Hiber Radio: የሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ፣አዋጁ ለወታደሩ ተጨማሪ ስልጣን ይሰጣል ሲሉ የአፈና እቅዳቸውን ይፋ አደረጉ

hailemariam_desalgn-state-of-emeregency-001

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰሞኑን በእሬቻ ላይ የተወሰደውን ጭፍጨፋ ተከትሎ የተነሳውን ተቃውሞ በአፈና መቆጣጠር አቃተው አገዛዝ የሚኒስትሮች ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን ይፋ አደረገ።አሰቸኳይ ጊዜ አዋጁ እስከ ስድስት ወር ደረስ ይዘልቃል ዝርዝሩ በተከታታይ ይገለጻል ብሏል።

የትግሉ እየተጋጋለና የስርኣቱ እየተሸበረ መሄድ በስርዓቱ ላይ የፈጠረው መደናገጥ ውጤት ትላንት ከሰዓት ሕወሃት ተሰብስቦ ማምሻውን ም/ቤቱ ተሰብስቦ ወስኗል። አገሪቱ በሕወሃት ጥቂት ባለስልታናት የምትዘወር መሆኑን ራሱ ስርዓቱ ደጋግሞ ያገለጠበት ይሄ አስቸኳይ መግለጫ ሕወሃት ተሰብስቦ ለይስሙላ በሚኒስትሮች ም/ቤት የጸደቀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰረግማቸው ከኖረው የአገር ውስጥ ተቃዋሚዎች ጋር እመክራለሁ ፣በጥልቅ እታደሳለሁ ከሲቪክ ተቃማት ጋር እነጋገራለሁ ሲል በአቶ ሀይለማሪያም በኩል አስነግሯል።

የስርኣቱን የውድቀት ዋዜማ የሚአፋጥን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሆኑን የሚገልጹ ወገኖች ከተቃዋሚው ወገን ለውጡን ለማፋጠን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያስፈልጋል ሲሉም ይደመጣሉ።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የስርዓቱን መዳከምና ተጨማሪ ግድአዎችን ለመፈጸም ከመንቀሳቀስ ውጭ የሚጨምረው ነገር የለም ሲሉ የስርዓቱን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈናውን ለማጠናከር ካልሆነ ለውጥ እንደማያመታ ይገልጻሉ።ስርዓቱ በአስቸኳይ ከስልጣን እንዲወርድ እየጠየቁ አለው ሕዝባዊ ተቃውሞ በአገዛዙ ማስፈራሪያ ኣላማውን ሳያሳካ ወደ ሁዋላ እንደማይል ይጠቀሳል፡፤

አቶ ሐይለማሪአም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለመታደስ የበለጠ እድል ይሰጣል ያሉት ለማስመሰያ መሆኑንና የሕወሓት ዋና ኣላማ ተጨማሪ አፈና ማካሄድ መሆኑን አፈ ቀላጤው ጌታቸው ረዳ ስለ አዋጁ በሰጡት ማበራሪያ ገልጸዋል። ወታደሩ ሕግና ስርኣት ለማስከበር ተጨማሪ ስልጣን ተሰጥቶታል ብለዋል። አስቀድሞ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች ሕዝባዊውን ተቃውሞና ተጋድሎ ተከትሎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር የቆዩ ሲሆን የአዲሱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሌሎቹንም አካባቢዎች የይስሙላውን አስተዳደር በማውረድ መሉ ለሙሉ የሕወሃትን ወታደራዊ ቁጥጥር ለማጽናት ያለመ መሀኑን የጌታቸው ረዳ መግለቻ ያጋልጣል።

 ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *