Hiber Radio: ሕወሓት በወ/ር አዜብ መስፍን በኩል በመተማና በሌሎችም የአማራ አካባቢዎች ሕዝቡን ለመከፋፈል ቤተክርስቲያን አሰራለሁ የሚል ዘመቻ ጀመረ፣ተጨማሪ የገበሬ ሚሊሻ እያሰለጠነ ሕዝቡን እርስ በእርሱ ሊያዋጋ እየጣረ ነው ተባለ፣ኢትዮጵያዊው በርካታ ስደተኞችን በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ በማሽጋገር ወንጀል ተከሰሰ ፣ግብጽ ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳን በማግባባት ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ መወጠኗ ተሰማ፣በርካታ መኮንኖቿ ጁባ ደ/ደቡብ ሱዳን ላይ መስፈራቸው ይነገራል፣በአማራ ክልላዊ መስተዳደር የተቀሰቀሰው ውጥረት አገረሸ፣ሀብታሙ አያሌው ለሕክምናው ያገዙትንና አብረውት የተጨነቁ ወገኖቹን አመሰገነ ድጋፋቸውና ጸሎታቸው እንዳይለየው ጠየቀና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ጥር 7 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በዋሽንግተን የተናኙት ተቃዋሚዎች በአሁኑ ወቅት አገሪቱ ያለችበትን አንገብጋቢ ሁኔታ የተረዱ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ተጨማሪ ጥፋቶችን ሳያደርስ ተባብረው ለመታገል የጋራ አገር አድን ግብረ ሀይል መስርተዋል። ልዩ ልዩ በጋራ የዲፒሎማሲውን ጨምሮ አገር ቤት ያለውን ትግል በአግባቡ ለመደገፍም ሆነ በዲፕሎማሲው ዘርፍ  ወጥ የሆነ ስራ ለመስራት ተስማምተዋል ይሄ ትልቅ እርምጃ ግን …> / ኤርሚያስ አለሙ ከኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አመራር አንዱ በዋሽንግተን ሶስት የአንድነት ድርጅቶች ጠርተውት የነበረውን የምክክር ጉባዔ በተመለከተ ከህብር  ተጠይቀው ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ( ክፍል አንድን  ያድምጡት)

<…በዋሽንግተኑ ጉባዔ ላይ አስር የተቃዋሚ ድርጅቶች ተገኝተዋል። ሌሎችም እንዲገኙ የተጋበዙ ነበሩ። የኢትዮጵያን አገራዊ ህልውና የሚቀበሉ የብሄርም ሆነ ህብረ ብሄራዊ የሆኑ ድርጅቶች በጋራ በምክክር ጉባዔው ላይ በመገናኘት በጋራ የሚያሳስባቸው መጪው የአገሪቱ ሁኔታ ላይ በአግባቡ ተነጋግረዋል። አገር አድን ግብረ ሀይሉን ጨምሮ ልዩ ልዩ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላትን አዋቅሯል ይሄ የነበረውን የአመራር ክፍተት ግንዛቤ ውስጥ ያደረገ የተሻለ ስራ መስራት የሚያስችል ነው …> አቶ ስለሺ ጥላሁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር /ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር ስለ ዋሽንግተኑ የምክክር  ጉባዔ  ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድን ያዳምጡት)

<…በአሁኑ ወቅት በጎንደር እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት እጅግ አሳሳቢ ነው። ሕወሃት በተቀነባበረ ሁኔታ በባህርዳርና በጎንደር ራሱ ቦንብ ከማፈንዳት ጀምሮ ሕዝቡን በማሸበር በመደብደብ ወጣት የተባለ ያለ ጥያቄ ከየመንጉ እያፈሱ ማሰር ተለመደ ነው። የጥምቀትን በዓል አስታኮ ከፍተኛ ሰራዊት ወደ ጎንደር የገባው በእሬቻ በኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አይነት ጭፍጨፋ ለማካሄድ ነው።ሁሉም ወገን ትላንት ጋምቤላው ሲጠቃ እኔም ጋምቤላ ነኝ ኦሮሞው ሲጠቃ እኔም ኦሮሞ ነኝ እንዳለው በጋራ አጋርነቱን ማሳየት በማህበራዊ ሚዲያው ዘመቻ ብቻ ሳይሆን በጎንደር፣በጎጃም  እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በጋራ ማውገዝ መሰለፍና ተቃውሞውን መግለጽ ይጠበቅበታል ሕዝብ እየሞተ የትግሉ መሪ እኔ ነኝ እኔ ነኝ የሚባለውም  መቅረት ያለበት ነው ታጋዩ ሕዝቡ ነው…> አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ በወቅታዊው የአማራ ተጋድሎና የሕወሓት አፈና ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ ቃለ  የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

የአሜሪካው / ባራክ ኦባማ የመጨረሻ የስንብት ንግግራቸውን ተከትሎ የተሰጡት ዓለማቀፋዊ ድጋፎች እና ነቀፌታዎች (ልዩ ጥንቅር)

የማርቲን ሉተር ኪንግ በዓል ስናስብ አርቆ አሳቢው ሕልመኛውን ዛሬ ላይ ስንዘክር (ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ሕወሓት በወ/ አዜብ መስፍን በኩል በመተማና በሌሎችም የአማራ አካባቢዎች ሕዝቡን ለመከፋፈል  ቤተክርስቲያን አሰራለሁ የሚል ዘመቻ ጀመረ

ተጨማሪ የገበሬ ሚሊሻ እያሰለጠነ ሕዝቡን እርስ በእርሱ ሊያዋጋ እየጣረ ነው ተባለ

ኢትዮጵያዊው ስደተኛ በርካታ ስደተኞችን በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ በማሽጋገር ወንጀል ተከሰሰ

“እኔ ተራ ደላላ እና የድርጊቱ ስለባ እንጂ ወንጀለኛ አይደለሁም”ተጠርጣሪው ለችሎት የሰጠው ምላሽ

ግብጽ ደ/ሱዳን እና ኡጋንዳን በማግባባት ጸረ ኢትዩጵያ ዘመቻ መወጠኗ ተስማ

በርካታ የግብጽ መኮንኖች ጁባ/ደቡብ ሱዳን ላይ መስፈራቸው ይነገራል

የአማራ ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ግፍ በሚፈጸምበት ማዕከላዊ እስር ቤት ያለበት ሁኔታ አልታወቀም

የአማራ ተወላጅ የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በብሄራቸው ሳቢያ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጸ

ሀብታሙ አያሌው  ለሕክምናው ያገዙትንና አብረውት የተጨነቁ ወገኖቹን አመሰገነ ድጋፋቸውና ጸሎታቸው እንዳይለየው ጠየቀ

በአማራ ክልላዊ መስተዳደር የተቀስቀስው ውጥረት አገረሽ

አገዛዙ ለሰሞኑ ጥቃት የተቃዎሚዎች እጅ አለበት ባይ ነው

ጀግናው አትሌት ፈይሳ ለሊሳ ዳግም በማራቶን አደባባይ ለሕዝቡ ያለውን አጋርነት የተቃውሞ ምልክቱን በማሳየት ገለጸ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይት ዎች  ያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈጸመበት ዓመት እንደነበር አስታወቀ

የጥምቀት ክብረ በዓል በክሊፎርኒያው ሎሳንጀለስ ከተማ ውስጥ በደማቅ ስነስርዓት ተከበረ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *