Hiber Radio: በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከ2.2 ሚሊዮን በላይ ህጻናትን ለከፋ አደጋ መጣሉ አለማቀፋዊ ሰጋት ፈጥሯል፣ በአዲስ አበባ ለማህበር ጽዋ የተሰባሰቡ የኦሮሞ ወጣቶች ኦነግ ልኳችሁ መንግስትን ልትወጉ ነበር ተብለው ክስ ቀረበባቸው፣ ኦነግ ጉዳዩ የወያኔ የፈጠራ ክስ ነው የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ በዚህ ማዳፈን አይቻልም ሲል ምላሽ መስጠቱን ጨምሮ ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 2 ቀን 2008 ፕሮግራም

<… በድርቁ ከሰቆጣ ተሰደው በደብረ ብርሃን የሚገኙትን በአምስት መኪና ጭነው ብዙዎቹን ወደ መጡበት መልሰዋቸዋል። ድርቁ ጎድቷቸዋል ወገኖቻችንን ተጎሳቁለው አፈር መስለው ማየት ይረብሻል ይሄ ሳያንሳቸው አትለምኑ ብሎ በፖሊስ ማሳደድ ግን ምን አይነት… >

አቶ አበበ ውቤ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ በደብረ ብርሃን በድርቁ ሳቢያ ተሰደው ከሰቆጣ የመጡትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አይቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ     (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ለማህበር ተሰበሰቡ ሰዎችንም ሆነ ሀሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ አደባባይ ወጥተው በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን በደል የሚቃወሙትን ኦነግ አስታጥቋችሁ መንግስት ልትወጉ ነው ማለት የወያኔ ሸፍጥ ነው። ወጣቶቹ የወገናቸው ብሶት ቆጭቷቸው ለመብታቸው የተነሱ ናቸውየኦሮሞ ሕዝብ ለመብቱ መቆምን  የወያኔ ጥይት፣እስር ሆነ  የፈጠራ ክስ አያቆመውም አንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ ቢል እንኳ መስዋዕትነቱን ከፍሎ ለነጻነቱ የሚያደርገው ትግል ይቀጥላል ተዳፍኖ የሚቀር አይደለም ትግሉን ሌላውም ሊቀላቀለው ይገባል።የተቃዋሚ ድርጅቶችም …>>

አባ ጫላ ለታ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በአገር ቤት ባለፈው ሀሙስ ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ስለተመሰረተባቸው የኦሮሞ ሰላማዊ ታጋዮች ላይ በመንግስት ላይ ጦርነት ልትከፍቱ  ነበር ስለተባለባቸው ክስ ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የግንቦት 7 አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የመን ላይ አፍኖ ለወሰደው የኢሃ አዲግ መንግስት የደህነነት ሰራተኞችን ለማጠናከር  ከሎንዶን መንግስት  የሚጎርፈው የገንዘብ እርዳታ  በተመለከተ  የእንግሊዝ መንግስት፣የሰበዊ መብት  ተሟጋቾች እና የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት የሰጡት አስተያየትን ያካተተው   ታዋቂው የእንግሊዝ ጋዜጣ ( ስንድየ  ሚይል ) ያወጣው ወቅታዊ  ዘገባ ሲዳሰስ (ልዩ ሬፖርታዥ)

ከአፍሪካ አገሮች እስከ ምዕራባውያን አገሮች የተዘረጋው ዓለም አቀፍ የጉቦ የማቀባበል ቅሌትና ግንባር ቀደም ተጠያቂው ዩኒ ኦይል ኩባንያ ገበና ሲፈተሽ (ልዩ ጥንቅር)

<…ከሰቆጣ የመጣነው ረሃቡ አሰድዶን ነው። አሁን ወደ ሰቆጣ ካልሄዳችሁ ያሉት ለሁለት ወር ለአንድ ቤተሰብ አስራ ሁለት ጣሳ እህል ዕርዳታ እንሰጣለን ከዚያ ውጭ የለም ብለዋልእምቢ ብለን ያልሄድነው አሁን በደብረ ብርሃን ሚስቶቻችን ወጥተው እንዳይለምኑ ፖሊስ እያሳደደድ ነው። ትታሰራላችሁ ብለው ያባርሩናል ችግር ላይ ነው ያለነው…> አቶ ይትባረክ ጻድቁ ከድርቁ ተፈናቃዮች አንዱ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ ምልልስ በከፊል(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ 2.2 ሚሊዮን በላይ ህጻናትን ለከፋ አደጋ መጣሉ አለማቀፋዊ  ሰጋት ፈጥሯል

በአዲስ አበባ ለማህበር ጽዋ የተሰባሰቡ የኦሮሞ ወጣቶች ኦነግ ልኳችሁ መንግስትን ልትወጉ ነበር ተብለው ክስ ቀረበባቸው

የኦነግ ጉዳዩ የወያኔ የፈጠራ ክስ ነው የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ በዚህማዳፈን አይቻልም ብሏል

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በስልጣን ኮርቻ  ላይ መቆየት ከፈለጉ የባህሪይ ለውጥ እንዲያሳዩ አንድ የአውሮፓ ህብረት የሕዝብ አንደራሲዎች መሪ ሰሞኑን ተግሳጻዊ ምክር  ሰጧቸው

ከኤርትራ የከዳው ሞላ አስግዶም መቀሌ ሙስና ሰፈር ላይ ሕወሓት ኢንቨስተር አድርጎ ቦታ መስጠቱ ተገለጸ

የኬኒያ  አየር መንገድ ፓይለቶቹን ለኢትዮጵያ  አየር መንገድ በተውሶ አሳልፎ ለመስጠት መወሰኑ  የናይሮቢ ነዋሪዎችን አነጋገረ

ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቁ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች  ኬኒያዎችን አባረው መሬት  መቆጣጠራቸው ተዘገበ

/ ነጋሶ ጊዳዳ የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ የሚል አዲስ የታሪክ መጽሐፍ ጻፉ

የዙምባብዊው / ሮበርት ሙጋቤይሞታል ብላቸሁ በመመኘታቸሁ አፈርኩባችሁበማለት ተተኪዎቻቸውን በነገር ሸነቆጧቸው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 30 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-041016-041716

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *