Hiber Radio: “የኤርትራ ባለስልጣናት እንደ ወያኔዎች ዘራፊዎች አይደሉም …ኢሳያስን እንመርጣለን ይላሉ ”አርበኛ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የውጭ ግንኙነት ሀላፊ፣“ከሟቹ መለስ ዜናዊ እኩል ሊጠየቁ ለሚገባቸው ጥብቅና መቆም አይገባም ” የ መብት ተሟጋቹ ያሬድ ሃ/ማሪያም

አቶ ነአምን ዘለቀ፣የኤርትራውያን ድጋፍና ተቃውሞ በአውሮፓ ፣አቶ ያሬድ ሀ/ማሪያም
አቶ ነአምን ዘለቀ፣የኤርትራውያን ድጋፍና ተቃውሞ በአውሮፓ ፣አቶ ያሬድ ሀ/ማሪያም

በታምሩ ገዳ

የአለማቀፉ ማህበረሰብን እንደሚወክል የሚነገርለት የተመድ የሰብ አዊ መብት አጣሪ ቡደን የኤርትራ መንግስት በዜጎቹ ላይ የተለያዩ ኢ-ሰብ አዊ የሆኑ ድርጊቶችን የፈጽማል ፣ከ400 ሺህ በላይ የአገሪው ዜጎች ለተለያዩ የመብት ረገጣዎች ተዳርገዋል በማለት ሰሞኑን ያወጣው ጠንካራ መግለጫን ተከተሎ በርካታ ኢትዮጵያዊያኖች እና ኤርትራዊያኖች የፖለቲካ መሪዎች፣ የመብት ተሟጋቾች እና የማህበረሰብ ክፍሎች ጎራ በመለየት በጉዳዩ ዙሪያ እየተናረኩበት የገኛሉ ።

የሰብ አዊ መብት አጣሪ ቡደን ዳሰሳን ከተቃወሙት ወገኖች መካከል የአርበኞች ግንቦት 7 የውጪ ጉዳይ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ነአምን ዘለቀ አንዱ ሲሆኑ የድርጅታችው አባላት ሆኑ ሰላም ወዳድ ወገኖች በሙሉ በተመድ የሰበዊ መብት አጥኚ ቡደን በኤርትራ ላይ ያለውን አቋም እንዲቀየር አልያም አሊያም የቡድኑን ወሳኔን ኣንዲቃወሙ ደጋፉቸውን በፊርማ እንዲያረጋግጡ ጥሪ ማቀረባቸውን ተከተሎ ከ ዋሽንግተን ዲሲ በአማሪኛ ፕሮግራም ከሚተላለፈው የ አዲስ ድምጽ ራዲዩ ባለቤት እና አቅራቢ ከሆነው አርቲስት እና ጋዜጠኛ አበበ በለው ጋር ባለፈው ሰኔ 12/ 2016 እ ኤ አ ባደረጉት ዘለግ ያለ ቃለ ምልልስ ድርጅታቸው ከ አሰመራ መንግስት ጋር ለመቆም ሶስት ጉዳዮች እንዳሰገደዱት የገለጹ ሲሆን እነርሱም” ኤርትራ ውስጥ እነደ ማንኛውም አገር በተለይ ከ ኢትዮ -ኤርትራ የድንበር ላይ ጦርነቱ በሁዋላ ከብሄራዊ ደህንነት አኳያ የሰበእዊ መብት ችግሮች አሉ፣የፖለቲካ አስረኞች አሉ፣ በብዙ መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች አሉ፣ለኢትዮጵያ ህዝብ የምመኘውን ሁሉ ለኤርትራ ሕዝብም እንዲሁ እመኛለሁ፣ ነገር ግን የተመድ አጣሪ ቡደን በኤርትራ ላይ ያለው አቋም ትክክል አይደለም፣ባለሁለት ፍርጅ አቋም/ደብል ስታንዳረድ ነው/፣አጨቃጫቂም ነው ።” በማለት አሰተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመቀጠለም ይህንኑ አቋማቸውን ሲያብራሩት”የወያኔ አገዛዝ በተለያዩ ጊዜያት በጋምቤላ ፣ በኦጋዴን ፣በኦሮሚያ እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ውስጥ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻቻን ላይ እጅግ ዘግናኝ የሆነ የመብት ረገጣ ሲፈጽም የተለያዩ የሰበዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጽኑ ሲያወግዙት ይህ በኤርትራ ጉዳይ እንዲያጠና የተዋቀረው እና የመብት ረገጣን አጣራለሁ የሚለው አለማቀፍ አካል ግን በወያኔ መንግስት ሰለ ተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ እሰከ አሁን ድረስ አንድም ያለው ነገር የለም።በኤርትራ ውስጥ የሚካሄደው የመብት ረገጣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚካሄደው የመብት ረገጣ የከፋ አለመሆኑን እኔ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ከኤርትራ መንግስት የበለጠ የከፋ የመብት ረገጣ የሚያድረጉ አገሮች እያሉ በአስመራ መንግስት ላይ የህ አይነቱ ጫና የበረታው የኤርትራ መንግስት ለውጪ ሃይሎች አጎብዳጅ ስላልሆነ ነው” ያሉት እቶ ነአምን ዘለቀ ለአባባላችው ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ እውቁ የሰብዊ መብት ተሟጋች ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም በአንድ ወቅት አሜሪካ ውስጥ “የድሮው የኢትዮጵያ ኩራት የቀረው ኤርትራ ውስጥ ብቻ ነው ማለታቸው ይታወሰልኝ” በማለት ለራዲዮኑ አድማጮች ደጋግመው አስታውቀዋል ።

ወደ ኤርትራ ለሶስት ጊዚያት እንደ ተጓዙ እና በዚያም ለአምስት ወራት መቆየታቸውን በተናገሩት በአቶ ነአምን ዘለቀ እምነት “ኤርትራ ውስጥ የማህበራዊ ፍትህ/ሶሺያል ጀስቲስ አለ፣የኢኮነሜ ፍትህ/ ጀስቲስ አለ፣ ኤርትራ ውስጥ የአኩልነት ፍትህ አለ ፣የኤርትራ ባለሰልጣናት እንደ ወያኔ ባለሰልጣናት እነደሆኑት አነ ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ በጉቦ የተጨማለቁ ሳይሆኑ በከረከሱ አሮጌ መኪናዎች የሚሄዱ እና ያለ አጃቢ ከህዝቡ መሃል በነጻነት በጎዳናዎች ላይ የሚጓዙ ናቸው።የኤርትራ ባለሰልጣንት በህዝቡ ጭንቅላት ላይ ሆነው የሚቀልዱ አይደሉም ፣ይልቁንም የህዝቡን ኑሮ የሚኖሩ ናቸው፣ በኤርትራ የሶሻል ጀስቲስ የምንላቸው እንደ ነጻ ህክምና እና የነጻ ትምህርት እድሎች አሉ። ይሁን እንጂ ገና ያልተሟሉ ነገሮችም አሉ። እንደ ነጻ ፕሬስ የመሳሰሉት በኤርትራ ውስጥ እንዲያብቡ እፈልጋሁ።” ያሉት የአርበኞች ግንባር እና የግንቦት ሰባቱ ከፍተኛ ሹሙ አቶ ነአምን በሶስተኛ ደረጃ እና ዋንኛ የደጋፍ ፊርማው አሰፈላጊነቱ ማሳመኛ ሃሳብ ብለው ያቀረቡት “ እኛ የዲሞክራሲ ሃይሎች ከኤርትራ በሰተቀር ወዳጅ የሚባል የለንም ፣ከዚህም አኳያ የኤርትራ መንግስት መዳከም ማለት የአኛ ሃይል መዳከም ማለት ነው። ይህንን የወያኔ ጨቋኝ ስርአትን ለመዋጋት የኤርትራ መንግስት እና ህዝብ የሚያደርጉለን ድጋፍ ከፍተኛ ነው። ” በማለት ድርጅታቸውም ሆነ ደጋፊዎቻቸው ለምን ከወቅቱ የአሰመራ መንግስት ጎን ሙሉ በሙሉ መቆም እንዳለባቸው ለማስረዳት ሞክረዋል ።

የአቶ ነአምን አስተያየትን በመለጠቅ ከጋዜጠኛ አበበ በለው የቀረበው ጥያቂ”በአርሶ አቀራረብ የተመድ የሰበዊ መብት አጣሪ ቡድን በኤርትራ ላይ ያካሄደው የምርመራ አካሄድ የሚመሰለው ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር በማነጻጸር ይመሰላል ፣ከአቶ ኢሳያስ መንግስት ደጋፊዎች በቀር በውጪ የሚገኙ የአገሪው ተወላጆች አንዳቸውም አገዛዙን የማይቃወሙ ይመሰላል” ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ”እኔ ወደ ኤርትራ በሄድኩበት ወቅት በብሄራዊ ውትድርናው ሳቢያ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጉረመርሙ ተቃዋሚዎችን አነጋግሬለሁ። ነጻ ምርጫ ቢመጣ ማን ትመረጣላችሁ? ብዩ ሰጠይቃቸው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂን እንመርጣለን ምክንያቱም አቶ ኢሳያስ ሃቀኛ ሰው በመሆናቸው ነው የሚሉ ወገኖች አጋጥመውኛል። ይህን ሁሉ ስልህ ግን በኤርትራ ውስጥ ችግሮች የሉም እያልኩ አይደለም ።የተመድ አጣሪው ቡድን ግኝት የፖለቲካዊ አንደምታ ያለው ፣በተወሰኑ ወገኖች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ፣ገለልተኝነት የጎደለው እና ኤርትራን ኢላማ ያደረገ ነው።የወያኔ መንግስትን ጨምሮ ላለፉት 25 አመታት በብዙ ሺህ ዜጎችን የጨፈጨፈ ፣ ሳይጠየቅ እንዲያውም ድጋፍ እየተደርገለት ፣ውንጀላው ደሃ እና ትንሽ በሆነችው በኤርትራ መንግስት ላይ ብቻ ለምን ተነጣጠረ?። ያ ነው የእኔ ጥያቄ።” በማለት ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል።

አርቲስት እና ጋዜጠኛ አበበ በለውም ጥያቄውን መወርወሩን አላቆምም”የ ወያኔ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚያደረሰውን ጭቆና እና እረገጣን ሁላችንም 100% እናወግዛለን ፣እዚህ ላይ ችግሩ ግን ተመሳስይ በሆነ ጉዳይ/የመብት ረገጣ ላይ ለምን የተለየ አቋም ተያዘ?’’ ሲል ላቀረበው ጥያቄ አቶ ነአምን ሲመልሱ”ተመሳስይ ግፍ የሚባል ነገር የለም ። በኤርትራ ውስጥ እንደ አትዮጵያ የዘር ማጥፋት /የጂኖሳይድ ወንጀል አይፈጸምም ፣በኢትዮጵያ ደረጃ የሚካሄደው ግፍ እና በደል በኤርትራ ውስጥ እንደማይካሄዱ አስረግጪ ልነግርህ አችላለሁ ። በኤርትራ በነበርበት ወቅት አገዛዙን እንቃወማለን የሚሉትን ሳይቀር ቁጭ ብዩ ለመጠየቅ እድሉ ነበረኝ።ሰለ ኤርትራ የሚነገሩት ሁሉ የተጋነኑ ናቸው ።ይህን ውንጀላን በተመለከተ ወደ ኤርትራ የተጓዙ ፍርንጆቹ ሳይቀሩ እያረጋገጡት ነው ።”በማለት ለአሰመራ መንግስት ያላቸው የደጋፍ አቋማቸውን አጠናክረዋል።

የፊርማ ማሰባሰቡ ዘመቻን በተመለከተ ከጋዜዘጠኛ አበበ በለው በኩል በተጨማሪነት የቀረበው ጥያቄ “ በእናንተ ምልከታ የኤርትራ መንግስት ብቸኛው አጋራችሁ/ረዳታችሁ መሆኑን ስትናገሩ በተቃራኒው ደግሞ የኤርትራው አገዛዝ አንገሽግሾናል ፣መኖር አልቻልንም የሚሉ ወገኖች መኖራቸው የታወቃል። ታዲያ እናንተ የየትኛው ኤርትራዊ ደጋፍን ነው የምትሹት? ፡(አፍቃሪ አቶ ኢሳያስ ወይስ ጸረ አቶ ኢሳይስ ) አቋምን ይዛችሁ ነው አላማችሁን የምታሳኩት?”የሚል ጥያቂ ሰንዝሮላቸው ነበር ። የአቶ ነአምን ምላሽም”እኔ ኤርትራ ውስጥ ጉደሉ የሚባሉ ነገሮችን ሁሉ እንዲሟሉ እፈልጋለሁ፣ ነገር ግን አሁን በአጣሪው ቡደን እንደችግር ትደረጎ የቀረበው በፖለቲካዊ ስሜት የተሞላ ነው ። እንደ እኔ አመለካከት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰበዊ መብት ረገጣ ከኤርትራ የሰበዊ መብት ረገጣ ጋር በጭራሽ አይወዳደርም ነው ያልኩት ።” ሲሉ መልሰዋል። አሰጣ ገባው ተካሮ ጋዜ ጠኛ አበበም የሚከተለውን የጠይቃል “እኛ ለኢትዮጵያ ነጻነት የምንታገል ሃይሎች ‘ኤርትራ እንድትነካብን አንፈልግም ‘ከሚለው አቋማችሁ በተቃራኒው የሚገኙ ወገኖች ለሚያነሱት ‘ለዚህ ሁሉ ችግራችን መነሻው እና መደረሻው የአቶ ኢሳያስ መንግስት ነው ‘ለሚሉ ወገኖች ምላሾት ምድን ነው?”ሲል የጠይቃል ። አቶ ነአምን ዘለቀም ሲመልሱ”ኤአርትራ ትንሽ እና ደሃ አገር መሆኑዋ የታወቃል ።ለዚህ ሁሉ የደህነነት፣ ኢኮኖሚ ፣የችግሯ ዋንኛ መንሰኤው ደግሞ የወያኔ መንግስት ነው ፣ስለዚህ የወያኔ መንግስት ከተወገደ፣ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ከመጣ ኤርትራ ውስጥ ያለው ችግር ይወገዳል፣ ሰጋቶችም ይቀንሳሉ ።” ብለዋል።

በአቶ ነአምን ተቃራኒ የቆሙት ደግሞ በአወሮፓ/ቤልጂየም ብራሰልስ የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብት ጉዳይ ተሟጋች ድርጅት መሰራች የሆኑት አቶ ያሬድ ሃ/ማሪያም ሲሆኑ አርሳቸውም ለተቃውሟቸው ምላሽ ሲሰጡ”የአርበኞች ግንቦት 7 ሃላፊዎች ጭምር የእውቁ ጥቁር አሜሪካዊው የመብት ተሟጋቹ የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ታዋቂው ጥቅሱን የጠቀማሉ ።እርሱም፦’በአንድ ቦታ የፍትህ መጓደል ማለት ፣ በሁሉም ቦታ የፍትህ መጓደል ማለት ነው’ ይሄ አባባል የወያኔ ስር አት በዜጎቻቸን ላይ የሚያደረሰውን በደል እና ግፍ የሁሉንም ሰላም ወዳድን ስሜት የቆረቁራል፣ይነካል ብለን አቤት የምንልበት አቀራረብ ነው ።በሌላ በኩል ደግሞ ኤርትራዊያን ወገኖቻቸን እየደረሰባቸው ያለውን በደል እና ሰቃይን በተመለከተ አለማቀፉ አጣሪ ቡደን ሪፖርት ሲያወጣ አቶ ነእምን ቀደም ሲል የሰጡትን አስተያየት ሰምቻለሁ ።ከኤርትራ መንግስት ጋር አብሮ/ተባብሮ መስራት አንደ ነገር ሲሆን ፣ለዚያ ስርአት/ለሻቢያ ጥብቅና መቆም ግን በአንድ ግለሰብ ላይ እንኳን ግፍ እና በደል ቢፈጸም ወንጀሉን ከፈጸመው ወገን ጎን እኩል የመቆም ያህል ሆኖ ነው የሚታየው ። የፖለቲካ ጥቅምን ማየት፣ መደራደረ፣ አብሮ መስራት እና አብሮ መታገል እንዳለ ሆኖ በደል በየትኛውም ስፍራ ይፈጸም ቢቻል በደልን መቃወም ተገቢ ነው ፣ካልሆነ ደግሞ በሌሎች አስገዳጅ ሁኔታዎች እንኳን ተይዘን ከሆነ ከበዳዮች ጎን መቆማችንን በሚያሳይ እና በሚያጋልጥ ሁኔታ፣ እንደ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አይነቱ በንጹሃኖች ደም እጁ ለተበላሸ ለኤርትራዊያኖች ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠሩ ብዙ ምስቅልቅሎች ተጠያቂ ለሆነ ፣ ከሟቹ መለሰ ዜናዊ እኩል ለመጠየቅ ወደ ኋላ ለማይባልበት ሰው/ለአቶ ኢሳይስ አፈወርቂ /ጥብቅና መቆም እና ለእርሱ ሲባል ፊርማ ማሰባሰብ በእኔ ግምት ከሞራልም ሆነ ለፍትህ እንታገላለን ከሚል አካል የሚጠበቅ አይመሰለኝም።”በማለት የአቶ ነአምንን አሰተያየትን በጽኑ ተቃውመዋል።

የተመድ አጥኚው ቡደን ገለልተኛነትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ያሬድ ከልምዳቸው መልሱ”ቡደኑን የሚዘውሩት አካላት የፖለቲካዊ ዘንባሌ፣የመቧደን ያለው አካል ለመሆኑ ጥርጥር የለውም።የአንድ አገርን ጉዳይ የማክረር ፣ የሌላው ወዳጅ አገርን ጉዳይ ችላ የማለት እና ኢፈተሃዊ የሆኑ መደጋገፎች ለመኖሩ በግላጭ ነው የሚታየው ።ከዚህ አኳያ አቶ ነአምን ያሉት ጉዳይ በጥቅሉ እወነታነት አለው ።’ኤርትራ ብቻ ነች ኢላማ የሆነቸው’ የሚለው የአቶ ነአምን አሰተያየት ግን ትክክል አይደለም ለምሳሌ ደ/ሱዳን፣ ሶሪያ ፣ ብሩንዲ፣ ሰሜን ኮሪያ ፣የመን፣ ጋዛ(ፍልስም) ፣ሲሪላንካ፣ሊቢያ፣ባህሪን የመሳሰሉት አገሮች ላይ ጥናት አድርጓል።ተፈጸሟልም ባለው የመብት ረገጣ ዙሪያ እርምጃ እንዲወሰድ ይጠየቃል። ከዚህ አኳያ ኤ ርትራ ብቸኛ አገር አይደለችም።ለምን ኢትዮጵያ ሳትወቀስ እንዴት በኤርትራ ላይ ብቻ ተነጣጠረ? ለሚለው ጥያቄ እርሱ እራሱን የቻለ ጉዳይ ነው ።

ኮሚሽኑ ዝም ብሎ ላጥና አይልም ከኢትዮጵያ የበለጠ እነ አሚንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሁማን ራይት ዎች የመሳሰሉት ጠንከር ያለ ሪፖርት ማወጣታቸውን ተከተሎ ነው ጥናቱ የተካሄደው ።ኢትዮጵያን በተመለከተ በጭላንጭልም ቢሆን ሰለ ጅምላ ጭፈጨፋዎች በተለያዩ ወገኖች ሪፖርት የሚቀርቡ ሲሆን ፣ኤርትራን በተመለከተ ግን ምንም አይነት መረጃ ከአሰመራ ለማግኘት በጭራሽ አይቻልም። አቶ ነአምን በተፈጠረላቸው አጋጣሚ ተጠቅመው የተወሰኑ ሰዎችን አነጋግረው ‘ሰላም ነው’ ተብለው ሊሆን ይችላል።በአጠቃላይ በአገሪቱ ሰላለው የሰበዊ መብት አያያዝ በተመለከት ግን 45ሺህ ኤርትራዊያኖችን ጨምሮ እነ አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል አጣሪ ቡድን ይቋቋም በማለት ጥሪ ሲያሰሙ ቁይተዋል።አቶ ኢሳያስ ለምእራባዊያኖች ተገዢ ባለመሆናቸው ነው የተባለው ጉዳይ እውነታነት ሊኖረው ሊሆን ይቻላል ። ለማንኛውም በኤርትራ ላይ ያነበብነው ሪፖርቱ ወጥቷል።”ብለዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ሲሞቱ እነሰማለን ኤኢርትራ ውስጥ ግን ሞቱ የሚባል ዜና የለም ከዚህ አኳያ የአቶ ነአምን መከራከሪያ ትክክል ነው አያስብልም ወይ?ለሚለው የጋዜጠኛ አበበ ጥያቄ አቶ ያሬድ ሲመልሱ”ኢህ አዲግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት ከስድስት ሺህ በላይ ሰላማዊ ዜጎችን ግድሏል።ታዲይ በኢ ህ አዲግ ላይ ለምን ማጣራት አይደረግም ለሚለው ጥያቁ እና አጥኚ ቡደኑንን ለመፋለም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ እና ፈተና ነው ።አቶ ነአምን እንዳሉት ኮሚሽኑ ሁለት ገጽታ/ደብል ስታንዳርድ ሊኖረው ይችላል።ከኤርትራ በከፋ የመብት ረጋጮች ሊኖሩ ይችላሉ።አጣሪ ቡድኑ ያጣራል።እኛም በአመት ሁለቴ ወደ ኮሚሽኑ ዘንድ የምንሄድው ለዚህ ጉዳይ ነው አሁን የኤርትራ ህዝብ እሮሮ ያገኘውን ማላሽ የሚስተካከል ምላሽ ለማግኘት ነው ። ኢትዮጵያን በተምለከተ ኮሚሽኑ እንዲያጣራ እጥብቀን መጎትጎት፣በማስረጃ የተደገፈ ሰለሆነ ምን ትጠብቃላችሁ ማለት ነው እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የመብት ረገጣ ሳታጣሩ በኤርትራ ላይ የማጣራት መብት የላችሁም፣ እርምጃውም ወዳጃችን አቶ ኢሳያሰን አትንኩ እንደ ማለት ነው ።አባባሉም ውሃ የሚቋጥር ምክንያት አይደለም ። በኢትዮጵያዊያኖች ዘንድ በቡደን/ቲፎዞ ፖለቲካ ምትክ የመቻቻል እና የመመካከር ባህል ሊጠነክር ይገባል ።”በማለት እግረ መንገዳቸውን ጥሪ አቅርበዋል ።

በተያያዘ ዜና የተመድ የሰብ አዊ መብት አጣሪዎች/ፓናሊስቶች በኤርትራ የወቅቱ አገዛዝ ላይ ያወጡትን የመብት ረገጣ ሪፖርት በተመለከተ ሪፖርቱን የሚቃወሙ(የአቶ ኢሳያስ አገዛዝን የሚደግፉ) እና በተቃራኒው አገዛዙን የሚቃወሙ(የአጥኚ ቡድኑ ሪፖርቱን የሚደግፉ) ወደ ሰባት ሺህ የሚገመቱ ከ አውሮፓ፣ ከካናዳ እና ከአሜሪካ የመጡ ኤርትራዊያኖች በትላንትናው እለት ሰኔ 21, 2016 አኤ አ የተመድ የሰብአዊ መብት ዋና ጸ/ቤት በሚገኝበት ጄኔቫ/ሲውዘርላንድ ታላቅ የድጋፍ/የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደዋል።ለተቃውሞ ሰልፍ ከወጡት እና ከአዘጋጆቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ነጋሽ ኦስማን የተባሉ ሰለፈኛ ለ አልጀዚራ ቴሌቪዥን በሰጡተ አስተያየት “ምንም እንኳን በኤርትራ ውስጥ ያለው የሰብ አዊ መብት ረገጣው ለእኛ እንግዳ ባይሆንም የአጣሪው ቡድን ሪፖርቱን በተመለከተ የአለም ሕዝብ አሮሮአችንን ያዳመጡን መሰሎ ነው የታየኝ።”በማለት ለ ኮሚሽኑ ድጋፋቸውን ሰጠተዋል። የደጋፍ ሰልፉን ለመቀላቀል ካታላቋ ብሪታኒያ ወደ ጄነቫ የተጓዙት ሰላም ኪዳኔ የተባሉአክቲቪስት በበኩላቸው “ኢርትራ ውስጥ ለተፈጸምው የሰብ አዊ መብት ረገጣ አገዛዙ ሊጠይቅ ይገባል።” ብለዋል።

በተቃራኒው ጎራ( የአሰመራ መንግስትን በመደገፍ) ከወጡት መካከል ራሄ ል ወ/አብ የተባሉት የስውዲ ን ነዋሪ” ኮሚሽኑ የተከተላቸው የቃለመጠይቅ ቲክኒኮች የተዛባ ነው።” በማለት ወግዛታቸውን አቅርበዋል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *