የልደት ቀን ምክንያት በማድረግ በድምጽ አንብቦታል-ያዳምጡት)

 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ይመስል ሕይወታቸውን እየገበሩ አሰተዋሽ ያጡት የሶማሊያ ወታደሮች ወቅታዊ እሮሮ እና ምሬት(ልዩ ዘገባ)

ከአሜን ባሻገር በኢትዮጵያውያን መካከል በሀሰት የተጫረውን ዘርን መሰረት ያደረገ የጥላቻ ቅስቀሳ በታሪክ ማስረጃ ባዶ ያስቀረ ነው። ሕዝብን በፍቅር ለማቀራረብ የተጋ ፣ነገ ሊመጣ የሚችለውን ችግር ዛሬ ላይ ለማስቀረት የሚጥር ታላቅ መጽሐፍ ነው። ዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገም ከነገ ወዲያም የሚነበብ ነው።ለነገዋ ለሁሉም እኩል የምትሆን ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መምጣት ምኞቱ የሆነ የዛሬው አስከፊ ጊዜ እንዲለወጥ የሚፈልግ ሁሉ በጥሞና ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው። ህብር ሬዲዮ

ቃለ መጠይቅ በቬጋስ ሁበርን ሲያሽከረክር ጉዳት ስለደረሰበት አሽከርካሪ ከአቶ ስሜነህ ጸጋዬ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት)ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያን የዛሬው አገዛዝ ሶሪያ ሳያደርጋት ሕዝቡ በጋራ የተሻሉ አማራጮችን አሁኑኑ እንዲያዘጋጅ ተጠየቀ

እስራኤል ለኢትዮጵያና ለኤርትራ የጦር መሳሪያ ማቅረቧ ተገለጸ

ኮ/ል መንግስቱ ሀ/ይለማሪያም ለፍርድ እንዲቀርቡ ዓለም አቀፍ ጥሪ ቀረበ

ሕዝቡ ዛሬም ኮ/ል መንግስቱ አገር ወዳድና አምባገነን ናቸው በሚል ያስታውሳቸዋል

የኦሮሞ ሕዝብ በኦህዴድ አገዛዝ ራሱን አስተዳድሮ እንደማያውቅ አንድ ምሁር ሰሞኑን ተናገሩ

በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞውን ተከትሎ ተደብድቦ ታሞ የነበረ ተማሪ ሕይወቱ አለፈ

የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የቀሩ ዋና ዋና አመራሮችን አገድኩ ያለው የስነስርዓት ኮሚቴ ሕገ ወጥ ውሳኔ ታገደ

ሕወሓት የአማራ ሕዝብን በጎሳ ለመከፋፈል የጀመረውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በድብቅ ያሰራጨው ሰነድ ተጋለጠ

የቅማንት ጉዳይ የሕወሓት ዋና አጀንዳ መሆኑን በተዘዋዋሪ ሰነዱ አጋልጧል

ኤርትራ ዘጠኝ የፊሊፒን ዜጎችን ሰሞኑን በቁጥጥር ስር አዋለች

በሙስና የተዘፈቁት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማን ከስልጣን ለማውረድ የአገሪቱ ፓርላማ ማክሰኞ ለውሳኔ ሊቀመጥ ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-040316-041016

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *