Hiber Radio : ኢትዮጵያዊያንን በግፍ የገደለው አይሲስ ሶማሊያ ውስጥ አየተንቀሳቀሰ መሆኑ ይፋ ሆነ፣“የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ማንም ሊያስተምራቸ በጭራሽ አይችልም”ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ

isis-beheads-ethiopians-in-libya-01

በታምሩ ገዳ

የዛሬ አንድ አመት በሊቢያ በርሃ እና የባህር ዳርቻው ላይ 30 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻቸንን የኢ/ኦ /ተ/ ቤ/ክ እምነታቸውን እንዲ ቀየሩ አሊያም ሞት እንደሚ ጠብቃቸው ዛቻ ቢደርባሳቸውም “ ሃይማኖታችንን በጭራሽ እንቀይረም ” በማለታቸው “ አንገታቸውን ለአክራሪው ቡድን ሰይፍ ፣ ግንባራቸውን ደግሞ ያለ ፍርሃት ለጥይት በመሰጠት እጀግ ዘገናኝ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በማህበራዊ መገናናዎች መሰራጨቱን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኖች ከዳር እሰከዳር በተለይ ደግሞ የሟቾቹ ቤተሰቦች ልባቸውን የሰበረው ያ የክፈለ ዘመናቸን የሰማእትነት ጽዋን እንዲከፈሉ ያድረጋቸው እራሱን የእስላማዊ መንግስት (Islamic State) በማለት የሚጠራው ፣ነገር ግን ፍጹም ሃይማኖታዊ እና ሰብ አዊ አስተምሮት የማይከተለው ቡድን የመሰፋፋት አድማሱን በመቀጠል ሰላም እና መረጋጋት በራቃት በጎረቤታቸን በሶማሊያ ውስጥ የእኩይ ተግባሩን እንቅስቃሲ መጀመሩን የሚያሳይ መረጃ ሰሞኑን ይፋ ሆኗል ።

ዋርካድ የተባለውን ድህረ ገጽ ዋቢ ያድረገው የ ቻይናው የሲሲቲቪ የአፍሪካ ፕሮግራም ሰሞኑን ከሞቃደሾ/ሶማሊያ እንደዘገበው ምንም እንኳን የአገሪቱ /የማሊያ መንግስት ማረጋገጫ ባይሰጥበትም የአሲስ የመጀመሪያ በሆነው የፕሮፓጋንዳ የምስል መረጃው ላይ ቀደም ሲል የ ሶማሊያው የአልሸባብ አዋጊ/ኮማደር የነበረው እና ባለፈው አመት አይሲስን መቀላቀሉ በፑንትላንድ አካባቢ መኖሩ የሚነገረለት ሺክ አብዱቃድር ሙመን ለአይሲስ አባላት “እናንተ የተመረጣችሁ ናችሁ”የሚል የሙገሳ እና የእንኳን ደህና ምጣቸሁን አቀባበል ሲያድረግላቸው በምስሉ ላይ ያሳያል። ይህ መቼ ?እና የት ቦታ ?የሚለውን የጋዜጠኝነት መጠይቆችን ለጊዜው ያልመለሰው የ አይሲስ የፕሮፓጋንዳ መረጃ በሶማሊያ ባለሰልጣናት እይታ “ሁሉንም አሸባሪዎችን እናወቃቸዋለን ፣እንጨፈልቃቸዋለን ” የሚል ምላሽ ቢኖርም በርካታ የመቋደሾ ነዋሪዎችም በተለይ ወጣቱ ክፍል ልብ ለማማለል እና ወደ ሽብር ተግባር እንዲ ገቡ ለማድረግ የተወጠነ ተራ ፕሮፓንጋንዳ ነው”የሚል ትርጓሚ ቢኖረውም ይህ ስድስት ደቂቃዎች የማይበልጠው ቪዲዮ ለአካባቢው እና ለተጎራባች አገራት ሰጋት መፈጠሩ አይቀሬ ነው ሲል ሲሲቲቪ ከመቋደሾ ዘግቧል ።

 

በመካከለኛው ምስራው እና በሰሜን አፍሪካ /ሊቢያ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ሃይማኖት የለሹ የአይሲስ ቡድን በተመሳሳይ ወር እዚያው ሊቢያ ውስጥ 21 የግብጽ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በግፍ ማራዱን ተከትሎ ካይሮ በ አሸባሪው ቡደን ላይ ተከታታይ የአየር ላይ ድብደባ መፈጸሟ አይዘነጋም። በርካታ ኢትዮጵያዊያን በወቅቱ ምሬታቸውን እና ቁጭታቸውን በአገራቸው ውስጥ ወደ አደባባይ ወጥተው ለመግለጽ እንኳን የደረሰባቸው ወከባ ፣ግፍ እና መከራ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

አይሲስ በሶማሊያ ውስጥ በሚገኙት የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ጦር ሃይል ላይ ሰሞኑን ጥቃት መፈጸሙን ቢናገረም የሰላም አሰከባሪው ባለሰልጣናት ግን ዘገባውን ያሰተባብላሉ። በጎርቤት ሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አፍቃሪ አልቅይዳ እንደሆነ የሚነገርለት የሶማሊያው አልሽባብ ም ቢሆን ከሰላም አስከባሪው ጦር የሚደርሰብት ብርቱ ጥቃትን መቁቋም ባለመቻሉ ከ ገጠራማዎች ቀበሌዎች ይልቅ ብዙ ህዝብ በሚኖርበት የመቁደሾ ከተማ እና በሰላም አስከባሪው የጦር ሰፈሮች ላይ የጥቃት ሙከራ ለማድረግ መሰናዳቱን መረጃዎች ይገልጻሉ። ከኢትዮጵያ ጨምሮ ወደ 22 ሺህ የሚጠጉ የሰላም አሰከባሪ ሃይል የሰፈረባት ሶማሊያ ሰላሟ እና ደህነነቷ የተነጠላጠለው በእነዙሁ የጎረቤ ት እና ባእዳን ሃይሎች ላይ መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ።

ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ ዜና በአሁኑ ወቅት በቀጠናው ውስጥ እየተሰፋፋ የመጣው ሰወዲ አርቢያ ሰራሽ ( በሺክ በእብዱል ዋሃብ ትምህርት እና በስወዲ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች አማካኝነት ) አንደተቋቋ መ የሚነገርለት የ ወሃቢዘም አደገኛ አቅጣጫ እንዳለው በጉዳዩ ዙሪያ ሰፊ ጥናት ያድረጉት በቀድሞው መንግስት በእርዳታ ማስተባበሪያ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ (ኮሚሽነር የነበሩት ) ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ አሰጠነቀቁ ።”የወሃቢዝም በአፍሪካ የወረራ አቅጣጫ” (The Wehabi Invasion of Africa) የሚል ሰፊ ጥናት ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ማድረጋቸውን ለአሜሪካ ራዲዮ የአማሪኛ ው ከፍል ባለፈው ቅዳሜ የገለጹት ሻለቃ ዳዊት ሺያት፣ ሱኒያ የሚባሉት የ እልምና አመለካከቶች ከነብዩ መሃመድ መሞት በኋላ ተከታትለው የመጡ አንጋፋ እስተምረቶች መሆናቸውን እና የሙስሊሙ ማህበረሰብም ሊከተላቸው እንደሚገባ ጠቀሰው ፣በተቃራኒው ደግሞ የሙስሊም ወንድማማቾች Muslims Brothers Hoods)፣ሳላፊስት እና ወሃቢዛም የዘመናቸን እና የተለየ የአስተምሮት ወጤቶች መሆናቸውን ስይገልጹ አላለፉም ። አነዚህ ዘመን አመጣሻ አስተምረቶች በአብዛኛው ፖሊቲካ ዘመም መሆናቸውን ያወሱት ሻለቃ ዳዊት ለአክራሪዎቹ የእምነት አራማጆች አልቃይዳ፣ አይሲስ መሰረቾቹ ዋሃቢዝም እንደሆነ እስምረውበታል።

የሰውዲ አረቢያ የዋሂብዝም ፍልስፍና በኢትዮጵያ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ መሰፋፋቱን የጠቀሱት ሻለቃ ዳዊት የወቅቱ የአገሪቱ ገዢ መንግስት(ኢህ አዲግ) በማንኛውም ሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት የገለጹ ሲሆን ፣ይሁን እንጂ “ምናልባት አንድ የውጪ አገር በፖለቲካው ውስጥ ተጽእኖውን ለማሰረጸ ጥረት ካደረገ የመንግስት ጣልቃ ገብነት አሰፈላጊ ሊሆን ይችላል። ከዚያ ወጪ ግን ሙስሊሞች እንደ ሌሎቹ የእምነት ተከታዩች ያለ መንግስት ጥልቃ ገብነት ፣በነጻ ሊንቀሳቀሱ ፣ ያሽቸውንም ሊመርጡ ይገባል ” በማለት የግል አቋማቸውን ገልጸዋል ። በኢትዮጵያ ውስጥ ቀደምት ከሚባሉት የእምነት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የእሰልምና ሃይማኖት ተከታዮችን “ማንም ወገን ቢመጣ ሊያስተምራቸው አይችልም” ያሉት የደርግ ስር አትን እና ሰላጣናቸውን ጥለው ወደ አሜሪካ የተሰደዱት ሻለቃ ዳዊት “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከነቢዩ መሃመድ ጀምሮ ሲወረድ ሲዋረድ የመጣውን ሃይማኖታቸውን ላለፈው አንድ ሺህ አመት በላይ በሚገባ አጣጥመው የተማሩ በመሆናቸው ምንም አይነት አዲስ አስተምሮት እና ጫና አያሻቸውም፣እንግዳ ነገር ሲመጣ ሙስሊሞች እራሳቸው ለታገሉ ይገባል እንጂ መንግስት ጣልቃ ሊገባ አይገባውም” በማለት ምክራቸውንም ለግሰዋል ። የዋሂብዝም ተከታዮች ኢትዮጵያ ውስጥ ሰለመኖራቸው ምን ማስረጃ አለ?” ለሚለው የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢዋ ጥያቄ ሻለቃ ዳዊት ሲመልሱ “ ኢትዮጵያ ውስጥ በአይኔ ያየሁት ነገር ባይኖረም ከኢትዮጵያ ወደ ፓኪስታን /ማዳራስ እንዲሁም ወደ ሱዳን እና ወደ ሌሎች አገራት ለአስተምሮቱ በመጓዝ ጥናታቸውን ሲጨርሱ ወደ ኢትትዮጵያ ለመመለስ የሚፈልጉ መኖራቸውን ሲናገሩ ሰምቻለሁ “ብለዋል።ታዲያ ችግሮችን ለማቅለል ሲባል ምን መደረግ አለበት ይላሉ ? ለሚለው ተከታይ ጥያቄ”ሁል ጊዜ ውይይት እና መመካከር ቁልፉ ሚና ይጫውታል”ብለዋል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *