Hiber Radio: የቅሊንጦ እስር ቤት እሳት ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ሁኔታ በአገዛዙ እንዲነሳ መደረጉን አንድ የእስር ቤቱ ጠባቂ አጋለጠ፣እሳቱን ጭምር ለማጥፋት በሚሞክሩ እስረኞች ላይ በቀጥታ ሲተኮስ ነበር፣የአቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የእስረኞቹ መጨረሻ አልታወቀም የሟቾች ቁጥር ከአርባ በላይ ደርሷል፣የካናዳ መንግስት እና ሽሪኮቹ በኢትዮጵያ እየደረስ ያለው የስብዓዊ መብት ረገጣን ችላ ማለታቸው ታላቅ ተቃውሞ ገጠማቸው

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ነሐሴ 29 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…በሕዝቡ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ተቃውሞ በመሪዎቹ ላይ እርምጃ ወስዶ የሕዝቡን ትግል የተቀላቀለውን ከሁለት ሻምበል በላይ ጦር ሰራዊት የዕምቢታ ጦር የሕዝቡ አጋር ነው ይሄ እርምጃ ማደግ አለበት ነገ ከነገ ወዲያ በክፍለ ጦር ደረጃ ተመሳሳይ እርምጃ ወስዶ  ከሕዝቡ ጎን መቆሙን እንዲቀጥል ሕዝቡ ተገቢውን መረጃ መስጠት አለበትሰራዊቱ ራሱ በሕወሓት ዘረኛ የጦር አዛዦች የተንገፈገፈ ነው። አሁንም ለመላው የሰራዊት አባላት ጥሪ አለኝ…> / ደረሰ ተክሌ የቀድሞ የሰራዊቱ የጥናትና ምርምር ሀላፊ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በመሪዎቹ ላይ እርምጃ ወስዶ የሕዝቡት ትግል ስለተቀላቀለው ሁለት ሻምበል ጦር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጡት ማብራሪያ(ያድምጡት)

< … አሁን በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው ግድያና አፈና ሌላው ቀርቶ እስረኞች በታሰሩበት እየደረሰባቸው ያለው ግፍ ይሄን ሕገ ወጥ ድርጊት ነው ተብሎ የሚታለፍ አይደለም።ከኢትዮጵያ አልፎ ለአካባቢው አገሮች አደገኛ አለመረጋጋት የሚያመጣ እርምጃ ስለሆነ ከዚህ ቀደም የተባበሩት መንግስታት የሳዳም መንግስት ኩርዶችን ሲጨፈጭፍ የወሰደውን አይነት እርምጃ ሊወስድ ይችላልየኦሮሞም ሆነ የአማራ ሕዝብ ሌላውም ኢትዮጵያዊ ጭምር በጋራ በትግሉ ወቅት ያነሳቸውን አብይ ጉዳዮች ያካተተ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት ለውጡን በጋራ ማፋጠን በጋራ ጠላት ላይ ማተኮር ያስፈልጋል ከዚህ በሁዋላ… >   ሔኖክ ጋቢሳ የህግ ባለሙያና መምህር ስለ ወቅታዊው ሁኔታ ለህብር ከሰጠን ቃለ መጠይቅ(ቀሪውን ያዳምጡ)

የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ፓለቲካዊ ሁኔታ በተመለከተ የስጡት አስተያየት አዲሱ የእንግሊዝ መንግስት በአቶ  አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስራት መለቀቅ ሙከራ  ዙሪያ የሰጠው ምላሽ እና የመብት ተሞጋቾች እና የአቶ እንዳርጋቸው ባለቤት ምላሽ(ልዩ ዘገባ)

በቬጋስ በመጪው ረቡዕ 10 ጊዜ የኢትዮጵያውያን ቀን ይከበራል በአገር ቤት ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ሳቢያ በዕለቱ የሙዚቃ ዝግጅት አይቀርብም (የኮሚኒቲው /ሊቀመንበር የሰጡትን ማብራሪያ ይዘናል)

ወታደሩ ወገኔ ሕዝብ ላይ አተኩስ(ግጥም)

ዜናዎቻችን

የቅሊንጦ እስር ቤት እሳት ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ሁኔታ በአገዛዙ እንዲነሳ መደረጉን አንድ የእስር ቤቱ ጠባቂ አጋለጠ

 እሳቱን ጭምር ለማጥፋት በሚሞክሩ እስረኞች ላይ በቀጥታ ሲተኮስ ነበር

የአቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የእስረኞቹ መጨረሻ አልታወቀም የሟቾች ቁጥር ከአርባ በላይ ደርሷል

በወሎ ከሁለት መቶ በላይ የመንግስት ሰራተኞች አገዛዙ በአማራ ላይ ለከፈተው ጦርነት ማብራሪያ የጠራውን ስብሰባ ተቃውመው ረግጠ ወጡ

ደሴ የቤት ውስጥ አድማ ቀጠለ

የቅሊንጦ የማጎሪያ ቤቱ ጠባቂዎች በልዪ የፖሊስ ሃይላት ተተኩ

የአትዮጵያዊው ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ዘመድ በአገዛዙ ታጣቂዎች ጥርሱ እንደረገፈ፣እግሩ በጥይት እንደ ተመታ ተናገረ

አትሌት ፈይሳ ወደ አገሩ ከተመለሰ ሞት ይጠብቀዋልየፈይሳ ዘመድ እማኝንነት

የካናዳ መንግስት እና ሽሪኮቹ በኢትዮጵያ እየደረስ ያለው የስብዓዊ መብት ረገጣን ችላ ማለታቸው ታላቅ ተቃውሞ ገጠማቸው

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳይን በቅርበት እየተከታተልነው ነውካናዳ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችበአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ ቀረበ

*አገዛዙ ግን ዛሬም በሩን ለውጭ ታዛቢዎች አልከፍትም እንዳለ ይገኛል

/ መረራ ጉዲና ተቃዋሚዎች በመንግስት ለውጥ ላይ ብቻ ሳይሆን  ከለውጡ በሁዋላ ባለ ሁኔታ በፍጥነት በጋራ መስራት አለብን ብለዋል

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas/hiber-radio-090416

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *