Hiber Radio: ሕወሓት ያዘጋጃቸው የአማራ ሕዝብን የማይወክሉ ሽማግሌዎች ወደ አክሱም ሊሄዱ መሆኑ ተገለጸ፣ሽማግሌ ከተባሉት ውስጥ የደህንነት አባላት ይገኙበታል፣ከለንደኑ የእሳት ቃጠሎ ከ19ኛ ፎቅ ላይ ነፍሷ የተረፈው የ6ዓመቷ ጨቅላ ሰቆቃዋን በስዕል ማቅረቧ ብዙዎችን አሰደነቀች፣ኢትዮጵያውያን አገዛዙ ከሚሰጣቸው ዕለታዊ አጀንዳ ወጥተው ተባብረው ጸረ ወያኔ ትግሉ ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ ቀረ፣የኤርትራ ሰራዊት ከጅቡቲ ጋር ያወዛገበው የራስ ዱሜራን መሬትን ተቆጣጠረ፣የግፍ እስረኛዋ እማዋይሽ አለሙ በማህበራዊ ሚዲያው በዘመቻ ታሰቡ፣በኢትዩጵያ ውስጥ እድሜ ጠገብ እና ታሪካዊ መስጊድ ተገኘ፣በኦሮሚያ የቁቤ ቋንቋን ተከትሎ ስርዓቱ በራሱ እያደረገ ያለው ለውጥ አዲስ ሕዝባዊ ቁጣ ሊቀሰቅስ ይችላል ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ሰኔ 11 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…የተናጠል ተቃውሞ ተሞክሮ አልተሳካም። ጠንካራው የኦሮሚያ ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ጠንካራው የሙስሊሞች ተቃውሞ እየተካሄደ ያለው የአማራው ተጋድሎ እና ሌሎቹም በተናጠል አይተናል ተፈላጊውን ውጤት አምጥተዋል ወይ? የሚያዋጣን ትግሉን የጋራ ማድረግ ስንችል ነው…በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት የታየው ተቃውሞ በሌላ አገር መንግስት ለውጧል እኛ ጋር ግን… > አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…በቬጋስ የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን በዲሞክራቲክ ፓርቲ ስር ያቋቋሙት ቡድን የፖለቲካ ተሳትፎው ውጤት እያመጣ ነው።ለመጀመሪያ ጊዜ የእኛን ጉዳይ ሰምቶ በሲቲ ካውንስሉ ውስጥ ሊሰማን የሚችል አንድ ሰው እንዲመረጥ አስተዋጽዎ አድርገናል የፖለቲካ ትግላችን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት…> አቶ አሌክሳንደር አሰፋ በክላርክ ካውንቲ በዲሞክራቲክ ፓርቲ ስር የሚገኘው ቡድን ሊቀመንበር ከህብር ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን ያድምጡት)

<…በትግሉ ውስጥ ጥርጣሬ የሚፈጥሩ አለመተማመንን የሚያስከትሉ መረጃ የሌላቸው ወሬዎች ይወሩ ነበር ። በአንድነት ፓርቲ ውስጥ እኔ ከመታሰሬ በፊት ከደህነት ጋር ግንኙነት ስላለው ሰው ተናግሬ ነበር ። ከታሰርኩ በሁዋላ አንድነት ፓርቲ ሲፈርስ የነበሩት አመራሮች እውነታውን ተረድተዋል። አሁንም መረጃ እንጂ ማስረጃ የለኝም እንጂ…>   ሀብታሙ አያሌው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከህብር ሬደዮ ጋር ካደረገው ሰፋ ያለ ውይይት የተወሰደ (ክፍል ሁለትን አድምጡት)

በሎንዶን ከተማ በባለ 24 ፎቁ ላይ በተከሰተው አሳዛኝ የእሳት አደጋ ዙሪያ የኢትዩ ጵያዊያኖች እና የኤርትራዊያኖች ሰቆቃ እና የጀግነት ተጋድሎ በከፊል ሲቃኝ(ሪፓርታዥ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ሕወሓት ያዘጋጃቸው የአማራ ሕዝብን የማይወክሉ ሽማግሌዎች ወደ አክሱም ሊሄዱ መሆኑ ተገለጸ

ሽማግሌ ከተባሉት ውስጥ የደህንነት አባላት ይገኙበታል

ከለንደኑ የእሳት ቃጠሎ 19 ፎቅ ላይ ነፍሷ የተረፈው 6ዓመቷ ጨቅላ  ስቆቃዋን በስዕል ማቅረቧ ብዙዎችን አሰደነቀች

መኖሪያ ቤቴን ለምን ያቃጥሉብኛል?” 6አመቷ ዩሃና ዬሀንስ የግርጌ ማስታውሻ የተወሰደ

ኢትዮጵያውያን አገዛዙ ከሚሰጣቸው ዕለታዊ አጀንዳ ወጥተው ተባብረው ጸረ ወያኔ ትግሉ ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ ቀረበ

በኢትዩጵያ ለረሀብ የተጋለጡ ወገኖች ቁጥር በእጥፍ እንዳያሻቅብ ለጋሾች ስጋት ገብቷቸዋል

ሁኔታዎች መጥፎ ደረጃ ላይ ናቸው፣የከፋም ሊመጣ ይችላልበተመድ የስብአዊ ጉዳዩች ሹሙ አህመድ አል መርኪ ፍራቻቸውን ሲገልጹ

የግፍ እስረኛዋ እማዋይሽ አለሙ በማህበራዊ ሚዲያው በዘመቻ ታሰቡ

እስረኛዋ ከቃሊቲ በላኩት መልዕክት እየከፈሉ ባሉት መስዋዕትነት እንደማይቆጩ ገልዋል

የአሜሪካ እና የእንግሊዝ መንግስታት ዜጒቻቸው ወደ ኢትዩጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ በጥንቃቄ እንዲያደርጉት አስገነዘቡ

ዜጒቻችን ቢታሰሩ እንኳን የኢህአዲግ መንግስት መረጃ አይሰጠንምየአሜሪካ መንግስት ግምገማ እንዳተተው

በኦሮሚያ የቁቤ ቋንቋን ተከትሎ ስርዓቱ በራሱ እያደረገ ያለው ለውጥ አዲስ ሕዝባዊ ቁጣ ሊቀሰቅስ ይችላል

በአለማቀፉ ቀይመስቀል ለኢህአዲግ ፓሊሶች ስለ አለማቀፋዊ የስብአዊ መብት እና እንክብካቤ ስልጠና ሰጠ

አምቦ ተማሪዎች ተቃውሞ ጀምረው /ቤቶች እየተዘጉ ነው

/ ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዬኤርትራ የድንበር ይገባኛል ግጭት ለጠፋው 70ሺህ ህይወት አሜሪካንን ተጠያቂ አደረጉ

የኤርትራ ሰራዊት ከጅቡቲ ጋር ያወዛገበው የራስ ዱሜራን መሬትን ተቆጣጠረ

ጅቡቲ ጦሯን በተጥንቀቅ አቁማለች፣የአፍሪካ ህብረት መረጋጋት ይስፈን ብሏል

ሕወሓት በአገሪቱ ስም የራሱን ሰዎች ብቻ በዓለም አቀፍ ተቋማት ማሾሙን ቋጥሏል አንድ ወታደራዊ ባለስልጣኑ የኢጋድ ከፍተኛ ወታደራዊ አማካሪ ሆነው ተሾሙ

በኢትዩጵያ ውስጥ እድሜ ጠገብ እና ታሪካዊ መስጊድ ተገኘ

እና ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *