Hiber Radio: የፕ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ መልስ መታሰር ይጠበቅ እንደነበር ተገለጸ፣የሕወሓት አገዛዝ ግራ መጋባትና መደናበር አይሏል

dr-merera-gudina-003

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የወቅቱ ሊቀመንበርና በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ስማቸው በግንባር ከሚጠቀስ ሰላማዊ ታጋዮች ተርታ የሚጠቀሱት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቅርቡ በአውሮፓ ሕብረት ጋባዥነት በወቅቱ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለማስረዳት ብራስልስ ሰንብተው ሲመለሱ በአዲስ አበባ ቦሌ ላይ መያዛቸው የተጠበቀ እንደነበር የተለያዩ መረጃዎች ገለጹ።

ፕ/ር መረራ የአውሮፓውን ስብሰባ ተከትሎ በተለይ በስብሰባው ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መገኘትን በማስታከክ የተለያዩ አፍቃሪ ወያኔ ድህረ ገጾች እና የአገዛዙ ቴሌቪዥን ጭምር ፕ/ር መረራን ሲያብጠለጥሉና ሲዘልፉ የሰነበቱ መሆኑን ያዩ ወደ አገር ቤት እንዳይመለሱ ከተመለሱ ለማሰር እንደሚያስቡ ፍንጭ ሰጪ መሆኑን ገልጸው ነበር።

ፕ/ር መረራ ጉዲና ትላንት ከአውሮፓ ከገቡ በሁዋላ ቡራዩ የሚገኘው ቤታቸው በበርካታ ታጣቂዎች ተከቦ የነበረ ሲሆን የቤተሰብ አባሎቻቸው ጭምር መታሰራቸውነ አንዳንድ መረጃዎች ያሳያሉ።ፕ/ር መረራ በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ምርመራ በእስር ላይ ሲሆኑ የእስራቸው መንስዔ አውሮፓ ፓርላማ በጠራው ስብሰባ ላይ ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጎን መቀመጣቸው ብቻ መሆኑን አስቀድሞ ከነበረው መስፈራሪያ መሰረት አድርገው ብዙዎች ግምታቸውን ሰጥተዋል።አገዛዙ መገናኛ ብዙሃን አስቀድሞ የተደረገ ዛቻ ፕ/ር መረራ ወደ አገር ቤት እንዳይመለሱ ለማድረግ እንደነበር ገልጸው እሳቸው ያንን እያወቁ ወደ አገር ተመልሰው የመታውን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን አሳይቷል።

የኦፌኮና የመድረክ አመራር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና የአገዛዙን የአፈና አዋጅ ወደ ጎን በማድረግ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም በሁዋላ በተሌአዩ መንገዶች ሀሳባቸውን ሲሰጡና ሕወሃት/ኢህአዴግ በአፈናና በማሰር የሕዝቡን ጥያቄ እስከመጨረሻው አፍኖ እንደማይዘልቅ ደጋግመው ተችተዋል። ተቃዋሚዎች በተባበረ ክንድ እንዲታገሉ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርጉ ቆይተዋል፤

ከዶ/ር መረራ ጉዲና ቤት ታፍነው የተወሰዱ ቤተሰቦቻቸው ስም ዝርዝርና ብዛት ያልታወቀ ሰሆን እነሱም እንደ ዶ/ር መረራ ማዕከላዊ ይታሰሩ ሌላ ቦታ የታወቀ ነገር የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዶ/ር መረራ መታሰር የስርዓቱን የበለጠ ግራ መጋባት ያሳያል የሚሉ ወገኖች በቅርቡ የቀድሞው ኮሚነኬሽን ሚ/ር የሕወሓቱ ጌታቸው ረዳ አቶ በቀለ ገርባ የታሰሩት ወንጀል ስለሰሩ መንግስትን ለማፍረስ ስለተንቀሳቀሱ ነው በተቀዋሚነት ሰው አይታሰርም ዶ/ር መረራ መቼ ታሰሩ ሲሉ ተደምጠዋል። ዶ/ር መረራን ለሽፋን አስቀምቶሌሎቹን ለማሰሩ ሕጋዊ ሽፋን ለመስጠት የሞከረው አካል ሰሞኑን በጀመረው የተጠናከረ የማሰር እርምጃ አውቁን ፖለቲከና ማሰሩ በአገር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ አውነተና ተቃዋሚዎችን አስሮ ለመጨረስ መወሰኑን ያሳያል ብለዋል:፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና እ.ኤ.አ በ2010 ለቢቢሲ በሰጡት ቃል እኔ ብታሰር ሰላሳ ሚሊዮን አሮሞ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል ።የሕዝቡ ጥያቄ ካልተመለሰ እስር መፍትሄ አይደለም ማለታቸው ይታወሳል።

የወቅቱ የኮሚኒኬሽን ሚ/ር ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ ስለ ዶ/ር መረራ መታሰር ከውጭ ጋዜጠኞች ተጠይቀው እንደማያውቁ ተናግረዋል:፡ መረጃው ከአሳሪዎቹ ከህወሓት ባለስልጣናት ወደ ይስሙላዎቹ ባለስልጣናት ጋር እስኪደርስ ስንት ቀን ይፈጃል ? የሚል ጥያቄ ያስከትላል።

ዶ/ር መረራ ገዲና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሁዋላ በጅምላ እንደሚታሰሩት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ይቅር ወይም ያቅርቧቸው ታወቀ ነገር የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ፕ/ር መረራ ጉዲና መታሰራቸው አውግዞ የእስሩንም እርምጃ አናዳጅ ማለቱ ተጠቅሷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *