Hiber Radio: ፍትሕ ለኢትዮጵያ ፍትሕ ለማዋይሽ በሚል በመጪው ቅዳሜ ዘመቻ ይጀመራል

ፍትሕ ለኢትዮጵያ ፍትሕ ለማዋይሽ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ከነገ በስቲያ ቅዳሜ በአገር ቤትና በውጭ በቃሊቲ እስር ቤት የዕድሜ ልክ እስረኛ የሆኑትን አራት ልጆች እናት ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙንና ሌሎች በግፍ እስር ላይ ያሉ እናቶችና ሌሎች ሴቶችን የህሊና እስረኞች የሚታሰቡበት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ጥሪ ቀረበ።

ናርዶስ ዘሪሁን ከወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ልጆች አንዱዋ እና ሌሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በጋራ በሚያስተባብሩት በዚህ ዘመቻ በ2001 ዓ.ም በሀሰተኛ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ከእነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጋር በጋራ ተከሰው በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ከፍተኛ ስቃይ እንደተፈጸመባቸው ከዚህ ውስጥ የሕወሓት አገዛዝ ዘረኛ መርማሪዎች ጡታቸውን በምላጭ እየተለተሉ ግፍ እንደፈጸሙባቸው ተደጋግሞ መዘገቡ አይዘነጋም።

እነ ናርዶስ ዘመቻውን አስመልክቶ ባወጡት መግለጫ <<ፍትሕ ለኢትዮጵያ! “ፍትሕ ለእማዋይሽ”

የእናት ኢትዮጵያንም ሆነ የኢትዮጵያ አንጡራ እናቶች ግፍና መከራ ከማናችንም የተሰወረ እውነታ አይደለም።

የዚህ የድረ_ገፅ ዘመቻ ዋነኛ ዓላማም የወያኔ አገዛዝ፣ የእስረኛዋን ኢትዮጵያ ብሎም የእስረኛ እማዋይሽ ዓለሙን ነፃነት ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ይመልስ ዘንድ ተፅዕኖ መፍጠር ነው። በመሆኑም “ፍትህ ለኢትዮጵያ! ፍትህ ለእማዋይሽ” በሚል መርህ ቃል፣ በመጪው ቅዳሜ 17/06/2017 በ8 ሰዓት ወይም 2PM በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ማለትም……

Twitter

Facebook Page

Facebook Profile በመቀየር

Google Plus

Instagram

አመቺ በሆኑ መንገዶች አማካኘነት ፍትህ ለኢትዮጵያ! “ፍትህ ለእማዋይሽ” በሚል መሪ ቃል የምናደርገውን ዘመቻ ይቀላቀሉ ዘንድ፣ አንድም በታሰረች አገር፣ አንድም በታሠረች እናት ስም እንጠይቃለን!! >> ሲሊ ጥሪ አቅርበዋል። ለዘመቻው የሚሆን ተጨማሪ ፎቶ ግራፎች ተያይዘው እንደሚቀርኑ ገልጸዋል።

የዓለም የእናቶች ቀንን አስመልክቶ ናርዶስ ዘሪሁን ስለ ወ/ሮ እማዋይሽ ዓለሙ ከህብር ሬዲዮ ጋር ባለፈው አድርጋ የነበረው ቃለ መጠይቅ ለማስታወስ ተያይዙ ቀርቧል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *