Hiber Radio: ሕወሓት በሕዝቡ ላይ የከፈተውን ጦርነት ለመመከት የአማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ሽንፈት የደረሰበት የሕወሓት ሰራዊት የገበሬ ጎጆና ሰብል ወደማቃጠል ገብቷል፣የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያውን አገዛዝ አስጠነቀቀ ፣የዶ/ር መረራ መታሰር የተጀመረው የዕርቅ ሂደት ላይ እንቅፋት ፈጥሯል አለ፣ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩና የተቃዋሚው ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ በእስር ቤት ድብደባ ተፈጸመባቸው ፣ትዊተር የአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ባልተገባ ባህሪያቸው ሳቢያ አካውንታቸውን እዘጋለሁ ሲል አስጠነቀቀ ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ህዳር 25 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየተባባሰ መሄዱን በተመለከተ ምዕራባውያን አሁን የሚያወጡት መግለጫ ጠንካራ ቢሆንም ዛሬም የተለመደ የዲፕሎማሲ መሞዳሞድ ያለበት ነው።ከዚህ አልፈው ሕዝቡ ላይ ግፍ እየፈጸመ ባለው ስርዓት ላይ ለምን ማዕቀብ አይጥሉም የሚለው አግባብ ቢሆንም ያንን አላደረጉም። እነሱ ትኩሳቱን የሚለኩት በሕዝቡ ላይ በሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሳይሆን አገዛዙ ሕዝቡን እየረገጠም ቢሆን መግዛት ይችላል ወይስ የሕዝቡ ተቃውሞ ጠንክሮ ማስተዳደር የማይችልበት ደረጃ ይደርሳል ነው። ወሳኙ እነሱ ሳይሆኑ ሕዝቡ ነው።ተቃውሞው ተጠናክሮ ካልቀጠለ ግን   …> የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ያሬድ ሀይለማሪያም በቤልጂየም የሚገኘው ስብስብ ለሰብዓዊ መብት ጉዳይ በኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር በወቅታዊ የሰብዓዊ መብትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ክፍል አንድን ያድምጡት)

<…በደህነቶች ታፍኜ ልክ እንደተሰረቀ ዕቃ በጨርቅ አይኔን ተይዤ ፣እጅና እግሬ በሰንሰለት  ታስሮ ትግሪኛ ተናጋሪዎች ብቻ ፍጹም ሰብዓዊ በሆነ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ለቀን ማታ ማታ እግሬ ከፍተኛ ደም እስኪፈሰው ፣ጀርባዬም እየደማ እንደ ዕባብ ተቀጠቀጥኩ።በስምንተኛው ቀን ዐይኔ ተሸፍኖ ወደማይታወቅ ሌላ የደህነት ጎሬ ተወስጄ 1 ወር 15 ቀን የተለመደ ድብደባ ከፈጸሙብኝ በሁዋላ አሁንም ወደ ሌላ ቦታ በመውሰድ ከፍ ያለ ድብደባ ተፈጸመብኝ ዐይኔ ተሸፍኖ የተወሰድኩበት ቦታ ሲያወረ እንደሰማሁት ደብረዘይት እንደሆነ አወቅሁየከዚህ ቀደሙ ሳይበቃ አሁን ደግሞ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስም ተይዤ ታስሬ እኔና ቤተሰቤ እንሰቃያለን…> ወጣቱ አስራት እሸቴ የመኢአድ አባል በአሁኑ ወቅት በደብረ ብርሃን እስር ቤት ያለበትን ሁኔታና ከትላንት እስከዛሬ በሕወሓት የተፈጸመበትን ግፍ ዓለም እንዲያውቅልን ብሎ ይፋ አድርጓል።ሕይወቱ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነው(የወጣቱን እሰረኛ ደብዳቤ ሙሉውን ያድምጡት)

 ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ጋምቢያን 22 ዓመታት የመሩት / ያያ ጃሜ ሽንፈታቸውን በአደባባይ መቀበላቸው እና ለአዲሱ / የእንኳን ደስ ያለዎ መልእክት የማስተላለፋቸው ውሳኔ ስልጣን ወይም ሞት ላሉት ለሕወሓት/ኢህአዲግ ገዥዎች እና ለአፍሪካ አምባገነኖች የሚሰጠው ትምህርት ሲቃኝ(ልዩ ጥንቅር)

<…የጎንዮሽ ትግል ይቁም ሲባል የሚመለከተው  ሁሉንም ወገን ነው።ሁሉም  ከስድብ ወጥቶ ምክንያታዊ ውይይት ላይ ማተኮር አለበት ።በተለይ በብዕር ስም ራሱን ደብቆ የሚሳደበውማ ኮልኮሌው ብዙ ነው።ይሄ መቅረት አለበት ሲባል ግን ምክንያታዊ ውይይት እንዲኖር መፍቀድ አለብን ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢ መልስ መሰጠት አለባቸው ..የታሪክ ሽሚያው ቀርቶ ሁሉም የሕዝቡን ትግል ቢደግፍ እዛ ላይ ሊያተኩር ይገባል…> ከጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ(የመጨረሻው ክፍል)

ሑበር በቬጋስ በቅርቡ የጀመረው የሁበርፑል አገልግሎትን በተለመከተ የሚነሱ ቅሬታዎች የአሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ (ያድምጡት)

ዜናዎቻችን

ሕወሓት በሕዝቡ ላይ የከፈተውን ጦርነት ለመመከት የአማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ሽንፈት የደረሰበት የሕወሓት ሰራዊት የገበሬ ጎጆና ሰብል ወደማቃጠል ገብቷል

ትግሉ ድጋፍ ይፈልጋል

የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያውን አገዛዝ አስጠነቀቀ

የዶ/ መረራ መታሰር የተጀመረው የዕርቅ ሂደት ላይ እንቅፋት ፈጥሯል አለ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩና የተቃዋሚው ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ በእስር ቤት ድብደባ ተፈጸመባቸው

ዳንኤል ሺበሺ ግራ ጆሮው ክፍኛ ተጎድቷል ሕክንናም ተልክሏል

ትዊተር የአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ባልተገባ ባህሪያቸው ሳቢያ አካውንታቸውን እዘጋለሁ  ሲል አስጠነቀቀ

ትራምፕየአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማን የሚያቃጥል ዜግነቱን ይነጠቃልማለታቸው ውዝግብ አስነሳ

ሁለት ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችን ቤይሩት/ሊባኖስ  ውስጥ በከሰል ጭስ ታፍነው ሲሞቱ ሌላዋ  ከሞት አደጋ ተረፈች

የሕወሓት/ኢህአዲግ መንግስት የጎረቤት /ሱዳን ታጣቂዎችን እንደማይረዳ ጁባ ማረጋገጫ ማግኘቷን ገለጸች

<<የኢህአዴግ ባለስልጣናት ስልጣኔ የጎደላቸው ናቸው>> የደ/ሱዳኑ ባለስልጣን ትችት

ሕዝቡ የጀመረውን የነጻነት ትግል አጠናክሮ ስርዓቱ በጉልበት መግዛት እንደማይችል ማሳየት አለበት ተባለ

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *