Hiber Radio: ኢትዮጵያ ከጫት ምርት ሽያጭ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቀዳለች፣ ትርፍ ለማጋበስ ሲባል ብቻ ተተኪው ትወልድ እስከ መቼ ድርስ መሞት አለበት?

hiber-radio-chatt-001

በታምሩ ገዳ

በበርካታ የምእራብ እና የምስራቅ አውሮፓ አገራት አንዲሁም በሰሜን አሜሪካ ከ ህገወጥ አደናዥ እጾች ተርታ በመፈርጅ የአየር ግዛታቸውን እንዳይረግጥ የህግ ማነቆ የተደርገበት ፣ነገር ግን በምድረ ኢትዮጵያ በሰፋት የሚበቀለው እና የኢኮኖሚው ዋልታ የሆነው የቡናን ደረጃን በመንጠቅ ላይ ከሚገኘው የጫት ተክል ምርት መጠነ ሰፊ የውጭ ምንዝሬ ለማግኘት መታቀዱ ታወቀ።

አና ዶሉ የተባለው የቱርኩ የዜና አገልግሎት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሮ ያጠናቀረው ዘገባ ኣንደሚያትተው ከሆነ በአገሪቱ የ ንግድ ሚንስተሩ ቀመር/ ትንበያ መሰረት ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ከ 840 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሬ/ገቢ ያሰገኘው የጫት ተከል “እደግልን ተምንደግልን” ተብሎ በቀጥዩቹ አምስት አመታት ውስጥ እስከ 1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ያስገኛል ተብሎ ተሰፋ ተጥሎበታል።

ቸረነት አዱኛ በአገሪቱ የጫት ምርት መነሃሪያ ከሆኑት መካከል አንዷ በሆነችው የሓዋሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆን ፣ጫት ቃሚ እና ጫት ሻጭ ነው። ታዲያ የጫት ተክል እና ስርጭቱ ይታገድ ለሚልው የአንዳንድ ወገኖች አስተሳሰብ ከአናዶሉ ዘጋቢ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ”ይህ ፈጣሪ የሰጠን የጫት ምርት እሰከ አለም ፈጻሜ ድረስ ሊቋረጥ አይገባውም “ በማለት ከጫት መቃም እና ከሽያጭ ስለሚገኘው ትርፉ እና ምቾቱን ደግፎ ተናግሯል። በቃለመጠይቁ መሃል ጣልቃ የገባው አይኑ ያፈጠጠው፣ መንፈሱ ያለተርጋጋው ባለ ጢማሙ የጫት ደንበኛው “ አቦ ይሔ ፈልሰፍናህን አቁም !! ይልቁንም ጫታችንን ሰጠኝ ። ለወሬ ጊዜ የለንም። በማለቱ ውይይቱን ማቋረጡን ዘጋቢው ያወሳል።

ለመዲናይቱ አዲስ አበባ የጫት ቃሚዎች አስራ አምስት (15) አይነት የተለያዩ የጫት መርቶች እንደሚጎርፉላት የሚገልጸው ዜና ዘገባው በ ግል ተመራማሪው አቶ ዳነኤል መገርሳ እምነት “ በአንድ ወቅት በተወሰኑ የማህበረሰቡ ክፍሎች ዘንድ ይዘወተር የነበረው ጫት በዛሬይቱ ኢትዮጵያ በሄራዊ እና ባሕላዊ ሱስ አስያዥ ተክል እና የብዙ ሚሊዮኖች ዶላር መገኛ ሆኗል። ዛሬ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ወጣት ወንዶች እና ሴቶች የጫት ምርኮኛ ሆነዋል። “ብለዋል።ባለፈው 2014 -2015 አኤ አ ከ248ሺህ ሄክታር የጫት መሬት ላይ 275 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ጫት የተመረተ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 45 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ጫት ለውጪ ገበያ የቀረበ ሲሆን ቀሪው 226 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የጫት ምርት በሃገር ውስጥ የጫት ደምበኞች ተቅሟል ።” በማለት የአገሪቱ የስታስቲክስ መስርያ ቤት መዘገቡን ያጣቅሳሉ።

በተመራማሪው አቶ ዳንኢል ዳሰሳ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ጫት ቃሚዎች በአጠቃላይ በአመት ወደ 800 ሚሊዮን ብር ወይም 35 ሚሊዮን ዶላር ለጫት ወጪ ያድረጋሉ።የጫቱም አይነት እና ጥራት ዋጋውም በጥቅሉ (በዙርባው) ከ 35 ብር እሰከ 1000 ብር ይደርሳል ብለዋል። ይህን ያህል የማህበረሰቡን ኪስ የሚያስበረብረው የጫት ሱስ ለጤና ጠንቅነቱ ቀላል የማይባል ሲሆን የህክምና ባለሙያው ዶክተር መሳፍንት አበበ ሰለ ጫት ለጤነነት ያለው ጠንቅነትን ሲመክሩ”ጫትን ማዘወተር ለቀባጣሪነት(አለመረጋጋት) ፣ ለ ጭንቀት ፣ ለደም ግፊት ፣ለእንቅልፍ እጦት እና ለጨጓራ ህመሞች ይዳርጋል።” ሲሉ ያሰጠነቅቃሉ ፣ይገሰጻሉ።

ከ ጎረቤት ሶማሊያ እና ጅቡቲ አንስቶ ማላዊ ፣ሕንድ፣ ደ/አፍሪካ ፣እስራኤል፣ ሆንግ ኮንግ ፣ብራዚል ፣ ኖሮዊይ የመሳሰሉት 90 አገሮች ላይ መዳረሻውን በማድረግ ለወቅቱ መንግስት እና ለሰግብግብ ነጋዴዎች በታክስ እና በትርፍ መልክ ደጎስ ያለ እና ተዝቆ የማያልቅ ገንዘብ (ብር/ዶላር) ማሰገኛ የሆነው የጫት ተክል የአገሪቱ ትወልድን በተተኪነት ሆነ በብሩህ ተስፋ አላሚነት መጉዳቱ እየታወቀ በአገዛዙም ሆነ አግባብነት ባላቸው መንግስታዊ የሆኑ እና ያልሆኑ ተቋማት ዘንድ በአደገኛው/አደንዛዡ የጫት ተክል ላይ አንደ ምእራብ አውሮፓዎቹ እና እንደ አሜሪካ ጠበቅ እና ቆንጠጥ የሚያድረግ ሕግ በጫት ተከል እና ዝውውሩ ላይ እንዲወጣ ጥረት ያለማድረጋቸው አሊያም ጉዳቱን እየተመለከቱ ችላ ማለታቸው ተተኪው ትወልዱን የመግደል ያህል እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *