Hiber Radio: እውቁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ የብሄራዊ አንድነት ጥሪ አቀረበ፣ፖለቲካ ሀጢያት ሊሆን እንደማይገባ ገለጸ፣በፈጠራ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ክስ ዕድሜ ልክ የተፈረደባቸው ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ማንንም መጉዳት የማይፈልጉ መልካም ዕናት መሆናቸው ተገለጸ፣በመቀሌ ተደብድበው ይቅርታ እንዲጠይቁ ታግተው የነበሩ የባህር ዳር ከነማ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ተለቀው ጉዞ ጀምረዋል፣ እንደ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በውሃ ላይ እራመዳለሁ ያሉ ፓስተር ህይወታቸውን አጡ፣በደ/ሱዳን ውስጥ በጦር መሣሪያ ግዢ ላይ የነበሩ የኢህአዲግ ተቃዋሚዎች ሰሞኑን መታሰር ባለስል ጣነቱን አወዛገበ፣በአማራ ክልል ወላጆች እየተቃወሙ ከ10 ዓመት በላይ በሆናቸው ህጻናት ሴቶች ላይ ዘራቸውን እንዳይተኩ ለማድረግ የወሊድ መቆጣጠሪያ በሰውነታቸው መቀበሩ ተጋለጠ ሌሎችም

የህብር ሬዲዮ  ግንቦት 7 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…መቀሌ ኳስ ሊጫወቱ የሄዱትን የባህር ዳር ከነማ ተጫዋቾች ሕዝቡ ዘራቸውን እየጠቀሰ ሲሰድባቸው ነበር ገና መቶ ዓመት እንገዛለን የሚሉ ፉከራዎች ነበሩ። የተበደሉት የተደበደቡት በተቃራኒው ታስረዋል ይሄ የሚያሳየው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በካርታ ላይ ካልሆነ በስተቀር… > ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሙሉቀን ተስፋው ስለ መቀሌው በባህር ዳር ከነማ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ላይ ስለተወሰደው ጥቃት ካደረግነው ውይይት የተወሰደ (ቀሪውን ያድምጡት)

<… በማዕካላዊ ሁሉም እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ፣አሳምነው ጽጌ የደረሰባቸውን ግፍ ለመናገር ሲሞክሩ እንዳይናገሩ ይከለከሉ ነበር። እናቴ ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ላይ ግፍ ተፍሟል ብዙ ጊዜ ግን እነሱ ስለከፈሉት መስዋዕትነት አይነሳም ሊረሱ አይገባም…አምላክ እናቴን በሕይወት አቆይቷት ከእነዚህ አውሬዎች እኢ ወጥታ እንዳገኛት ምኞቴ ነው ።እናቴ ባለሽበት እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሰሽ… > ናርዶስ ዘሪሁን በቃሊቲ በሀሰተኛ መፈንቅለ መንግስት ክስ ሳቢያ ዕድሜ ልክ በካንጋሮ ፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ ልጅ ጋር ካደረግነው ቆይታ(ቀሪውን ያድምጡት)

<…እናትነት ከባድ ነው ደስታም ነው …በሎስ አንጀለስ እኛ ልጆቻችን የኦቲዝም ችግር ያለባቸው ወላጆች በጋራ ተሰባስበን ብዙ እየሰራን ነው ይሄ ጥንካሬን ይሰጥሻል…> ወ/ሮ ፌቨን ፋንቱ ከራሱዋ አልፋ ለሌሎች ብርታት ስለሆነችበት ጥረቱዋ የእናቶችን ቀን አስመልክተን እንግዳ አድርገናታል ታወጋናለች(ቀሪውን ያድምጡ)

የዳግማዊ መአሕድ ያካሄደውን የአማራ ዓለም አቀፍ ጉባዔ በተመለከተ ቆይታ ከዲሲ ሜትሮ የዳግማዊ መአሕድ ሊቀመንበር ጋር(ያድምጡት)

የብሔራዊ ምርመራ ቢሮ(FBI)ዳይሬክተሩን በቀጭን ትእዛዝ ያባረሩት የአሜሪካው ፕ/ት ትራምፕ የገጠማቸው ተቃውሞ እና ድጋፍ ሲቃኝ(ልዩ ዘገባ)

ለትዳር ጓደኞቻቸው ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ ሲሉ እጅግ አሳቃቂ ግርፋት የሚደርስባቸው ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችንን በእናቶች ቀን በጨረፍታ ስናስታውሳቸው (አጭር ዘገባ)

 ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

እውቁ አርቲስት  ቴዲ አፍሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ የብሄራዊ አንድነት ጥሪ አቀረበ

ማንም ሰው ከፓለቲካ ተጽእኖ ውጪ ሊሆን አይችልም፣ስለ ፓለቲካዊ ጉዳዪች መነጋገር ሐጢያት አይደለምቴዲ አፍሮ ለአሶሼትድ ፕሬስ ከሰጠው አስተያየቱ የተወሰደ

በዓለም ታላላቅ መገናኛ ብዙሃን ላይ የቀረበው ቴዲ አፍሮ ስርዓቱ በተቆጣጠረው የአገሪቱ ቴሌቪዥን የትግራይ ተወላጅ የስርዓቱ ደጋፊዎችን ተቃውሞ ተከትሎ እንዳይተላለፍ ታገደ

፣በፈጠራ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ክስ ዕድሜ ልክ የተፈረደባቸው ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ማንንም መጉዳት የማይፈልጉ መልካም ዕናት መሆናቸው ተገለጸ

የሮማው ሊቀ ጳጳስ የዛሬ 100 ዓመት ድንግል ማርያምን በራዕይ የተመለከቱ እና ስለሁለተኛው የአለም ጦርነት የተነበዩ ሁለት የበግ እረኞችን በጻድቅነት ሰየሙ

እንደ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በውሃ ላይ እራመዳለሁ ያሉ ፓስተር ህይወታቸውን አጡ

በመቀሌ ተደብድበው ይቅርታ እንዲጠይቁ ታግተው የነበሩ የባህር ዳር ከነማ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ተለቀው ጉዞ ጀምረዋል

የሕክምና ዕርዳታ በማድረጉ የታፈነው የአማራ ብሄር ተወላጅ የመቀሌ አይደር ሆስፒታል ዶክተር የደረሰበት አልታወቀም

በደ/ሱዳን ውስጥ በጦር መሣሪያ ግዢ ላይ የነበሩ የኢህአዲግ ተቃዋሚዎች ሰሞኑን መታሰር ባለስል ጣነቱን አወዛገበ፣

የደ/ሱዳን መንግስት ተገቢውን እገዛ እያደረገልን ነውየተቃዋሚው የኢትዮጵያ አንድነት ግንባር ሹሙ / ፓል ኡጁሉ ለዜና ሰዎች ከሰጡት ማረጋገጫ የተወሰደ

በአማራ ክልል ወላጆች እየተቃወሙ ከ10 ዓመት በላይ በሆናቸው ህጻናት ሴቶች ላይ ዘራቸውን እንዳይተኩ ለማድረግ የወሊድ መቆጣጠሪያ በሰውነታቸው መቀበሩ ተጋለጠ ሌሎችም

ሰሞነኛው የግብጽ እና የሱዳን ፓለቲካዊ ተቃርኖ በኢትዮጵያው የህዳሴ ግድብ ህልውና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳይፈጥር ተስግቷል

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮhttps://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas/hiber-radio-051417ች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *