Hiber Radio: የፊታችን ዕሁድ ነሐሴ 8 ቀን 2008 በ22 ከተሞች የሕወሃትን የግድያ እርምጃ በመቃወም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ

wollo-desse-001

በጎንደር፣ በባህርዳር እና በደብረ ታቦር የተደረገው ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን እሁድ ነሐሴ 8, 2016 22 ከተሞች እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ አስታወቁ::

በሽዋ:- ደብረብርሃን፣ ደብረሲና፣ አንኮበር፣ ሸዋሮቢት፣ ሸኖ፣ አዲስ አበባ እንዲሁም በጎጃም: ዳንግላ፣ ደብረማርቆስ፣ ደጀን፣ ኮሶ በር፣ ቡሬ፣ አዴትና ሞጣ: በተጨማሪም በወሎ:- ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ መቄት፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ቆቦ እና አላማጣ አምባገነኑ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ በመቃወምና የሕዝቡን ጥያቄዎች በመደገፍ የፊታችን እሁድ ነሐሴ 8, 2018 ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ::

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞችም እንዲሁ ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ እየተባለ ነው ይህ በእንዲህ እንዳለ በስልጣን ላይ ያለው የሕወሃት አገዛዝ በፌዴራል ስም በአካባቢዎቹ የፌዴራልና የአማራ ልዩ ሀይል የሚል ዩኒፎርም እአለበሰ የትግራይ ልዩ ሀይል አባላትን ለዘር ማጥፋት እርምጃው አሰማርቷል በተለይ እውነተና የብአዴን አመራሮች ጉዳዩን ሊአጤኑት ይገባል የሚሉ ማስጠንቀቂያዎች ከየአካባቢዎቹ ይወጣሉ። ሰልፉ በታቀደባቸው ቦታዎች አስቀድሞ ወጣቶችን ማፈስ ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም የሕሁዱ ሰልፍ በ22ቱ ከተሞች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ቅዳሜ ነብሰ ገዳዩ ስርኣት በጎንደርና በባህር ዳር በሕዝብ ተቃውሞ የደረሰበትን ክስረት ተከትሎ በወሰደው የጭካኔ እርምጃ እንዳይወገዝ ራሱ በጠራው የግዳጅ ሰልፍ ለማውገዝ መዘጋጀቱን በመጥቀስ የሕዝቡ ሰልፍ በተጠቀሱት ከተሞች ዕሁድ ነሐሴ 8 ቀን 2008 መሆኑን አስተባባሪዎቹ በአጽንዎት ገልጸዋል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *