Hiber Radio: በቤተ ክህነት ሙስና መኖሩን ያጋለጠው የኢትዮ-ምህዳር ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ታስረ

getachew-worku-aristed-002

የሳምንታዊው ኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ፣ በጋዜጣው ላይ ግንቦት 2007 ዓ.ም ታትሞ በወጣውና በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም ላይ የገንዘብና የንብረት ሙስና መኖሩን የሚያጋልጥ ዜና መስራቱን ተከትሎ፣ የቀረበበትን ክስ ሲከታትል ቆይቶ ዛሬ በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 6ኛ ወንጀል ችሎት የጥፋተኘት ውሳኔ ተሰጥቶት መታሰሩን ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዘገበ።

የጋዜጠኛውና የጋዜጣው ጠበቃ አቶ በሀይሉ ተስፋሁን እንደገለጹት፤ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 613/3 መሰረት ከባድ የስም ማጥፋት በሚል ደንበኛቸው ጥፋተኛ መባሉን መናገራቸውን ይሄው ዘገባ ይጠቅሳል።

እንደጠበቃው ምላሽ ከሆነ፣ በወቅቱ ዜናውን የሰራው ሪፖርተር ከሰበካ ጉባዔው የውስጥ ምንጮች በመረጃ ተገቢውን መረጃ ከማጠናቀር ባሻገር፤ የዜና ዘገባውን ሚዛናዊ ለማድረግ ሪፖርተሩና ጋዜጠኛ ጌታቸው ጉዳዩ የሚመለከተውን ሃይማኖታዊ ተቋም ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም “ዜናውን እንዳታወጡት!” የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ነበር።

ክሱ ከተጀመረም በኋላ ክሱን በበቂ ሁኔታ መከላከላቸው የሚናገሩት ጠበቃ በሃይሉ፣ በዛሬው የፍርድ ቤት ወሎ የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት ከተሰማ በኋላ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለህዳር 06 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ጋዜጠኛ ጌታቸውም ዛሬ ፖሊስ ጣቢያ የታስረ ሲሆን ከነገ በኋላ ባሉ ቀናት ወደቂሊንጦ እስር ቤት ይዘዋወራል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮ-ምህዳር በሀገራችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትታተም የነበረች ጋዜጣ ስትሆን በተለያዩ ጊዜያት ህትመቷ እየተቋረጠ በዋና አዘጋጁ የግል ጥረት አሁንም ደረስ ዘወትር ቅዳሜ የምትነበብ ጋዜጣ ነች። ጋዜጠኛ ጌታቸውም በተለያዩ ጊዜያት እየተከሰሰና እየታሰረ አስቸጋሪውን የኢትዮጵያ የጋዜጠኘት ሙያ በመጋፈጥ ላይ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስና የዜና ዘገባ ቀርቦበት ኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣ ላይ ክስ አቅርቦ ነርበ። ጌታቸውም እንደዋና አዘጋጅነቱ ክስ ቀርቦበት ከባልደረቦቹ ጋር ሀዋሳ ፍርድ ቤት ሲመላለልሱ፤ እነሱ ተጭነውበት የነበረው ባጃጅ ተሽከርካሪ ሆነ ተብሎ ተገጭቶ የመገልበጥ አደጋ ገጠመው።

የጋዜጣው ከፍተኛ አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነም በአደጋው በደረሰበት ከባድ አደጋ ከወገቡ በታች ፓራላይዝድ ሆኖ ዛሬም ድረስ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ይገኛል።

ጋዜጠኛ ኤፍሬም በሀገርና ከሀገር ወጪ የህክምና እርዳታ ቢደረግትለም ከገጠመው ችግር ሊፈወስ አልቻለም። በወቅቱም ጋዜጠኛ ጌታቸው ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶበት እንደነበረ አይዘነጋም ሲል ጋዜጠኛ ኤልያስ በዚሁ ዘገባው አስታውሷል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *