Hiber Radio : የ12ተኛ ብሔራዊ ፈተናን ለመከላከል በሚል አገዛዙ በኢትዮጵያ ፌስቡክን ጨምሮ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ማፈኑን አመነ፣አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ የእንግሊዝ መንግስት ተገቢውን ጥረት እንዲያደርግ የሕዝብ እንደራሴዎች በሙሉ ድምጽ ወሰኑ ፣ሐሙስ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ውድቅ ሆኖ የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጠ ፣በአወዛጋቢው በአባይ ግድብ ጥናት ላይ ኢትዮጵያ፣ግብጽ እና ሱዳን በአዲስ አበባ ሊፈራረሙ ነው

 

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 3 ቀን 2008 ፕሮግራም

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ንቅናቄ ዶ/ር መረራ የተገኙነት ታላቅ ስብሰባ በሚኒሶታ ሚኒያፖሊስ አካሔደ ውይይት ከአቶ ነጌሳ ኦዶ የፓርቲው ዓለም አቀፍ የድጋፍ ማህበር ሊቀመንበር ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያድምጡት)

<…የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ፌዴሬሽን ኢትዮጵያውያንን ከመላው ዓለም ማሰባሰብ የቻለ እና የተሳካለት ነው።ነገር ግን ይህን ታላቅ መድረክ የበለጠ ለማሳደግና ለሚመጡት እንግዶች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉ ለምሳሌ የዘንድሮ የመግቢያ ዋጋ እና…> አክቲቪስትና የህግ ባለሙያ ተክለሚካኤል አበበ(ልጅ ተክሌ) የተጠናቀቀውን የ33ተኛ የኢትዮጵአውያን ስፖርት ፌዴሬሽን አስመልክቶ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያድምጡት)

<…የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በመደረጉ የተሰረዙ ኮንሰርቶች ነበሩ ።ብዙ ሰዎች ቴዲ አፍሮ ጋር ሄደዋል ።ለዚህ ምክንያቱ ሰው መትፋቱ አይመስለኝም ለዘፋኞቹም ሞራል ሲባል ጥሩ የፕሮሞሽን ስራ የተሰራ አይመስለኝም…የቶሮንቶው ጠሜዳ መግቢያ ዋጋ በእርግጥ የመጀመሪያው ቀን ውድ ነበር ሰዎች ከዚያ በሁዋላ ፌዴሬሽኑ ወደ ሃያ ዶላር ዝቅ ማድረጉንና ከአስራ ሁለት ዓመት በታች ላሉ አለማስከፈሉን የተረዱ አልመሰለኝም።ከዚያ በተጨማሪ …> ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ የቶሮንቶውን ዝግጅት አስመልክቶ ለህብር ከሰጠው ማብራሪያ( ሙሉውን ያዳምጡት)

በሀብታሙ ጉዳይ የተጠየቀው የቦርድ ወረቀት አግባብ አይደለም ቦርድ የሚኢፈው ከባንክ የውጭ ምንዛሬ ለሚፈልግ ወይ በመንግስት ለሚታከም ለህመሙ ማረጋገጫ በሚል ነው ። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የህክምና ወረቀት አምጡ አለን አመጣን አይ የቦርድ ሲባል እሱኑ ከሆስፒታሉ ጠይቀን ከሶስቱ ዶክተሮች ሁለቱ ጽፈው አንዱ እየተጠበቅ ነው እሱም …> አቶ ዳንኤል ሺበሺ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ለህብር ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

በሚኒሶታና በሉዚያና በፖሊስ የተገደሉት ጥቁሮችን ተከትሎ በዳላስ የተደረገው ተቃውሞና በዳላስ የቀድሞው የአሜሪካ ወታደር በፖሊሶች ላይ የወሰደው የግድያ እርምጃ ሲዳስ(ልዩ ዘገባ)

ሁበርና ሊፍትን በመቃወም በሳን ሆሴ የታክሲ አሽከርካሪዎች ያደረጉት ትግልና ያገኙት ውጤት ቃለ መጠይቅ (ያዳምቱት)

የኢራቅ የሰሞኑ የሽብር ጥቃት የዓለም ዋና ዋና የፖለቲካ መሪዎች ምልከታና የኢራቅ መጻኢ ዕጣ ምን ይሆናል(ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

የ12ተኛ ብሔራዊ ፈተናን ለመከላከል በሚል አገዛዙ በኢትዮጵያ ፌስቡክን ጨምሮ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ማፈኑን አመነ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ የእንግሊዝ መንግስት ተገቢውን ጥረት እንዲያደርግ የሕዝብ እንደራሴዎች በሙሉ ድምጽ ወሰኑ

ሐሙስ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የዐቃቤ ሕግ ይግባኝ ውድቅ ሆኖ የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጠ

ዶ/ር መራራ የአገር ቤቱን ተቃውሞ ለማገዝ ዲያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠየቁ

በአወዛጋቢው በአባይ ግድብ ጥናት ላይ ኢትዮጵያ፣ግብጽ እና ሱዳን በአዲስ አበባ ሊፈራረሙ ነው

በድርቅ ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ከትግራይ መሰደድ መጀመራቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ተገኝተው የፖለቲካ ስደተኛ አናባርርም ያሉት የእስራኤሉ ጠ/ሚ/ር ኔታንያሁ ተቃውሞ ገጠማቸው

በአቶ ስብሃት ነጋ የደረሰው ውርደት እንዳይደርስባቸው አንድ የሕወሓት ባለስልጣን የክብር ዶክትሬት አልቀበልም ማለታቸው ተገለጸ

 Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-071016-071716

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *