Hiber Radio: ድምጻዊ ኤልያስ ተባበል የሕዝቡን ትግልና ጥያቄ አዜመ

elias-tebabel-welekayit-002

በመሰንቆውና ባህላዊና ዘመናዊን ሙዚቃ እያዋዛ በማዜም የሚታወቀው አንጋፋው ድምጻዊ ኤሊያስ ተባባል በወቅታዊው የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ዙሪያ የሚያጠነጥን አዲስ የትግል ነጠላ ዜማ አዘጋጅቶ ዛሬ በዘሐበሻ ድህረ ገጽና ማህበራዊ ሚዲአ ገጽ ተሰራጨ:: የጎንደር አማራ ሕዝብ ወልቃይትን አላስነካም በሚል ስለመታገሉና በኦሮሞ እና አማራ ህዝቦች መካከል ስላለው የደም አንድነት የሚያጠነጥነው ይኸው ነጠላ ዜማ አማራ ትግሬ ትግሬ አማራ ላይሆን እያለ ያዜማል።ከዘፈኑ መካከል

<< ጀግናው ጎንደር

የግንባር ስጋ ነው ላመነበት ነገር ..

ወልቃይትን እንቁልጭልጭ

ጠገዴን እንቁልጭልጭ

አርማጭሆን እንቁልጭልጭ

አላስነካም ብሏል ጀግናው እኔ ተቀምጬ…>> የሚል ስንኝም አለው:: ያድምጡትና አስተያየትዎን ያስፍሩ ። በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በንጹሃን ላይ የከፈተውን ግድያ ተከትሎ አስቀድሞ ይሁኔ በላይ ሰከን በል ፣መስፍን በቀለ ሰላም ለኢትዮጵያ ናቲ ማን አሁን ተነካሁ የሚሉ ቀስቃሽ ዜማዎች መቻወታቸው አይዘነጋም።የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በወሬ የሕዝብ ነን ማለት ብቻ ሳይሆን ሕዝብ ሲገደል ከሕዝቡ ጎን መቆም አለባቸው የሚሉ ወቀሳዎች ዛሬም ለብዙዎቹ የኪነት ጥበብ ባለሙአዎች ይሰነዘራል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *