Hiber Radio: በአዲስ አበባ ታስረው የተፈቱት የአፍሪካ ህብረት ዲፕሎማት ናይሮቢ ላይ በድጋሚ ታሰሩ

ሚስተር ኦማር ፋሩክ ኦስማን
ሚስተር ኦማር ፋሩክ ኦስማን

በታምሩ ገዳ

ሚስተር ኦማር ፋሩክ ኦስማን የ ሁለት አገራት ፓስፖርት ባሌቤት ሲሆኑ የ አፍሪካ ሕብረት የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ያላቸው ናቸው።ታዲያ ሰሞኑን ኬኒያ ውስጥ ካልተከፈለ የሆተል እዳ ጋር በተያያዘ ከፍርድ ቤት ደጃፍ ለመቅረብ ፣የዲፕሎማቲክ ፓስፖርታቸው እሰከ መነጠቅ መደረሱን የናይሮቢ ዘገባዎች ሰሞኑን በሰፋት አትተዋል።

ኬኒያ ቢዝነስ ደይሊ የተባለ ጋዜጣ ሰሞኑን እንደዘገበው በትውልዳቸው የሶማሊያ ዜግነት ያላቸው የእንግሊዝ እና የሶማሊያ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ያዡ ሚስተር ኦማር ባለፈው ሳምንት ከናይሮቢው የ ጆሞ ኬንያታ አለማቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በኩል ወደ ሞሮኮ ለ ስራ ጉዳይ ለመጓዝ ሲሉ በ አንድ የቱሪስት እና እስጎብኝ ድርጅት በቀረበባቸው የማጭበረበር ወንጀል ሳቢያ በኬኒያ የኢሚግሪሽን ስራተኞች ቁጥጥር ስር ከዋሉ በሁዋላ ጉዛቸውም ተደናቅፎ ሶስቱም ፓስፖርቶቻቸው ለፖሊስ ለማስረከብ መገደዳቸው ተዘግቧል።

ለ አፍሪካ ህብርት ዲፕሎማቱ ኦማር በናይሮቢ ላሲኦ ሪጀንሲ ሆተል (Laico Regency Hotel )ውስጥ ባለፈው 2012 አኤ አ የምስራቅ አፍሪካ የጋዜጠኞች ማህበርን በ ዲፕሎማቱን በመወከል የ ሰብሰባ ዝግጅት ማድረጉን የሚናገረው ፒንክል የተባለው የጉዞ ወኪል ለሰጠው አገልግሎት ከ ዲፕሎማቱ ኦማር እንደሚከፈለው ቃል የተገባለት 3.6 ሚሊዮን የኬኒያ ሽልንግ (36 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ) ሳይከፈለው መቅረቱን አወስቶ በተለያዩ የጋራ ውይይቶች እና ምክክሮች ላይ ዲፕሎማቱ ኦማር ለጉዞው ወኪሉ የአገልግሎት ዋጋውን እንደሚከፈሉ ቃል ቢገቡም ቃላችውን አልጠበቁም ሲል ክሷቸዋል ። “እንዲያውም ዲፕሎማቱ የአገልግሎት ክፈያቸንን በ ባንክ አካውናታቸን በኩል መላካቸውን ቢገልጹም አክውናታቸንን ሰነመለከተው በኣርሳቸው ስም ምንም አይነት ገንዘብ ያለመጨመሩን ተረድተናል። ከዚያ በሁዋላ ዲፕሎማቱ ኦማር ወደ ኬኒያ ሲመጡ እራሳቸውን መሸሸግ ጀመሩ” የሚለው የጉዞ ወኪሉን አቤቱታን የተመለከቱት ዳኛ ኦልጋ ስዊስ ሰኞ አለት ዲፕሎማቱ ኦማርን ከፍርድ ቤት እንዲቀረቡ በማስደረግ /በማስመጣት ከ አጠቃላይ ገንዘብ ውስጥ ግማሱን (በ 1.8 ሚሊዮን የኬኒያ ሽልንግ (17 ሺህ ዶላር) )በማስያዝ ለጊዜው እንዲለቀቁ በይነዋል።

በተባበሩት መንግስትታት በትምህርት ፡ የሳይንስ እና የባህል ተቋም(Unesco ) ሰፖንሰርነት ናይሮቢ ውስጥ በወቅቱ የተካሂደው ስብሰባን የመሩት ዲፕሎማቱ ኦማር ያለመከሰሰ እና ያለ መታሰር መብታቸው መደፈሩን ( ዲፕሎማቲክ ኢሚዊኒታቸው )በኬኒያ የጸጥታ ሃይሎች እና በፍርድ ቤቱ እንደተደፈር ፣ የጋዜጠኞች ማህበሩም (EAJA) ደሞዛቸውን በማቆየቱ እና ለሰብሰባው የተባለውን ገንዘብ ወደ ደሞዛቸው እንዲዛወ ር እና የሆቴሉ ኣና የሰበሰባው ወጪ/እዳውንም ማህበሩ እንደሚከፍል በኢሜል ቅላ እንደገባላቸው (ከሆቴሉ ክፍያ ንጹህ መሆናቸውን )፣ በኬኒያ ውስጥ ቢሆን የመደበቅ/የመሽሎክሎክ ባህሪይ እንዳላሳዩ ይልቁንም በተለያዩ (ለ8 ጊዜያት )ወደ ናይሮቢ ጎራ ማለታቸው በመገለጽ የቀረቡባቸውን ውንጀላዎችን ተቃውመዋል ። በፍርድ ቤት የተነጠቁት የ አፍሪካ ህብርት ዲፕሎማቲክ ፓስፖርታቸን ጨምሮ 3 ፓስፖርታቸው እንዲ መለሱላቸውም ችሎቱን ጠይቀዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ስሙ የተጠቀሰው የ ምስራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች ማህበር(EAJA) በበኩሉ ለከሳሹ የጉዞ ድርጅት በላከው የኢሊክትሮንክስ መል እክት /ኢሜል “ዲፕሎማቱ የስራ ማስኪያጃ የተመደበውን ፉንድ አላግባብ አባክነዋል፣ቀደም ሲል የገቡትንም ቃል አልፈጸሙም ” ሲል እራሱን ከተጠያቂነት አርቋል።

ያለ መታደል አሊያም መጥፎ ባህሪ ሆኖባቸው ይሁን የአፍሪካ ህብረት ዲፕሎማቱ ኦማር እኤ አ በ ህዳር 2013 በኢትዮጵያ ውስጥ የሆቴል እና የታክሲ ወጪ አልከፈሉም በሚል ክስ ታስረው በስተመጨረሻም ወደ ትወልድ አገራቸው ጎረቤት ሶማሊያ እንዲባረሩ/ዲፖርተድ መደርጋቸውን የ ናይሮቢው አሰጎብኝ ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ኢልሳቤጥ ሞቡጋ ለችሎቱ ባቀረቡት የጽሁፍ አቤቱታ “ሚስተር ኦስማን በተለያዩ አገራት ጥሩ መስተንግዶ እና አገለግሎት ካገኙ በሁዋላ ደብዛቸውን የማጥፋት ባህሪይ እንዳላቸው እንደኛው (የፒናክል አስጎብኝ ድርጅት) ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥም (በ ጁፒተር ሆተል ላይ )ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸማቸውን ተረድተናል” በማለት በዲፕሎማቱ ላይ የውንጀላ ዶሲያቸውን አጠናክረዋል ያወሳሉ። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን በጥልቀት ለማየት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ስጥቷል። ፓስፖርታቸውን እና ያለመከሰስ መብታቸውን በመገፈፍ በናይሮቢ ጎዳናዎች ላይ እንደተራ ሰው የሚንገላወዱት ሚስተር ኦማር “ይዋል ይደር እንጂ እውነት ታሸንፋለች !!!” ባይ ናቸው።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *