Hiber Radio: በአማራና በኦሮሚያ ክልል የሚደረጉትን ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ሁሉም እንዲደግፍ ጥሪ ቀረበ፣የሕወሃት አገዛዝ ሕግ ጥሶ ሰልፉን የማደናቀፍ ሩጫው ተቀባይነት አላገኘም

amhara-oromo-protest-002

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በሉት ሃያ አምስት ዓመታት በአማራ በኦሮመ ሕዝቦች ለይ ከሚአደርሰው የከፋ በደል በተጨማሪ ለሕዝቡ ሰላማዊ ጥያቄ የሚሰጠው የጥይት ምልስን ለመቃወም፣ የሕዝብ መብት እንዲከበር ለመጠየቅ በመላው ኦሮሚያ እና በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር በደብረ ታቦር፣በእስቴ እና በባህር ዳር እንዲሁም ባለፉት ስምንት ወራት በኦሮሚአ ሰላማዊውን የሕዝብ ጥያቄ ተከትሎ፡የአገዛዙን አጋዚ ወታደሮች የሚፈጽሙትን መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ለመጠየቅ የተጠራ፣የህዝቡ መብት እንዲከበር ድምጽን ለማሰማት የጠጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደነናፍ አገዛዙ በየክልሉ አስተዳደር በኩል የተለያዩ መልዕክቶችን ለማውጣት ቢሞክርም ሕዝቡ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በውጭ የሚገኙ የተሌአዩ አክቲቪስቶች ህዝቡ ተባብሮ በዚህ ስርኣት ላይ ለመነሳትና የሚፈጸመውን ግፍ በቻለው አጋጣሚ ሁሉ በመቃወም አጋርነቱን እንዲገልጽ ጠይቀዋል።

ሕዝበ ሕግ ረሱ ጻፈውን ሕገ መንግስት ሲፈልገው እየደፈጠጠ በሰላም ድምጹን ለማሰማት አደባባይ ባዶ እጁን ሲወታ የጥይት ምላሽ የሚሰጥ ሀይል የህዝቡን ሕገ መንግስታዊ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ መብት ሊፈቅድ አይችልም ሕዝቡ ተባብሮ ጸረ ወያኔ ተቃውሞውን አጠናክሮ ማሰማት አለበት ብለዋል።

በአማራ ከልል በመጪው ቅዳሜ በደብረ ታቦር እና ዕሁድ በባህር ዳር የወልቃይት የአማራነትን ጥያቄ እንደ ጎንደር ሁሉ በማያዳግም መንገድ ለማረጋገጥና ብሄራዊ ጭቆናውን ለመቃወም የተጠራ ሲሆን  እና በኦሮሚያ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የተጠራውን የቅዳሜ ሐምሌ 30 ሰልፍ ለማክሸፍ በአገዛዙ በኩል ተከታታይ መግለቻዎች እየተሰጡ ቢሆንም በሕዝቡ በኩል ለሰላማዊ ሰልፉ ጠንካራ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ከአካባቢዎች የሚወቱ መረጃዎች ይገልጻሉ። የኦሮሚያ ክልል የወቅቱ ጽ/ት አቶ ሙክታር ከድር ሰላማዊ ሰልፍ አልተጠራም ሕገ ወጥ ነው ሲሉ መግለጫ ቢያወጡም ተቃባይነት አላገኙም የሕወሓት ተላላኪነታቸውን አቁመው ትግሉን እንዲቀላቀሉ በመህበራዊ መዲአው እስከመጠየቅ የዘለቁ አሉ።

በደብረ ታቦር፣በባህር ዳር እና በመላው ኦሮሚአ የሚደረጉትን ሰልፎች ሁሉም ነጻነት ወዳድ በአገር ውስጥም በውጭም እንዲደግፍ ተደጋጋሚ ጥሪ በማህበራዊ ሚዲያ ጭምር እየቀረበ ነው፡

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *