Hiber Radio: የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ያሬድ ኃይለማርያም በሃብታሙ አያሌው ላይ በተፈጸመው ስቃይ እና በሌሎችም የሕወሓት ወንጀሎች ዙሪያ ይናገራል

<… በአዲስ አበባ ውስጥ ማዕከላዊ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቪላዎች ስም የሌላቸው እስር ቤቶች ሆነው ማሰቃያ ይፈጸምባቸዋል።ሀብታሙ አያሌው የደረሰበትን ሰቆቃ ሲናገር ስሰማ በጣም አዝኜያለሁ ነገር ግን ሀብታሙም ከባህሉ ከሀይማኖቱና ለአድማጭ ጭምር በመጠንቀቁ ሙሉ ለሙሉ የተፈጸመበትን ግፍ የተናገረ አይመስለኝም ።ትላንትም እንደ ሀብታሙ ያለ እና በሀብታሙ ላይ ከደረሰውም በላይ ስም ባላቸውና በሌላቸው እስር ቤቶች ብዙ ግፎች ተፈጽመዋል ዛሬም ያ አልቆመም። ችግሩ ይሄን ሰቆቃ ለአንድ ሰሞን ሰምተን እናዝናለን እንቆጫለን ቆይተን ትኩረታችን ሌላ ነው ።እነዚህን ግፍ ፈጻሚዎች በዓለም አቀፍ የተለያዩ ቦታዎች ለመፋረድ ይቻላል ይሄን ግን ማድረግ አልቻልንም ።አሁንም ግን እነሱን ለመፋረድ ስራውን የሚሰራ ተቋም ያስፈልገናል …> የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም ከቤልጂየም በወቅታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ ( ያዳምጡት)

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *